Tuesday, May 30, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበአሳንሰር ደኅንነት ላይ ቁጥጥር ካልተደረገ በተጠቃሚዎች ላይ አደጋ ሊያስከትል እንደሚችል ተነገረ

በአሳንሰር ደኅንነት ላይ ቁጥጥር ካልተደረገ በተጠቃሚዎች ላይ አደጋ ሊያስከትል እንደሚችል ተነገረ

ቀን:

በኢትዮጵያ በአገልግሎት ያሉ ሊፍቶች ደኅንነታቸው በገለልተኛ ተቋም አለመረጋገጡ፣ ተጠቃሚዎችን አደጋ ላይ ሊጥል እንደሚችል የዘርፉ ባለሙያዎች አስጠነቀቁ።

በኢትዮጵያ ያለው የኮንስትራክሽን መመርያ መሠረት ከአራት ወለል በላይ ያላቸው ሕንፃዎች ሊፍት እንዲገጥሙ የሚያስገደድ ሲሆን፣ ዘርፉን እንዲቆጣጠሩ ሥልጣን የተሰጣቸው የመንግሥት ተቋማት ግን ሊፍት መኖሩን ከማረጋገጥ ባለፈ የደኅንነት ሁኔታውን አያረጋግጡም።

በተለይ በአዲስ አበባ ያሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ሊፍት የተገጠመላቸው ሕንፃዎች ቢኖሩም፣ በጥቅም ላይ በሚውሉበት ወቅት ያላቸው የደኅንነት ሥጋት አለመረጋገጡ ለአደጋ ተጋላጭ ሊያደርጋቸው እንደሚችል ተጠቁሟል።

በምሥራቅ አፍሪካ ኬኒያና ጂቡቲ ያሉ ሊፍቶች በጥቅም ላይ ከዋሉ አንስቶ የደኅንነት ሁኔታቸው በየሦስት ወሩ እየተገመገመ ሠርተፍኬት እንደሚሰጡ የሚያነሱት በዘርፉ ከአሥር ዓመት በላይ ልምድ ያካበቱት የሊፍት ባለሙያ የሆኑት አቶ ዳዊት መኮንን፣ መሰል ቁጥጥር በኢትዮጵያ ሊተገበር ይገባል ይላሉ።

ሊፍቶች ከተገጠሙ በኋላ ያላቸው የደኅንነት ሁኔታ በሦስተኛ ወገን አለመረጋገጡ፣ በተጠቃሚዎች ደኅንነት ላይ ችግር ሊፈጥር እንደሚችል አስጠንቅቀዋል። ‹‹በአሁን ሰዓት ቁጥጥር እየተደረገ ያለው በግንባታ ወቅት ሊፍት መገጠም ወይም አለመገጠሙን ነው›› ያሉት አቶ ዳዊት፣ ይህ ቁጥጥር በድህረ ኮንስትራክሽን ወቅት ሊተገበር ይገባል ብለዋል።

በኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ከማንኛውም የኢኮኖሚ ዘርፎች የበለጠ ዕድገት ያሳየ ሲሆን፣ ባለፉት አሥርት ዓመታት በየዓመቱ በአማካይ ከ13 በመቶ በላይ ዕድገት አሳይቷል። ከግንባታ መስፋፋት ጋር ተያይዞ የመጣው ዕድገት በሊፍት ማስመጣትና መግጠም ላይ ለተሰማሩ ድርጅቶች የገበያ ዕድል ከፍቷል።

ሊፍት አስመጪዎች የመግጠምና ከተገጠመ በኋላ የጥገና ሥራዎችን ደርበው ይሠራሉ የሚሉት በሲቪል ምህንድስና ከ17 ዓመት በላይ ልምድ ያላቸው አቶ አንተነህ ፀጋዬ፣ ድርጅቶቹ ከአምስት እስከ አሥር ዓመታት የሚደርስ ዋስትና መስጠታቸው፣ ደኅንነት የማረጋገጥ ጉዳት ትኩረት እንዳያገኝ ማድረጉን ያነሳሉ።

በተለያዩ አካባቢዎች ፍጥነታቸው የደከመ፣ በተደጋጋሚ የሚቆሙና ለተጠቃሚዎች ምቹ ያልሆኑ ሊፍቶችን መመልከት የተለመደ መሆኑን የገለጹት አቶ አንተነህ፣ ዘርፉን የሚቆጣጠረው ተቋም ከግንባታ በኋላ ከገንቢዎች ጋር ያለው ግንኙንት ስለሚያከትም የሚቆጣጠር አካል የለም ይላሉ። ይህም ከደኅንነት አኳያ ትክክል አይደለም ያሉት አቶ አንተነህ፣ የሊፍቶች ደኅንነት በየጊዜው እያረጋገጠ ዕውቅና የሚሰጥ ተቋም ያስፈልጋል ብለዋል።

የመቆጣጠሩን ኃላፊነት ለግል አልያም ለመንግሥት ተቋም ነው መሰጠት ያለበት የሚለው ሊያከራክር ይችላል የሚሉት አቶ አንተነህ፣ ይህ ከአገሪቷ ፖሊሲ ጋር የሚገናኝ ጉዳይ ነው ብለዋል። የግል ዘርፍ ራሱን በራሱ እንዲቆጣጠር የማድረግ ልማድ ያልተለመደ ነው፡፡ ስለዚህም የሊፍት ደኅንነት ቁጥጥሩን መንግሥት ቢይዘውም ችግር አይኖረውም ብለዋል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመስቀል አደባባይ የመግቢያ ክፍያ ለምን?

ወጣቶች፣ ሕፃናትና አረጋውያን ሳይቀሩ መንፈሳቸውን የሚያድሱበት እንዲሁም ሐሳባቸውን በነፃነት...

በሕገ መንግሥቱ የተዋቀረው ‹‹የብሔር ፖለቲካ›› እና ‹‹ሥርዓቱ›› ያስከተለው መዘዝና መፍትሔው

(ክፍል አራት) በዓቢዩ ብርሌ (ጌራ) ባለፈው ጽሑፌ (በክፍል ሦስት) አሁን ያለው...

የኢትዮጵያ ኅብረተሰብና የመንግሥት መሪ ምሥል

በበቀለ ሹሜ በ2015 ዓ.ም. መጋቢት ወር ውስጥ ይመስለኛል በ‹ሸገር ካፌ›...

ዩኒቨርሲቲዎችን ራስ ገዝ ያደረገው አዋጅ የፍትሐዊነት ጥያቄ አስነሳ

በቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት ስምንት ዩኒቨርሲቲዎችን ራስ ገዝ በማድረግ ተቋማዊና...