Wednesday, June 12, 2024

[ክቡር ሚኒስትሩ ከተቃዋሚ ፓርቲው ትይዩ ሚኒስትር ጋር በወቅታዊ ጉዳይ ላይ እየተወያዩ ነው]

 • ክቡር ሚኒስትር የክልል ልዩ ኃይሎችን በተመለከተ መንግሥት ያሳለፈው ውሳኔ ላይ ፓርቲያችን ማጣራትና ማረጋገጥ የሚፈልጋቸው ጉዳዮች በመኖራቸው ነው እርስዎን ለማግኘት የጠየቅሁት።
 • ሌሎች ፓርቲዎችም የእናንተን መንገድ ቢከተሉ ጥሩ ነበር።
 • እንዴት?
 • ምክንያቱም አበክረው ሲጠይቁት ለነበረው ጥያቄ መንግሥት ምላሽ ሲሰጥ ጾመኞች ነን አሉ።
 • ክቡር ሚኒስትር እኛም ለመለየት ተቸግረናል።
 • ምኑን?
 • የትኛው የፍስክ፣ የትኛው ደግሞ የጾም እንደሆነ።
 • ለምን?
 • ምክንያቱም አንዳንድ አመራሮች መንግሥት ልዩ ኃይልን የማፍረስም ሆነ የመበተን ፍላጎት የለውም ይላሉ።
 • እውነት ነው።
 • ሌሎች አመራሮች ደግሞ በመንግሥት ውሳኔ መሠረት የክልል ልዩ ኃይሎች ወደ መከላከያ እንደሚቀላቀሉ ይገልጻሉ።
 • ልክ ነው!
 • የቱ ነው ልክ?
 • ሁለቱም፡፡
 • የክልል ልዩ ኃይል አይፈርስም?
 • እኛ ልዩ ኃይልን የማፍረስ ዕቅድ ጨርሶ የለንም። መልሶ የማደራጀት ውሳኔ ነው ያሳለፍነው፡፡
 • ስለዚህ ወደ መከላከያ ይቀላቀላል የሚባለው ትክልል አይደለም?
 • ትክልል ነው እንጂ! ይቀላቀላሉ።
 • ካልፈረሱ እንዴት ሆነው ወደ መከላከያ የሚቀላቀሉት?
 • ምን ችግር አለው? ቀላል እኮ ነው።
 • በምን ዓይነት አደረጃጀት ሊቀላቀሉ ይችላሉ?
 • ማለት?
 • ከተቀላቀሉ በኋላ በመከላከያ ሠራዊት የአማራ ልዩ ኃይል ወይም የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ነው አደረጃጀታቸው?
 • እርስዎም እንደ ሌሎቹ ተቃዋሚዎች ከሥጋው እጾማለሁ ሊሉ ነው?
 • አይደለም፣ ተሳስተዋል ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • እርስዎ ነዎት የተሳሳቱት፡፡
 • እንዴት?
 • ምክንያቱም የጠቀሱት አደረጃጀት በሙከራ ጭምር የሚያስጠይቅ ነው።
 • የምን ሙከራ?
 • ሕገ መንግሥቱን በኃይል የመናድ፡፡
 • ክቡር ሚኒስትር እንዴት እንደዚህ ይላሉ?
 • በመከላከያ ሠራዊት ውስጥ የሌለ የክልል ልዩ ኃይል አደረጃጀትን ማንሳት ሕግ መንግሥቱን የመናድ ዕሳቤ ቅጥያ ነው!
 • ክቡር ሚኒስትር ከእርስዎ ማብራሪያ ተነስቼ ያልኩት ነው?
 • እኔ እንደዚያ ወጣኝ?
 • መንግሥት የክልል ልዩ ኃይልን የማፍረስ ዕቅድ የለውም ነገር ግን ወደ መከላከያና ሌሎች የፌዴራል የፀጥታ ተቋማት ይቀላቀላሉ አላሉም?
 • ብያለሁ፡፡
 • ታዲያ?
 • እስኪቀላቀሉ ድረስ ነዋ!
 • እንደዚያ ከሆነ ያድርጉልኝ?
 • ከምኑ?
 • ከሥጋውም ከመረቁ!

[የጊዜያዊ አስተዳደሩ መሪ ወደ ሚኒስትሩ ደውለው መንግሥት ሰሞኑን ባወጣው መግለጫ ላይ ማብራሪያ እየጠየቁ ነው]

