Monday, July 22, 2024

[የክቡር ሚኒስትሩ ባለቤት የቴሌቪዥን ቻናሎችን እየቀያየሩ ሲመለከቱ ቆይተው አንድ ጉዳይ ቀልባቸውን ስቦ ጥያቄ ሰነዘሩ]

 • የሱዳን የጦር ኃይሎች በከተማ ውስጥ እርስ በርስ ፍልሚያ መጀመራቸውን ሰማህ?
 • አዎ። ወንድም የሆነውን ሕዝብ ለመከራ ዳረጉት።
 • እኔ እንኳን እሱን ለማለት አልነበረም።
 • እና ምን ልትይ ነበር?
 • ነገሩ ከሰሞኑ ውሳኔያችሁ ጋር መገጣጠሙ ገርሞኝ ነው።
 • የቱ ውሳኔ?
 • የክልል ልዩ ኃይሎችን አስመልክቶ የወሰናችሁት።
 • ምን አገናኘው?
 • የሱዳኑ ክስተት እናንተ ካስረዳችሁት በተሻለ ሁኔታ ስለ ውሳኔያችሁ ምክንያትና አስፈላጊነት ግንዛቤ ይፈጥራል ማለቴ ነው።
 • እንዴት? የእኛ ምክንያት ምንድነው?
 • ፍርኃት ነዋ!
 • የምን ፍርኃት?
 • የሱዳኑ እንዳይከሰት።
 • ፍርኃት እንኳን አይደለም። ቢሆንም ሌላውም በዚህ መልኩ ቢረዳው ጥሩ ነበር።
 • ምን ያድርጉ ብለህ ነው?
 • እንዴት?
 • እነሱም ፈርተው ነዋ።
 • ለምን ይፈራሉ?
 • ሌላ ኃይል ይወረኛል፣ መሬቴን ይወስዳል ብለው ይሆናላ።
 • እነሱ እንኳ ገና ከግጭት እየወጣን ስለሆነ ቢሰጉ አይገርምም፣ የሕዝቡ ግን ግራ ያጋባል።
 • የሕዝቡ ምን?
 • ለተቃውሞ አደባባይ ወጥቶ መንገድ መዝጋቱ?
 • ምን ያድርግ ብለህ ነው?
 • እንዴት?
 • ፈርቶ ነዋ!
 • ለምን ይፈራል?
 • ያፈናቅሉኛል፣ ጥቃት ይደርስበኛል ብሎ ነዋ?
 • መንግሥት ባለበት አገር?
 • መንግሥት ያነጻጽር ይሆናል እንጂ አይጠብቀኝም ብሎ ይሆናላ?
 • የምን ንጽጽር? ከምን?
 • አሜሪካ ላይ ከደረሰ ጥቃት፡፡
 • ካንቺ ቁም ነገር መጠበቄ ነው ስህተቱ፡፡
 • አትሳሳት! ቁም ነገር ነው ያወራሁት!
 • ምኑ ነው ቁም ነገሩ?
 • የዚህ አገር ችግር ምን እንደሆነ እየነገርኩህ እኮ ነው?
 • ምንድነው የዚህ አገር ችግር?
 • ፍርኃት!
 • የምን ፍርኃት?
 • አለመተማመን የወለደው ፍርኃት፡፡

[ክቡር ሚኒስትሩ ዋና ጸሐፊው ጉብኝት እንዳያደርጉ መከልከላቸውን በተመለከተ ስለወጣው መረጃ ከአማካሪያቸው ጋር እየተወያዩ ነው]

 • ክቡር ሚኒስትር ባዘዙኝ መሠረት ዋና ጸሐፊው ጉብኝት እንዳያደርጉ የከለከለው ማን እንደሆነ የሚመለከታቸውን ተቋማት መረጃ ጠይቄያለሁ።
 • እሺ፣ ምን ምላሽ አገኘህ?
 • አንዳንዶቹ ጨርሶ መረጃውን አልሰሙም።
 • እነሱን ተዋቸውና የሌላውን ንገረኝ።
 • የውጭ ግንኙነት ሰዎች በዚህ ጉዳይ ኦፊሳላዊ ምላሽ እንደማይሰጥ ነው የነገሩኝ።
 • እንዴ? አጋሮቻችን ኦኮ እየጠየቁን ነው? ምላሽ የለንም ልንላቸው ነው?
 • እኔም ይህንኑ ጥያቄ አንስቼ ነበር።
 • እሺ ምን አሉህ?
 • የግድ ምላሽ ለሚፈልጉት ብቻ ማለት ያለብንን ነግረውኛል።
 • ምን በሏቸው አሉ?
 • እኛ አልከለከልንም፣ የመንግሥት አቋም አይደለም!
 • ምን ማለት ነው? ማነው የወሰነው ብለው መጠየቃቸው ይቀራል እንዴ?
 • አኔም ይህንኑ አንስቼ ነበር።
 • እሺ፣ ማን አሉ?
 • በግላቸው!

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...

ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም በሌላት አገር ዘመናዊ ስታዲየም እየገነቡ ያሉ ክልሎች

አዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዘመናዊ ስታዲየም ለማስገንባት ከ500 ሚሊዮን...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከፍተኛ ትርፍ ቢያገኝም የውጭ ምንዛሪ ገቢው ቅናሽ ማሳየቱ ተጠቆመ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ2016 የሒሳብ ዓመት ያሰባሰበው የውጭ ምንዛሪ...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[ክቡር ሚኒስትሩ የቅርብ ወዳጃቸው ከሆነች አንድ ባለሀብት የተደወለላቸውን ስልክ አንስተው በኮሪደር ልማቱ ላይ የምታቀርበውን ቅሬታ እየሰሙ ነው]

ክቡር ሚኒስትር እኔ የኮሪደር ልማቱ ላይ ተቃውሞም ሆነ ጥላቻ እንደሌለኝ የሚያውቁ ይመስለኛል? በዚህ እንኳን አትታሚም።  የእውነቴን ነው ክቡር ሚኒስትር። አውቃለሁ ስልሽ? ለኮሪደር ልማቱ አዋጡ ሲባልም ያለማመንታት አምስት ሚሊዮን...

[ክቡር ሚኒስትሩ በችግኝ ተከላ ፕሮግራም ላይ ሳይገኝ ከቀረው አንድ የተቋማቸው ባልደረባ የሆነ የተቃዋሚ ፓርቲ አባልን አስጠርተው እያናገሩ ነው]

ለምንድነው በዚህ አገራዊ ፋይዳ ባለው ፕሮግራም ላይ ያልተገኘኸው? ክቡር ሚኒስትር ህሊናዬ አልፈቀደልኝም። መቃወምና መተቸት ብቻ ውጤት የሚያመጣ መስልዎህ ከሆነ ተሳስተሃል። አልተሳሳትኩም ክቡር ሚኒስትር? ቆይ የመጀመሪያ ዓመት የችግኝ ተከላ...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላነጋግርህ የፈለኩት ክቡር ሚኒስትር፡፡ እርስዎማ ቀጠሮ መያዝ አያስፈልግዎትም፣ ምን ገጠመዎት? እኔማ ምን ይገጥመኛል አንተኑ ልጠይቅህ እንጂ? ምን? እውነት ለመናገር የማየው ነገር አሳስቦኛል፡፡ ይንገሩኝ...