Tuesday, September 26, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ተቋርጦ የነበረው የሊግ ጨዋታ በአዳማ ይቀጥላል

ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ተቋርጦ የነበረው የሊግ ጨዋታ በአዳማ ይቀጥላል

ቀን:

  • ቤትኪንግ ኢትዮጵያን ለቆ መውጣቱን አክሲዮን ማኅበሩ አስታውቋል

በአይቮሪኮስት አስተናጋጅነት ለሚከናወነው የ2023 የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለሚያደርገው ተሳትፎ ተቋርጦ የነበረው የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር፣ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እንደሚቀጥል ተገልጿል፡፡

የ2015 ዓ.ም. ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 17ኛ እስከ 27ኛ ሳምንታት ያሉ ጨዋታዎች በአዳማ ከተማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲና በሐዋሳ ከተማ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየሞች እንደሚከናወኑ አክሲዮን ማኅበሩ አስታውቋል፡፡

ከመጋቢት 23 ቀን እስከ ግንቦት 27 ቀን 2015 ዓ.ም. የሚከናወኑ የሊጉ የጨዋታ መርሐ ግብሮችም ይፋ ሆነዋል፡፡ በዚህም መሠረት ቅዳሜ መጋቢት 22 ቀን 17ኛ ሳምንት መቻል ከአዳማ እንዲሁም ሲዳማ ቡና ከሐዲያ ሆሳዕና በአዳማ በሚያደርጉት ጨዋታ ይጀምራል፡፡

በአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ ላይ የተሳተፉት የብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች ወደ ኢትዮጵያ በገቡ ከአምስት ቀናት በኋላ ወደ ክለባቸው ተመልሰው መደበኛ ውድድር ላይ ይመለሳሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የስም ስያሜ የወሰደው ‹‹ቤትኪንግ›› በአስተዳደራዊ ችግር ምክንያት ከኢትዮጵያ መውጣቱን የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር አስታውቋል፡፡

ተቋሙ ከአክሲዮን ማኅበሩ ጋር የውል ስምምነት የሌለው እንደሆነና የስም ስያሜውን የገዛው ‹‹መልቲ ቾዝ አፍሪካ›› በመሆኑ፣ ከአገር መልቀቁ ከአክሲዮን ማኅበሩ ጋር የሚያገናኘው እንዳልሆነ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ክፍሌ ሰይፉ ለሪፖርተር አብራርተዋል፡፡

እንደ ጽሕፈት ቤት ኃላፊው አስተያየት ከሆነ የሊጉ ውድድር ‹‹ቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ›› የሚል ስያሜን ይዞ እንደሚቀጥል የጠቀሱ ሲሆን፣ አዲስ ስያሜም ካለ ውድድሩን ለማስተላለፍ መብት ያለው ዲኤስቲቪ ብቻ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የቤት ባለንብረቶች የሚከፍሉትን ዓመታዊ የንብረት ታክስ የሚተምን ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ

በአዋጁ መሥፈርት መሠረት የክልልና የከተማ አስተዳደሮች የንብረት ታክስ መጠን...

እንደ ንብረት ታክስ ያሉ ወጪን የሚያስከትሉ አዋጆች ከማኅበረሰብ ጋር ምክክርን ይሻሉ!

የመንግሥትን ገቢ በማሳደግ ረገድ አስተዋጽኦ እንዳላቸው የሚታመኑት የተጨማሪ እሴት...

ለዓለምም ለኢትዮጵያም ሰላም እንታገል

በበቀለ ሹሜ ያለፉት ሁለት የዓለም ጦርነቶች በአያሌው የኃያል ነን ባይ...