Saturday, September 23, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየእግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሠልጣኝ የመልቀቂያ ደብዳቤ ማስገባታቸው ተሰማ

የእግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሠልጣኝ የመልቀቂያ ደብዳቤ ማስገባታቸው ተሰማ

ቀን:

  • ብሔራዊ ቡድኑ ወደ አሜሪካ እንደሚሄድ ተጠቁሟል

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሠልጣኝ ውበቱ አባተ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የመልቀቂያ ደብዳቤ ማስገባታቸው ተሰማ፡፡

ከሳምንታት በፊት የአይቮሪኮስት 2023 አፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በሞሮኮ የጊኒ አቻውን የገጠመው የዋሊያው ስብስብ፣ በምድብ ጨዋታ ሽንፈት ማስተናገዱን ተከትሎ ዋና አሠልጣኙ ከኃላፊነታቸው ለመልቀቅ መወሰናቸው ተነግሯል፡፡

አሠልጣኝ ውበቱ የመልቀቂያ ደብዳቤ ማስገባታቸውን ሪፖርተር ከፌዴሬሽኑ ምንጮች መረዳት ችሏል፡፡ በዚህም መሠረት የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው የመልቀቂያ ደብዳቤውን መቀበሉን ምንጮቹ ያረጋገጡ ሲሆን፣ በቅርቡ ውሳኔውን እንደሚያሳውቅ ተጠቁሟል፡፡

በዚህም መሠረት የብሔራዊ ቡድኑ ቀሪ የማጣሪያ ጨዋታዎች አዲስ በሚቀጠረው አሠልጣኝ እንደሚመሩ ተረጋግጧል፡፡

ዋሊያዎቹ በዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከስድስት ጨዋታዎች አራቱን አከናውነው ሁለት ቀሪ ጨዋታዎች ከማላዊና ከግብፅ ብሔራዊ ቡድኖች ጋር በዚህ ዓመት መገባደጃ ሰኔና መስከረም 2016 ዓ.ም. ወር ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

ብሔራዊ ቡድኑ ሦስተኛና አራተኛ ጨዋታ ላይ ያሳየው አቋም ከምድቡ ደካማ በመሆኑ አሠልጣኝ ውበቱ ላይ ከፍተኛ ትችት እንዲሰነዘርባቸው ገፊ ምክንያት የሆነ ሲሆን፣ ከኃላፊነታቸው ይለቃሉ ወይስ አይለቁም የሚለው ጥያቄ ተበራክቶ ነበር፡፡  

ከዚህ ጋር ተያይዞም አሠልጣኙ የመልቀቅና ያለመልቀቅ ውሳኔ በእሳቸው ብቻ የሚፀና አለመሆኑንና ከብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ጋር ተወያይተው የሚወስኑት ጉዳይ መሆኑን በጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ማብራራታቸው ይታወሳል፡፡ ሆኖም የአሠልጣኙ ከኃላፊነታቸው መልቀቅና አለመልቀቅ መነጋገሪያ ሆኖ የከረመ ሲሆን፣ አሁን እርግጥ መሆኑን ከፌዴሬሽን ምንጮቹ በተገኘው መረጃ ተረጋግጧል፡፡

ዋሊያዎቹን ለማሠልጠን ከሁለት ዓመታት በፊት ኃላፊነት የተረከቡት አሠልጣኝ ውበቱ አባተ፣ በአጠቃላይ 35 ጨዋታዎችን ያደረጉ ሲሆን፣ አሥሩ የአቋም መለኪያ ጨዋታዎች ናቸው፡፡

ከእነዚህም መካከል 25 የውድድር መርሐ ግብር ጨዋታዎች ሲሆኑ፣ ዋሊያዎቹ ማሸነፍ የቻሉት ስድስት ጨዋታዎችን ብቻ ነው፡፡

በ2023 የአፍሪካ ዋንጫ ምድብ አራት ከግብፅ፣ ከጊኒና ከማላዊ ጋር በተደለደለው የዋሊያዎቹ ስብሰብ፣ በሦስት ነጥብና በግብ ተበልጦ በአራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡

በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወደ አሜሪካ እንደሚያቀና ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ በይፋዊ ማኅበራዊ ድረ ገጹ ላይ አስታውቋል፡፡

የዋሊያዎቹ ስብስብ ሰኔ መጨረሻ ላይ ወደ አሜሪካ የሚያቀና ሲሆን፣ ሐምሌ 1 እና ሐምሌ 8 ቀን 2015 ዓ.ም. የአቋም መለኪያ ጨዋታ እንደሚያደርግ ተገልጿል፡፡

የብሔራዊ ቡድኑ የጉዞ ዓላማ በአሜሪካ ከሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር ግንኙነት ለማጠናከር ግብ ያደረገ መሆኑ የተጠቀሰ ሲሆን፣ የገቢ ምንጭ አማራጩን ለማስፋት ማቀዱ ተጠቁሟል፡፡

ዋሊያዎቹ በአሜሪካ ቆይታቸው የሜጀር ሊግ ሶከር (Major League Succor) ላይ እየተሳተፈ የሚገኘውን ዲሲ ዩናይትድ (DC United)፣ የካሪቢያን ቡድን (Caribbean Team) በወዳጅነት የሚገጥም ይሆናል፡፡

ብሔራዊ ቡድኑ በሜጀር ሊግ ሶከር ላይ የሚሳተፍ ሌላ ሦስተኛ ክለብ እንደሚገጥም የተገለጸ ሲሆን እስካሁን አለመረጋገጡ ተጠቁሟል፡፡

ቡድኑ በአሜሪካ የሚያደርገው ጉዞ ሙሉ ወጪ የፊፋ ዕውቅና ባለው ‹‹ሲጂኤ›› በተባለ ድርጅት ሙሉ ወጪ እንደሚሸፈን ተጠቅሷል፡፡

ዋሊያዎቹ በአሜሪካ ቆይታቸው የወዳጅነት ጨዋታ ከማድረጋቸው በዘለለ፣ የገቢ ምንጭ የማስፋት ዕድል እንዳለው የተጠቀሰ ሲሆን፣ የማልያ ሽያጭ እንደሚያደርግ ይጠበቃል፡፡

ከዚያም ባሻገር ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ በአሜሪካ ከሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር ተቀራርቦ መሥራት የሚቻልበትና የገቢ ምንጭ የሚያሳድግበትን መንገድ ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻሎችን ማሳየት የተሳነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን፣ ባለፉት ሁለት ዓመታት በአፍሪካ ዋንጫና የአፍሪካ አገሮች ዋንጫ (ቻን) ላይ መካፈል ቢቻልም ወጥ የሆነ አቋም ማሳየት አልቻለም፡፡

በዚህም በቅርቡ የሚሾመው የብሔራዊ ቡድኑ ዋና አሠልጣኝ ዋሊያዎቹ የገቡበትን ምስቅልቅል ችግር ይፈታል ወይ? ለሚለው ጥያቄ ምላሽ በሁሉም ሰው ዘንድ የሚጠበቅ ነው፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ኮሚሽን ሪፖርት ምን ይዟል?

ለአሜሪካ ድምፅ አማርኛ ዝግጅት የስልክ አስተያየት የሰጡ አንድ የደንበጫ...

መንግሥት በአማራ ክልል ለወደሙ የአበባ እርሻዎች ድጋፍ እንዲያደርግ ተጠየቀ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአማራ ክልል የተፈጠረው ግጭትና አለመረጋጋት በቢዝነስ...

አምናና ዘንድሮ!

እነሆ መስከረም ጠብቶ በአዲስ መንፈስ ተሞልተን መንገድ ጀምረናል። ‹‹አዲስ...