በአዲስ አበባ ከተማ በወንዞች ዳርቻ ጎጆዋቸውን ቀልሰው የሚኖሩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ሥጋት ላይ የሚወድቁት፣ የበልግና የክረምት ወቅቶች ሲመጡ ነው፡፡ የፊተኛውም ሆነ የኋላኛው ዝናብ የሚያስከትለው ጎርፍም ሆነ ደራሽ ውኃ የሰዎች ሕይወትንም ቀጥፏል፣ ጉዳትም አድርሷል፡፡ ብዙ ቤቶችንም አፍርሷል፡፡ ጠራርጎ ወስዷል፡፡ ፎቶዎቹ በአዲስ አበባ ከተማ በውኃ ሙላት የደረሱትን ጥፋቶች በከፊል ያሳያሉ፡፡
ፎቶ መስፍን ሰሎሞን