_የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የነበሩት የቡሌ ሆራ ፕሬዚደንት ያለመከሰስ መብት ተነሳ
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስ የግዢ መመሪያን በመተላለፍ የተለያዩ ግዢዎችን በመፈጸም የሙስና ወንጀል ተጠርጥረዋል የተባሉት የቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚደንት ጫላ ዋታ(ዶ/ር)ን ያለመከሰስ መብት ያነሳው፣ በፍትሕ ሚኒስቴር ጥያቄ መሆኑ ታውቋል።
ምክር ቤቱ ከለውጥ በፊት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድቤት ፕሬዚደንት የነበሩትንና ባሁኑ ጊዜ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ የነበሩትን ወ/ሮ ሌሊሴ ደሳለኝን የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት እንዲሁም ወ/ሮ ዛህራ ዑመርን ምክትል ፕሬዚደንት አድርጎ ሾሟል።