Tuesday, October 3, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየሴቶች ንፅህና መጠበቂያ ችግርን ለማቃለል የተዘረጋ ውጥን

የሴቶች ንፅህና መጠበቂያ ችግርን ለማቃለል የተዘረጋ ውጥን

ቀን:

የኢትዮጵያ ልጃገረድ ተማሪዎች በመደበኛ የትምህርት ገበታቸው ላይ እንዳይገኙ ከሚያደርጋቸው መሠረታዊ ምክንያቶች መካከል የሴቶች የወር አበባ የንፅህና መጠበቂያ (ሞዴስ) እጥረት እንደሆነ በተደጋጋሚ ይነገራል፡፡

በተለይ በገጠራማ ቦታዎች ላይ የሚገኙ ሴት ልጆች የችግሩ ገፈት ቀማሽ ሆነዋል፡፡ ችግሩ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ በመምጣቱ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ሊሰናከሉ ችለዋል፡፡ ችግሩን ለመቅረፍ መንግሥትና የተለያዩ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እየሠሩም ይገኛሉ፡፡ ከእነዚህ መካከል እሸት ችልድረን ኤንድ ዩዝ ዴቨሎፕመንት ኦርጋናይዜሽን ይገኝበታል፡፡

የእሸት ችልድረን ኤንድ ዩዝ ዴቨሎፕመንግ ኦርጋናይዜሽን ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሲሳይ ታረቀኝ እንደገለጹት፣ በኢትዮጵያ አብዛኛው ሴት ልጆች የንፅህና መጠበቂያ ባለማግኘታቸው የተነሳ ከትምህርት ገበታቸው እየቀሩ ነው፡፡

በተለይ በክልሎች ላይ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ይህ ችግር እንደሚታይባቸው የተናገሩት ዋና ሥራ አስኪያጁ፣ ችግሩን ለመቅረፍ ተቋሙ በአሰላ ከተማ በሚገኙ ሲሊንጎ የመጀመርያ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ ምቹ የሴቶች ማረፊያ በመገንባት ሥልጠና እየሰጠ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በአሰላ ከተማ ትምህርት ቤት የተገነባው የሴቶች ማረፊያ አንድም ሴቶች የወር አበባ ሲመጣባቸው የሚያርፉበት፣ በሌላ በኩል ደግሞ ለስለስ ባሉ ጨርቆች የንፅህና መጠበቂያ  የሚሰፋበት መሆኑን አክለው ገልጸዋል፡፡

ተቋሙ ከዚህ ቀደም ይህንን ተሞክሮ በአዳማ ከተማ በሚገኝ ትምህርት ቤት ላይ መሥራቱን ገልጸው፣ በቀጣይም በሌሎች ክልሎች በማስፋፋት ሴቶች በንፅህና መጠበቂያ ችግር ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው እንዳይቀሩ እንደሚሠሩ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

አብዛኛው በገጠራማ ቦታ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ላይ የሴቶች ንፅህና መጠበቂያ እንደልብ እንደማይገኝ፣ ይህንን በመረዳት መንግሥት የበኩሉን ድርሻ መወጣት እንዳለበት ተናግረዋል፡፡

 በአሰላ ከተማ በሚገኘው ትምህርት ቤት ላይ አርባ ሴቶችና አርባ ወንዶች ሥልጠና እንዲያገኙ በማድረግ የሴቶችን ንፅህና መጠበቂያ በተለያዩ ጨርቆች በእጃቸው እንዲሰፉ እየተደረገ ነው ሲሉ አስረድተዋል፡፡

በተለይ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የማኅበረሰብ ክፍሎች ለልጆቻቸው የንፅህና መጠበቂያ ለመግዛት እንደሚቸገሩ፣ ይኼም በክልሎች ውስጥ ብቻ ሳይሆን በአዲስ አበባ ከተማም ጭምር እንደሚታይ አቶ ሲሳይ ተናግረዋል፡፡

ከተለያዩ ጨርቃ ጨርቆች የሚሠራው የንፅህና መጠበቂያን ደረጃቸውን የጠበቀ ባይሆንም የብዙ ሴት ልጆችን ችግር የሚያቃልል መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የሴቶች ንፅህና መጠበቂያ (ሞዴስ) ዋጋ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱ ችግሩን እንዳጎላው የተናገሩት አቶ ሲሳይ፣ አሰላ ከተማ ውስጥ ከንፅህና መጠበቂያ ሞዴስ እጥረት ውጭ የሴቶች ጥቃት የሚበዛበት ቦታ መሆኑን አስታውሰዋል፡፡

ከዚህ በፊት በአሰላ ከተማ የሴቶች ጥቃት በተመለከተ ከፍተኛ ችግር እንደነበር በሒደት ግን ችግሩ እየተቀረፈ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

እሸት ችልድረን ኤንድ ዩዝ ዴቨሎፕመንት ኦርጋኔዝሽን የሕፃናትና የወጣቶችን ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና የጤና ችግሮችን በማቃለል አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን ዋና ሥራ አስኪያጁ ገልጸዋል፡፡

በዋጋ መናር ምክንያት በገጠር የኢትዮጵያ ክፍል የሚኖሩ 72 በመቶ ወጣት ሴቶች የንፅህና መጠበቂያ ምርቶችን እንደማያገኙ የኢትዮጵያ የሥነ ሕዝብ ጤናና አካባቢ ጥበቃ ጥምረት የተሰኘ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ያጠናወ ጥናት ያሳያል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ተመድንና ዓለም አቀፋዊ ሕግን ከእነ አሜሪካ አድራጊ ፈጣሪነት እናድን!

በገነት ዓለሙ በእኔ የተማሪነት፣ የመጀመርያ ደረጃ ተማሪነት ጊዜ፣ የመዝሙር ትምህርት...

የሰላም ዕጦትና የኢኮኖሚው መንገራገጭ አንድምታ

በንጉሥ ወዳጅነው ፍራንክ ቲስትልዌይት የተባሉ አሜሪካዊ ጸሐፊ ‹‹The Great Experiment...

ድህነት የሀብት ዕጦት ሳይሆን ያለውን በአግባቡ ለመጠቀም አለመቻል ነው

በአንድነት ኃይሉ ድህነት ላይ አልተግባባንም፡፡ ብንግባባ ኖሮ ትናንትም ምክንያት ዛሬም...