Tuesday, July 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜና‹‹ኢትዮጵያ ከአውሮፓ ኅብረት ምክር ቤት ጉባዔ በጎ ውሳኔዎችን ትጠብቃለች›› ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

‹‹ኢትዮጵያ ከአውሮፓ ኅብረት ምክር ቤት ጉባዔ በጎ ውሳኔዎችን ትጠብቃለች›› ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

ቀን:

በመጭው ግንቦት ወር መጀመሪያ ሳምንት በብራስልስ ከሚጀምረው የአውሮፓ ኅብረት ካውንስል ጉባዔ፣ ኢትዮጵያ በጎ የሚባሉ ውሳኔዎችን እንደምትጠብቅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ መለስ ዓለም (አምባሳደር) በሳምንታዊ መግለጫቸው እንዳሉት፣ የኢትዮጵያና የአውሮፓ ኅብረት ግንኙነት ረዥምና በጣም ጠንካራ የሚባል ነው ብለዋል፡፡

ባለፉት ሁለት ዓመታት ኢትዮጵያ ፈታኝ ጊዜ ውስጥ በነበረችበት ሁኔታ ሳይቀር የሁለቱ ግንኙነት ‹‹በጣም የሰመረ ነበር ተብሎ›› የሚገለጽ ስለመሆኑ ያብራሩት ቃል አቀባዩ፣ በወቅቱ ከአትዮጵያ ጋር የነበረው ችግር አውሮፓ ኅብረት ውስጥ ከነበሩ በጣት የሚቆጠሩ ግለሰቦች እንጂ ጉዳዩ ተቋሙን የሚወክል አልነበረም ብለዋል፡፡

‹‹ኢትዮጵያ ከአውሮፓ ኅብረት ጋር ያለው ግንኙነት እንዲሻሻል ብቻ ሳይሆን፣ የአውሮፓ ኅብረት ወንድሞቻችንን ይፈልጋሉ፣ ለዚህም በተናጠል ከየአገሪቱና በቡድን ከኅብረቱ ጋር ግንኙነት እናደርጋለን፤›› ያሉት መለስ (አምባሳደር) በመጪው ግንቦት 2015 በሚደረገው የአውሮፓ ኅብረት ምክር ቤት ጉባዔ ኢትዮጵያን በተመለከተ በጎ ውሳኔዎችን ያሳልፋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል፡፡

ከሰሞኑ በአዲስ አበባ ጉብኝት ያደረጉት የስሎቫኒያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ የጣሊያን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና ሌሎችንም ጨምሮ በኢትዮጵያ የሚያደርጉት ጉብኝት፣ ኢትዮጵያ ከኅብረቱ ጋር ያላት ግንኙነት እየተሻሻለ ስለመምጣቱና በዓለም አቀፍ ግንኙነት ውስጥ የማይተካ ሚና እየተጫወተች መሆኑን ማሳያ እንደሆነም ቃል አቀባዩ አስረድተዋል፡፡

በመሆኑም ‹‹ኢትዮጵያ ሌሎች አገሮች በምፍትፈልጋቸው ልክ እነሱም ይፈልጓታል›› ያሉት ቃል አቀባዩ ለሰብዓዊና ለበጎ አድራጎት የሚደረግ የዲፐሎማሲ ግንኙነት እንደሌለ ጠቅሰው፣ የዲፐሎማሲ ግንኙነት ማሣሪያው ብሔራዊ ጥቅም ነው ብለዋል፡፡

ስሎቫኒያ በግብርና፣ በውኃ ዲፕሎማሲ በአካባቢ ጥበቃና በንብ ማነብ ትልቅ ልምድ ስላላቸው፣ እነሱንም ጨምሮ በበርካታ ጉዳዮች በጋራ ለመሥራት እንደሚፈልጉና በተያዘው ሳምንት በኢትዮጵያ ያደረጉት ጉብኝት በአካባቢያዊና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ከኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጋር እንደተመካከከሩ ተናግረዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...

ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም በሌላት አገር ዘመናዊ ስታዲየም እየገነቡ ያሉ ክልሎች

አዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዘመናዊ ስታዲየም ለማስገንባት ከ500 ሚሊዮን...