Saturday, May 18, 2024
- Advertisment -
- Advertisment -

[የምክር ቤቱ አባል ላቀረቡት ጥያቄ በተሰጣቸው ምላሽ አቤቱታቸውን ለክቡር ሚኒስትሩ እያቀረቡ ነው]

 • ክቡር ሚኒስትር እየሆነ ያለው ነገር ትክክል ነው?
 • ምነው?
 • ምክር ቤቱም ሆነ አባላቱ የተከበሩ ተብለው የሚጠሩት በምክንያት አይደለም እንዴ?
 • ትክክል ነው። ምክንያቱም፣ ምክር ቤቱ ትልቁ የሥልጣን አካል ነው፣ አባላቱም የሕዝብ ተወካዮች በመሆናቸው የተከበሩ ተብለው ነው የሚጠሩት።
 • ታዲያ ዝም ማለት ተገቢ ነው፣ መገሰጽ የለብንም?
 • ምኑን?
 • የተከበረው ምክር ቤት አባል ያቀረበውን ጥያቄ ‹‹ጥሩ ቀልድ ነው›› ሲሉ ዝም ማለት ተገቢ ነው?
 • እርስዎም እኮ በማይመጣው ነው የመጡት።
 • እንዴት?
 • ሥልጣን ይልቀቁ ነዋ ያሉት?
 • እንደዚያ ከሆነ ምክር ቤቱ አንድ ቋሚ ኮሚቴ ሊያቋቁምልን ይገባል።
 • የምን ቋሚ ኮሚቴ?
 • የቀልድ ጉዳዮች!

[ክቡር ሚኒስትሩ ከተቋሙ ሠራተኞች ማኅበር ጋር ስለ የመደመር ትውልድ መጽሐፍ ሽያጭ እየተወያዩ ነው]

 • ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር?
 • ሰላም፡፡
 • በአስቸኳይ እንደፈለጉኝ መልዕክት ደርሶኝ ነው የመጣሁት።
 • አዎ። ይህንን ደብዳቤ እየውና በጠየቁት መሠረት ይፈጸምላቸው።
 • ጉዳዩ ምንድነው?
 • ከኦሮሚያ ክልል የመጣ ደብዳቤ ነው። የተቋማችንን ትብብር ይፈልጋሉ።
 • የምን ትብብር ነው የጠየቁት?
 • የመደመር ትውልድ መጽሐፍን በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱና በተጠሪ ተቋማት ለሚገኙ ሠራተኞች በመሸጥ ገቢውን እንድናስገባላቸው ነው የጠየቁት።
 • ምን…?
 • የመደመር ትውልድ መጽሐፍን ለተቋማችን ሠራተኞች እንድንሸጥላቸው ነው የጠየቁት። ከደብዳቤው ጋር አያይዘውም ሁለት ሺሕ መጽሐፍቶችን ልከውልናል።
 • ክቡር ሚኒስትር ማለት የምችለው አንድ ነገር ብቻ ነው።
 • ምን?
 • አድርሰናል!
 • እንዴት? ምን ማለትህ ነው?
 • ተመሳሳይ የትብብር ጥያቄ ሰሞኑን ቀርቦልን አስተናግደናል።
 • ማነው የጠየቀው?
 • የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር።
 • ይህንኑ መጽሐፍ እንድንሸጥ ነው የጠየቁት?
 • አዎ። እነሱም ሁለት ሺሕ መጽሐፍ ነበር የላኩት።
 • እና ምን ምላሽ ሰጣችኋቸው?
 • በዋናው መሥሪያ ቤትና በተጠሪ ተቋማት ያሉ ሠራተኞችን አስቸግረን ከሞላ ጎደል ያቀረቡት መጽሐፍ ተሽጦላቸዋል።
 • በፌዴራል ተቋማት እንዲሸጡ ማን ፈቀደላቸው?
 • እንዴት?
 • መሸጥ የነበረባቸው በተከማ አስተዳደሩ ተቋማት ሥር ለሚገኙ ሠራተኞች እንጂ በፌዴራል ተቋማት ውስጥ ሽጡ አልተባሉማ፡፡
 • ኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥትም ወደ እኛ ተቋም መላክ አልነበረበትም።
 • እንዴት?
 • መጽሐፉን በራሱ ክልል ውስጥ ሸጦ ገቢውን ለተባለው ፕሮጀክት እንዲያውል ነዋ የታዘዘው።
 • አዲስ አበባ የክልሉ መንግሥት መቀመጫ መሆኗን እያስተዋልን እንጂ?
 • መቀመጫ መሆኗንማ አውቃለሁ።
 • ታዲያ ምንድነው የምትለው?
 • መቀመጫ ብቻ ነዋ ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • የመጽሐፍ ሽያጭን አስታከህ የሕገ መንግሥት ጥያቄ እያነሳህ ነው?
 • የሕገ መንግሥት ጥያቄ?
 • አዎ። ዳርዳር እያልክ ያለኸው ምን ልታነሳ እንደሆነ ያስታውቃል።
 • ኧረ እኔ ዳርዳር አላልኩም፣ የማነሳው ጥያቄም የለኝም።
 • አዲስ አበባ መቀመጫ ብቻ ነች አላልክም።
 • እሱንማ ብያለሁ።
 • ታዲያ ይኼ ምን ማለት ነው?
 • ምን ማለት ነው?
 • አዲስ አበባ የኦሮሚያ አይደለችም እያልክ ነዋ!
 • ክቡር ሚኒስትር እኔ እንደዚያ አልወጣኝም፣ አላልኩም!
 • መቀመጫ ብቻ ነች ማለት ምን ማለት ነው ታዲያ?
 • ክቡር ሚኒስትር የተፈለገው የመደመር ትውልድ መጽሐፍን መሸጥ አይደል?
 • የጠየቁት እሱን ነው!
 • ስለዚህ በሐሳብ መለያየት ያለብን አይመስለኝም። በዚያ ላይ…
 • እ… በዚያ ላይ ምን?
 • የመጽሐፉ ይዘትም ተደመሩ ነው የሚለው።
 • ስለዚህ?
 • መከራከራችን ትክክል አይደለም፣ ይጋጫል።
 • ከምንድነው የሚጋጨው?
 • ከመጽሐፉ መንፈስ ጋር ይጋጫል። አብሮ አይሄድም።
 • ስለዚህ መጽሐፉ እንዲሸጥ ታደርጋለህ።
 • ያው ሠራተኛው አንድን መጽሐፍ ለሁለተኛ ጊዜ ግዛ ብንለው የሚሰጠው ምላሽ ይታወቃል።
 • ምን ሊል ይችላል?
 • አንብቤ ስጨርስ ፓስታ ይሆናል እንዴ ብሎ ማሾፉ አይቀርም።
 • ስለዚህ?
 • እኔ ሌላ መፍትሔ እፈልጋለሁ።
 • ምን ዓይነት መፍትሔ?
 • ከድርጅቱ ወጪ ሆኖ መጽሐፉን በሠራተኞች ስም እንገዛለን።
 • መጽሐፍ ለመግዛት የተፈቀደልን በጀት የለማ፣ ኦዲት ስንደረግ ምን ልትል ነው?
 • ወጪውን ለመጽሐፍ ግዢ የዋለ አንለውም።
 • እና ምን ልትለው ነው?
 • ለመደመር ብለን እንመዘግበዋለን።
 • ኦዲተሩ ቢጠይቅስ?
 • ወጪው በመደመር ስም ተይዞ?
 • እ…?
 • አይጠይቅም!
 • እንደዚያ ከሆነማ ሃያ ሺሕ አድርገው።
 • ምኑን?
 • የመጽሐፉን ብዛት!

