Saturday, September 23, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትበአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የሚሳተፈው ብሔራዊ ቡድን ልምምዱን ጀመረ

በአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የሚሳተፈው ብሔራዊ ቡድን ልምምዱን ጀመረ

ቀን:

በዛምቢያ አስተናጋጅነት በሚሰናዳው የአፍሪካ ከ18 እና ከ20 በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና የሚካፈለው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን ዝግጅት መጀመሩን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታወቀ፡፡

ከ18 እና ከ20 ዓመት በታች የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ኢትዮጵያን የሚወክለው ቡድን ከመጋቢት 25 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ መደበኛ ልምምዱን እያደረገ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

ከሚያዝያ 21 እስከ ሚያዝያ 25 ቀን 2015 ዓ.ም. በዛምቢያ አዘጋጅነት በሚካሄው ሻምፒዮና ላይ፣ በአፍሪካ ከ18 እና ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ኢትዮጵያን የሚወክሉ ከ30 በላይ አትሌቶች በሁለቱም ፆታ በሁለቱም የዕድሜ ምድብ ተሳታፊ ይሆናሉ፡፡

ኢትዮጵያውያን ከ800 ሜትር ጀምሮ እስከ 10 ሺሕ ሜትር ድረስ ባሉ የውድድር ርቀቶች የሚወክሉ ሲሆን፣ ዘጠኝ አሠልጣኞች እንዲሁም አራት የሕክምና ቡድን አባላት ዝግጅት እያደረጉ ይገኛሉ፡፡

እንደሚታወቀው በአሁኑ ሰዓት በአገራችንም ሆነ በአዲስ አበባ አካባቢ የትራክ ልምምድ ሥፍራ እንደ ልብ የሌለ ቢሆንም፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር ችግሮችን እየፈታ ለሁለተኛ ጊዜ በሚካሄደው የአፍሪካው የ18 እና 20 ዓመት በታች የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ተከታታይ የሆነ ጠንካራና ከፍተኛ ዝግጅቱን እያደረገ ይገኛል፡፡

ብሔራዊ ቡድኑ በቃሊቲ፣ በሰንዳፋ፣ በሱሉልታ፣ እንዲሁም በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ መደበኛ ልምምድ እያደረጉ እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡ አትሌቶቹ በአሰላ በተሰናዳው ከ20 ዓመት በታች እንዲሁም በድሬዳዋ በተካሄደው ከ18 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ተካፍለው የነበረው አትሌቶች የተመረጡ ናቸው፡፡

በዚህም ሁሉም አትሌቶች ከዚህ ቀደም ዓለም አቀፍ ውድድሮች ላይ ተሳትፈው የማያውቁ እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡ ብሔራዊ ቡድኑ ጥሩ ዝግጅት እያደረገ እንደሚገኝ የተጠቆመ ሲሆን፣ የማዘውተሪያ ሥፍራ ግን እየተፈተነ እንደሆነ ተነግሯል፡፡

ብሔራዊ ቡድኑ ጣፎ በሚገኘው የአሸዋ ትራክ እንዲሁም አንድ ለእናቱ በሆነው የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ትራክ ላይ ልምምዱን እያደረገ እንዲሚገኝ ተጠቁሟል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ኮሚሽን ሪፖርት ምን ይዟል?

ለአሜሪካ ድምፅ አማርኛ ዝግጅት የስልክ አስተያየት የሰጡ አንድ የደንበጫ...

መንግሥት በአማራ ክልል ለወደሙ የአበባ እርሻዎች ድጋፍ እንዲያደርግ ተጠየቀ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአማራ ክልል የተፈጠረው ግጭትና አለመረጋጋት በቢዝነስ...

አምናና ዘንድሮ!

እነሆ መስከረም ጠብቶ በአዲስ መንፈስ ተሞልተን መንገድ ጀምረናል። ‹‹አዲስ...