Friday, June 2, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየአማራና ደቡብ ክልሎች ለሠራተኛ ደመወዝ መክፈል መቸገራቸውን የፓርላማ አባላት ተናገሩ

የአማራና ደቡብ ክልሎች ለሠራተኛ ደመወዝ መክፈል መቸገራቸውን የፓርላማ አባላት ተናገሩ

ቀን:

በአማራና በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልሎች የሚገኙ የመንግሥት ተቋማት በበጀት እጥረት ምክንያት ለሠራተኞቻቸው ደመወዝ ለመክፈል መቸገራቸውን፣ የክልሎቹ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት አስታወቁ፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በየካቲት ወር 2015 ዓ.ም.፣ ለአንድ ወር ወደ መረጣቸው ሕዝብ በመሄድ ስላደረጉት ውይይትና ምክክር በተመለከተ፣ ከመንግሥት አስፈጻሚና ሕግ ተርጓሚ አካላት ጋር ሰኞ መጋቢት 18 ቀን 2015 ዓ.ም. ውይይት አድርገዋል፡፡

በመድረኩ ከደቡብ ክልል የፓርላማ አባላት በሕዝብ ውይይት ወቅት የተነሱ ጥያቄዎቹን ለአስፈጻሚ አካላት ያቀረቡት አቶ መለስ መና የተባሉ የምክር ቤት አባል፣ ‹‹የደቡብ ክልል የበጀት ችግር ራስ ምታት ሆኖብናል፤›› ብለዋል፡፡

ለመንግሥት ሠራተኞች የሦስትና የአራት ወራት ደመወዝ ያልከፈሉ ተቋማት መኖራቸውን የገለጹት አቶ መለስ፣ በዚህም ምክንያት የመንግሥት አጠቃላይ አገልግሎት እየወደቀ ነው ብለዋል፡፡ በመሆኑም መንግሥት ተገቢውን ጥናት አድርጎ መልስ መስጠት ካልተቻለ፣ በዚህ የኑሮ ውድነት የመንግሥት ሠራተኛው ልጆቹን ትምህርት ቤት መላክ የማይችልበት ደረጃ ላይ ይደርሳል ብለዋል፡፡

አቶ መለስ ችግሩ በሁሉም የደቡብ ክልል አካባቢዎች የተከሰተ መሆኑን፣ ችግሩ ሊከሰት የቻለበት ዋነኛውና ትልቁ ምክንያት ክልሉ እስከ አሥር ዓመት የሚደርስ የማዳበሪያ ዕዳ ስለነበረበት ገንዘቡ ደመወዝ ከመከፈሉ ቀድሞ ዕዳ እየተከፈለበት በመሆኑ ነው ብለዋል፡፡ ለዚህ ችግር በተለየ ሁኔታ መፍትሔ ያሻዋል ያሉት አቶ መለስ፣ ችግሩ በዚሁ ከቀጠለ ግን የተቋማት አገልግሎቶች ሊቆሙ እንደሚችሉ ጠቁመዋል፡፡

በተመሳሳይ የአማራ ክልል የፓርላማ አባላትን ወክለው በውይይቱ ወቅት ጥያቄ ያቀረቡት ወ/ሮ ታለፍ ይታወቅ የተባሉ የምክር ቤት አባል፣ በአማራ ክልል የገጠመው የበጀት እጥረት ደመወዝ መክፈል አለመቻል ብቻ ሳይሆን ተቋማዊ ቁመና ይዘው ለመቀጠል የማይችሉበት ደረጃ ላይ ደርሰዋል ብለዋል፡፡

ወ/ሮ ታለፍ እንዳሉት፣ በአማራ ክልል ችግሩ በተለየ ሁኔታ የተከሰተባቸው አካባቢዎች  በሰሜን ወሎ ዞን፣ ደቡብ ወሎ ዞን ከለላ፣ ወረኢሉ፣ አልቡኮ፣ ኩታበር ወረዳዎች፣ በምሥራቅ ጎጃም ዞን እነማይ፣ አነዳድ፣ ደጀን፣ ጎንቻ፣ ሲሶ፣ ስናን፣ ብቸና ከተማዎች፣ በማዕከላዊ ጎንደር በበሁሉም ወረዳዎች፣ በአዊ ዞን ጃዊ ወረዳ፣ በምዕራብ ጎጃም ዞን ደንበጫ  ከተማ፣ በሰሜን ሸዋ ዞን ጣርማ በርና አንጎላላ ወረዳ ይገኙበታል፡፡

በአማራ ከልል የሚታየው ችግር የተለያየ ዓይነት ገጽታ እንዳለው የገለጹት ወ/ሮ ታለፍ፣ በመንግሥት የተመደበው የሥራ ማስኬጃ በጀት በዋጋ ንረት ሳቢያ ማብቃቃት እንዳልተቻለና አንዳንድ ወረዳዎች እንደ ወረዳ ለመቀጠል የማይችሉበት ደረጃ ላይ መድረሳቸውን ተናግረዋል፡፡

ከዚሁ የበጀት እጥረት ባለፈ በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት የደረሰውን ውድመት መልሶ ለማቋቋም በሚል መንግሥት ከ20 ቢሊዮን ብር መድቤያለሁ ቢልም፣ ድጎማው እንደ ክልል ሲፈተሽ የተሠሩ ሥራዎች እነዚህ ናቸው የሚል በተጨባጭ የተገኘ ገንዘብ እንደሌለ የገለጹት የፓርላማ አባሏ፣ ይህም በመሠረታዊነት የሕዝብ ጥያቄ ተነስቶበታል ብለዋል፡፡ በሌላ በኩል ይገነባሉ ተብለው በዕቅዱ የነበሩ የመንገድ ፕሮጀክቶች ሕዝቡ በምን ምክንያት እንደተሰረዙ ሳያውቅ፣ ተሰርዞብናል በሚሉ በርካታ አካባቢዎች ጥያቄ መቅረቡን አስረድተዋል፡፡

የምክር ቤት አባላቱ በየካቲት 2015 ዓ.ም. ከመረጣቸው ሕዝብ ጋር ውይይት ለማድረግ በነበረው ዕቅድ በ327 የውክልና ቦታዎች ውይይት ሲደረግ፣ በ127 ያህሉ በተለያዩ ምክንያቶች ውይይት ማድረግ እንዳልቻሉ በመንግሥት ተጠሪ ሚኒስትሯ ወ/ሮ መሠረት ኃይሌ ተገልጿል፡፡ የተነሳ ሲሆን ውይይት ከተደረገባቸው የውክልና አካባቢዎች መካከል 69 ያህሉ በፀጥታ ምክንያት መሆኑን አክለዋል፡፡

በፀጥታ ምክንያት ውይይት ከተደረገባቸው የውክልና ቦታዎች መካከል ኦሮሚያ ክልል ይገኝበታል ተብሏል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በአዲስ አበባ በድምቀት ተከበረ

የአዛርባጃን ኤምባሲ  የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በትላንትናው ዕለት አከበረ። ሰኞ...

የመንግሥትና የሃይማኖት ልዩነት መርህ በኢትዮጵያ

እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገሮች የሃይማኖት ተቋማት አዎንታዊ ሚና የጎላ...

ሐበሻ ቢራ ባለፈው በጀት ዓመት 310 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ

የአንድ አክሲዮን ሽያጭ ዋጋ 2,900 ብር እንዲሆን ተወስኗል የሐበሻ ቢራ...