- ከክርስቶስ ልደት 620 ዓመት በፊት ድራኮ የተባለው እጅግ በጣም ታዋቂ የአቴና ሕግ አርቃቂ በኤጂንያ ትያትር ቤት ውስጥ መድረክ ላይ ድንቅ ንግግር ካደረገ በኋላ በሺሕ የሚቆጠሩ አድናቂዎቹ ከሀር የተሠራ የካባ ስጦታ አጎረፉለት፡፡ ታዲያ አድናቂዎቹ እየተረባረቡ ካባውን እላዩ ላይ ጣል ጣል እያደረጉ ሲያከማቹበት፣ ድራኮ ሳይታሰብ በጨርቁ ክምር ታፍኖ ሞተ፡፡
- ከክርስቶስ ልደት 210 ዓመት በፊት ቂን ሺ ሃውኛ የተባለ የቻይና ንጉሥ አለመጠን ሜርኩሪ የተባለውን ፈሳሽ መሰል ማዕድን ስለወሰዱ ሕይወታቸው አልፏል፡፡ ንጉሡ ሜርኩሪውን ይወስዱ የነበረው ‹‹ሜርኩሪ ዘላለማዊ ሕይወትን ይሰጣል፤ ሜርኩሪ ከሞትም ያስቀራል›› ተብሎ ስለተነገራቸውና ዘልዓለም ለመኖር ደግሞ ከፍተኛ ፍላጎት ስለነበራቸው ነበር፡፡ ታዲያ ምን ያደርጋል በገዛ እጃቸው ‹‹ሩቅ አሳቢ ቅርብ አዳሪ›› ሆነው አረፉት፡፡
- ከክርስቶስ ልደት በፊት 210 ዓመት ላይ አንድ ክሪሲፐስ የተባለ ግሪካዊ ፈላስፋ የገዛ አህያውን ብዙ የወይን ጠጀ ከጋተው በኋላ አህያው ሰክሮ የበሰለ ዛፍ ላይ ለመውጣት ሲታገል በማየቱ፣ በተፈጠረው አስቂኝ ትይንት ለረጅም ደቂቃዎች ያለማቋረጥ ሲስቅ ትን ብሎት ሞተ፡፡ ጓደኞቹ የነበሩት ሌሎች ፈላስፎች ኮሜዲ እፈጥራለሁ ብሎ በራሱ ላይ ልቡ ፍርስ እስኪል ትራዴጂ ላመጣው ፈላስፋ መታሰቢያ እንዲሆን በማለት ከእንግዲህ ወዲያ በሞኝ ፍጥረት ላይ… በሰውም ይሁን በእንስሳ ላይ አንስቅም ሲሉ ቃል ገቡ፡፡
- ‹‹ማኅደር ቁጥር ፫›› (2005)
- Advertisement -
- Advertisement -