 • ክብርት ሚኒስትር፣ ሰላም?
 • ሰላም ነኝ፣ ምን እግር ጣለዎት?
 • ምን ስልስ ጣለዎት ነው የሚባለው።
 • ኪኪኪኪ … እውነት ነው። እንዲህ ስንደዋወል ደስ ይላል። ምን ጉዳይ ገጠመዎት?
 • መቼም አንዳንዴ ግርታ አይጠፉም ወይም ያንን ስልት እኛ ላይም መጠቀም ጀምራችሁ ይሆናል።
 • የቱን ስልት?
 • ኮንፊውዝና ኮንቪንስን፡፡
 • እንዴት?
 • መንግሥት ሰሞኑን የሰጠው መግለጫ ግራ አጋብቶናል።
 • ለምን?
 • ክቡር ሚኒስትር በግልፅ እንደሚረዱት የመከላከያ ሠራዊት አካል ያልሆኑ የፀጥታ ኃይሎች ከትግራይ ክልል እንደሚወጡ በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ማስፈጸሚያ ተስማምተናል።
 • አዎ። ትክክል ነው።
 • በፕሪቶሪያው ስምምነት ላይ የሰላም ስምምነቱ ዓላማ ተብለው የተዘረዘሩት ነጥቦች አንዱም በቀጥታ ከዚህ ጋር እንደሚገናኝ የሚገነዘቡ ይመስለኛል።
 • ልክ ነው። እስኪ ያስታውሱኝ፣ የትኛው ነጥብ ነበር?
 • በጦርነቱ ምክንያት በትግራይ ክልል የተስተጓጎለውን ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት ወደነበረበት መመለስ አንደኛው የስምምነቱ ዓላማ ነው።
 • አዎ። አስታወስኩት። ትክክል ነው።
 • መንግሥት ሰሞኑን የሰጠው መግለጫ ግን ይህንን ያላገናዘበ ይመስላል። በእኛ ላይም ግራ መጋባትን ፈጥሯል።
 • የትኛው መግለጫ ነው?
 • የክልል ልዩ ኃይሎችን በተመለከተ የተሰጠው።
 • ይህ መግለጫ ደግሞ እናንተ ላይ እንዴት ግርታ ይፈጥራል?
 • ፈጥሯል!
 • እኮ እንዴት?
 • ምክንያቱም የክልል ልዩ ኃይሎችን በተመለከተ መንግሥት ያሳለፈው ውሳኔ ከፕሪቶሪያው ስምምነት ጋር አይገናኝም ይላል።
 • ልክ ነው ይላል።
 • እርስዎም ጉዳይ ላይ በሰጡት መግለጫ የመንግሥት ውሳኔ ከሰላም ስምምነቱ ጋር አይገናኝም ብለው ቃል በቃል ደግመውታል።
 • አይገናኝም ብቻ አይደለም ያልኩት፡፡
 • እ…?
 • ከሰላም ስምምነቱም አይጣረስም ብያለሁ!
 • እንደዚያ ማለትዎን አልሰማሁም።
 • እንደዚያ ነው ያልኩት።
 • ከሆነማ መግለጫውም እንደ እርስዎ ነው።
 • እንደ እርስዎ ማለት?
 • ሰላማዊ ነው።
 • ነገር ግን ስምምነቱን ለማስፈጸም ብለን የወሰነው አይደለም።
 • ለምንድነው?
 • የአገራዊ ዕቅዳችን አካል ስለሆነ ነው።
 • ቢሆንም …ክቡር ሚኒስትር ቢሆንም?
 • ቢሆንም ምን?
 • ሚዛናዊ ነው!

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት...

የመንግሥት የ2017 ዓ.ም በጀትና የሚነሱ ጥያቄዎች

የ2017 ዓመት የመንግሥት ረቂቅ በጀት ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ለሚኒስትሮች...

ከፖለቲካ አባልነትና ከባንክ ድርሻ ነፃ የሆኑ ቦርድ ዳይሬክተሮችን ያካተተው ብሔራዊ ባንክ ያዘጋጃቸው ረቂቅ አዋጅና መመርያዎች

የኢትዮጵያ የብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማትን የተመለከቱት ድንጋጌዎችንና የባንክ ማቋቋሚያ...

የልምድ ልውውጥ!

እነሆ መንገድ ከቦሌ ሜክሲኮ። አንዱ እኮ ነው፣ ‹‹እንደ ሰሞኑ...

የ‹‹ክብር ዶክትሬት›› ዲግሪ ጉዳይ

በንጉሥ ወዳጅነው ‹‹የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ግልጽ የሆነ መመርያ እስኪወጣ ድረስ...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት የሚታወጁ ሕዝባዊ ንቅናቄዎችን ማለቴ ነው። ምን ታወጀ? አንዴ ከዕዳ ወደ ምንዳ አላችሁ፡፡ እሺ? የእሱን ውጤት እየጠበቅን ሳለ ደግሞ... እ...? ኢትዮጵያ ታምርት...

[ክቡር ሚኒስትሩ ሰሞኑን በተጀመረው አገራዊ የምክክር መድረክ ላይ ስለተላለፉ መልዕክቶች በተመለከተ ከባለቤታቸው ጋር እያወጉ ነው] 

እኔ ምልህ? እ... አንቺ የምትይው? አለቃህ በምክክር መድረኩ ላይ ያስተላለፉትን መልዕክት አደመጥክ? አዎ፡፡ የሚገርም እኮ ነው አልተገረምክም? ምኑ ነው የሚያስገርመው? ለኢትዮጵያ የሚበጀውን ምከሩና አምጡ ብለው የምክክር መድረክ እንዲዘጋጅ ካደረጉ በኋላ...

[የክቡር ሚኒስትሩ ባለቤት የኬንያው ፕሬዚዳንት ያስተላለፉትን መልዕክት ተመልክተው ባለቤታቸውን በነገር ይዘዋቸዋል]

የኬንያው ፕሬዚዳንት ከሕዝባቸው ለቀረበባቸው ቅሬታ የሰጡትን ምላሽ ሰማህ? እንኳን ምላሻቸውን ቅሬታውንም አልሰማሁም። እንዴት? አልሰማሁማ? የምን ቅሬታ ቀርቦባቸው ነው? ሰሞኑን ወደ አሜሪካ ለመጓዝ ውድና ቅንጡ አውሮፕላን ተከራይተዋል የሚል ቅሬታ...