Monday, June 24, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየትራፊክ ሥርዓት አለመዘመን የፈጠረው አደጋ

የትራፊክ ሥርዓት አለመዘመን የፈጠረው አደጋ

ቀን:

በኢትዮጵያ በቸልተኝነትና ሕግን በመጣስ ለትራፊክ አደጋ ተጋላጭ የሚሆኑ አሽከርካሪዎችና እግረኞች በርካታ ናቸው፡፡ በተለይም የትራፊክ ፍሰት ሥርዓቱ የዘመነ አለመሆኑ የበርካታ ዜጎችን ሕይወት እየተቀጠፈ ይገኛል፡፡ የተሽከርካሪና የእግረኛ ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ ደግሞ ለከተማዋ ፈተና ሆኗል፡፡  

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ የ2015 በጀት ዓመት የስድስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርቱን፣ ማክሰኞ ሚያዝያ 17 ቀን 2015 ዓ.ም. ለመንገድ ደኅንነት ምክር ቤት ሲያቀርብ የተነሳውም የዘርፉ ችግሮች አለመፈታታቸው ነው፡፡

ሪፖርቱ ከመቅረቡ በፊት ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ምትኩ አስማረ እንደገለጹት፣ በአዲስ አበባ ከተማ የተሽከርካሪና የእግረኛ ቁጥር በየጊዜው እየጨመረ በመምጣቱ፣ በከተማዋ ፈጣን ዕድገት ለማስመዝገብ ትልቅ እንቅፋት ሆኗል፡፡

የትራፊክ አደጋ ተጋላጭነትን ለመቀነስና በዘርፉ ላይ የሚታየውን ችግር ለመቅረፍ መንግሥት ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ ቢሆንም፣ በግዴለሽነትም ሆነ በተለያዩ ችግሮች ምክንያት ዜጎች ወጥተው እየቀሩ መሆኑን አክለው ገልጸዋል፡፡  

ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ 211 ሰዎች በትራፊክ አደጋ ሕይወታቸውን ሲያጡ፣ በ991 ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል፡፡ 749 ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላል የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው አስረድተዋል፡፡

በከተማዋ የትራፊክ አደጋ ችግርን ለመፍታት የከተማ አስተዳደሩ ከ2009 ዓ.ም. ጀምሮ የ13 ዓመታት የመንገድ ደኅንነት ስትራቴጂ በማዘጋጀት ሰፊ እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑንም ኃላፊው ተናግረዋል፡፡

በተለይ ለሞትና ለከፍተኛ ጉዳት መንስዔ ከሆኑ ችግሮች መካከል ጠጥቶ ማሽከርከርና በፍጥነት መንዳት እንደሚጠቀሱ፣ ችግሮቹን ለመቅረፍ አዳዲስ የቴክኖሎጂ አሠራሮች ተግባራዊ እየተደረጉ መሆኑን አስታውሰዋል፡፡

ሪፖርቱን ያቀረቡት የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ክበበው ሚደቅሳ እንደተናገሩት፣ በኢትዮጵያ በየጊዜው የሚስተዋለውን የትራፊክ አደጋ ለመቀነስ የደንብ ማሻሻዎችን ማፅደቅ ያስፈልጋል፡፡

በከተማዋ የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ ተቋሙ የተለያዩ ሥራዎችን መሥራቱን ገልጸው፣ ከእነዚህም ውስጥ የሌሊት ዕይታን ለማሻሻል የመንገድ መብራት ጥገና መከናወኑን አስታውሰዋል፡፡

በልመናና በሕገወጥ ንግድ ለተሠማሩ ሰዎች መብራት ላይ ምፅዋት የሰጡ 830 አሽከርካሪዎች ላይ ቅጣት መጣሉንም አስታውሰዋል፡፡

አስፋልት ዳር የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ለትራፊክ አደጋ ተጋላጭ እንዳይሆኑ የፍጥነት መገደቢያ መዘርጋቱን፣ ይህም ያጋጥሙ የነበሩ ችግሮችን በተወሰነ መልኩ ማቃለሉን ገልጸዋል፡፡

ከዚህ ጎን ለጎን ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ በታዋቂ ሰዎች፣  በበራሪ ጽሑፍ፣ በመኪና በመዘዋወር የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ መሠራቱን አክለዋል፡፡

በሪፖርቱ እንደ ችግር ካነሱት መካከል የትራፊክ ፍሰት ሥርዓቱ አለመዘመን፣ የመንገድ አጠቃቀም ችግር፣ በቅንጅት አለመሥራት፣ የተወሰኑ የምክር ቤት አባል ተቋማት ሚናቸውን በአግባቡ መወጣት ላይ ውስንነት መኖር ይገኙበታል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አስጨናቂው የኑሮ ውድነት ወዴት እያመራ ነው?

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የኑሮ ውድነት እንደ አገር ከባድ ፈተና...

‹‹ወላድ ላማቸውን አርደው ከደኸዩት ወንድማማቾች›› ሁሉም ይማር

በንጉሥ ወዳጅነው   የዕለቱን ጽሑፍ በአንድ አንጋፋ አባት ወግ ልጀምር፡፡ ‹‹የአንድ...

የመጋቢቱ ለውጥና ፈተናዎቹ

በታደሰ ሻንቆ ሀ) ችኩሎችና ገታሮች፣ መፈናቀልና ሞትን ያነገሡበት ጊዜ እላይ ...

ጥራት ያለው አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ሥርዓት ሳይዘረጉ አገልግሎት ለመስጠት መነሳት ስህተት ነው!

በተለያዩ የመንግሥትና የግል ተቋማት ውስጥ ተገልጋዮች በከፈሉት ልክ የሚፈልጉትን...