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

ለፖለቲካዊም ይሁን ኢኮኖሚያዊ ትግል መቀዛቀዝ ምክንያቱ የጠራ ርዕዮተ ዓለም አለመኖር ወይስ የምሁራን መዳከም?

መሬት ላራሹ ብለው በተነሱ ተማሪዎችና ምሁራን ድምፅ የተቀጣጠለው የመጀመሪያው...

በአዲስ አበባ ለሚገኙ አምራች ኢንዱስትሪዎች የሚሰጡ ድጋፎችንና መሥፈርቶችን ያካተተ አዲስ መመሪያ ወጣ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማው ወስጥ ለሚገኙ አምራች ኢንዱስትሪዎች...

የዘንድሮ የወጭ ንግድ ገቢ ከዕቅዱም ሆነ ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር ዝቅተኛ መሆኑ ተገለጸ

የኢትዮጵያ የወጭ ንግድ ገቢ በተያዘው የበጀት ዓመትም የታቀደውን ያህል...

ሕይወትም እንዲህ ናት!

ከዊንጌት ወደ አየር ጤና ነው የዛሬው የጉዞ መስመራችን፡፡ አንዳንዴ...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[ክቡር ሚኒስትሩ የቢሮ ሥራቸውን አጠናቀው ከውጭ አገር የመጣ ወንድማቸውን ለመጠየቅ ያረፈበት ገስት ሀውስ ሲደርሱ ወንድማቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ፕሮግራም በመገረም እየተከታተለ አገኙት]

ውይ መጣህ እንዴ? እስኪ አረፍ በል፡፡ ምንድነው እንዲህ ያስደነቀህ? ተደንቄ ሳይሆን ግራ ግብት ብሎኝ ነው። ምኑ ነው ግራ ያጋባህ? የድልድይ ማስመረቅና የድልድይ ማፍረስ ነገር ነዋ። አልገባኝም? አለቃችሁ ድልድይ ሲያስመርቁ የተናገሩትን...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከዘመዶቻቸውና ቤተሰቦቻቸው ጋር ሆነው በዓሉን በመኖሪያ ቤታቸው እያከበሩ ነው። ባለቤታቸውም ለበዓሉ የተዘጋጀውን ዳቦ ባርከው እንዲቆርሱ ለሚኒስትሩ እያቀረቡ ነው]

በል ዳቦውን ባርክና ቁረስልንና በዓሉን እናክብር? ጥሩ ወዲህ አምጪው... አዎ! በል መርቅ... ከዓመት ዓመት ያድርሰን... ኧረ በሥርዓት መርቅ ተው? ከዓመት ዓመት ያድርሰን አልኩኝ እኮ ...አልሰማሽም? ከዓመት ዓመት መድረሱ ብቻ ምን...

[ክቡር ሚኒስትር መንግሥት ይፋ ያደረገውን ንቅናቄ አመራሮችና ቤተሰቦቻቸው በግንባር ቀደምትነት እንዲቀላቀሉ መታዘዙን ለባለቤታቸው እያጫወቱ በዚያውም ወደተከፈተው የባንክ ሒሳብ ገንዘብ እንዲያስተላልፉ እያግባቧቸው ነው]

በይ እስኪ ሞባይልሽን አውጪና ወደዚህ የባንክ ሒሳብ አንድ ሺሕ ብር አስተላልፊ? ለምን? መንግሥት ያስጀመረውን ንቅናቄ አመራሩ ከነቤተሰቡ ግንባር ቀደም ሆኖ እንዲደግፍ ታዟል። የምን ንቅናቄ ነው መንግሥት ያስጀመረው? ‹‹ፅዱ...