Thursday, June 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዓለምየዓረብ አገሮች ከሶሪያ መሪ ጋር የጀመሩት ግንኙነት ተቃውሞ አስነሳ

የዓረብ አገሮች ከሶሪያ መሪ ጋር የጀመሩት ግንኙነት ተቃውሞ አስነሳ

ቀን:

በሶሪያ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ዓረብ አገሮች ከሶሪያ ፕሬዚዳንት በሽር አል አሳድ ጋር የጀመሩትን ግንኙነት በመቃውም በኢድሊብና በሌሎች የሶሪያ ከተሞች ሠልፍ ወጥተዋል፡፡

‹‹ፕሬዚዳንት በሽር አል አሳድ ለሕግ ይቅረቡ፣ ሁሉም የታሰሩ ዜጎች ይፈቱ፣ ከአገራቸው የተሰደዱ ዜጎች ወደ አገራቸው ይመለሱ›› በማለት ተቃውሞ ያሰሙ ዜጎች፣ በተለይ አንዳንድ የዓረብ አገሮች ከአል አሳድ መንግሥት ጋር እየጀመሩ ያሉት ግንኙነት አግባብ አይደለም ማለታቸውን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

የአል አሳድ ጠንካራ ተቀናቃኞች በሚገኙበት ኢድሊብ ከተማ ከፍተኛው የተቃውሞ ሠልፍ የተደረገበት መሆኑን ዘገባው ጠቁሞ፣ በበርካታ የሰሜን ምዕራብ ሶሪያ አካባቢዎች የተቃውሞ ሠልፍ መካሄዱን አሥፍሯል፡፡

እሑድ ሚያዝያ 15 ቀን 2015 ዓ.ም. የተካሄደው የተቃውሞ ሠልፍ፣ በሶሪያ ላለፉት 12 ዓመታት በተካሄደ የእርስ በርስ ጦርነት ከቀዬአቸው የተፈናቀሉ ዜጎች በተጠለሉበት አዛዝ፣ የቱርክና የሶሪያ ድንበር ከተማ በሆነችው ታል አባያድ እንዲሁም በጥቂት ተሳታፊ በአምስተርዳም፣ በበርሊንና ቬይና ውስጥ ነው፡፡

የተቃውሞ ሠልፉ የተደረገው የሶሪያ ሕዝብ አብዮት እንዲከስም ላደረጉ የዓረብ አገሮች የቅሬታ መልዕክት ለማስተላለፍ እንደሆነም አስተያየቱን ለአልጀዚራ የሰጠ ወትዋች ገልጿል፡፡

የሶሪያ ፕሬዚዳንት በሽር አል አሳድን ከሥልጣን ለማውረድ እ.ኤ.አ. በ2011 የተጀመረው ተቃውሞ ግቡን ሳይመታ ሶሪያን ለእርስ በርስ ጦርነት ዳርጓታል፡፡ መንግሥት ለመለወጥ የታለመ ተቃውሞም አገሪቱ የጦር ምድር እንድትሆን፣ ሕዝቦች እንዲሞቱና እንዲፈናቀሉ፣ ቅርሶችና መሠረተ ልማቶች እንዲወድሙ፣ አጠቃላይ ሥርዓቱ እንዲጎዳ አድርጓል፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ ኃያል ነን የሚሉ አካላትና የታጠቁ ቡድኖችም በውክልና ጦርነት ሶሪያን አንኮታኩተዋታል፡፡ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ሰዎች በጦርነቱና በጦርነቱ ምክንያት ሲሞቱ፣ ከጦርነት በፊት ከነበረው የሶሪያ ሕዝብ ግማሽ ያህሉ ቤቱን ጥሎ እንዲሰደድም አድርጓል፡፡

አሁን በታጣቂ ቡድኖች ተይዛ በምትገኘውና የሦስት ሚሊዮን ሶሪያውያን መኖሪያ በነበረችው ኢድሊብ ከተማ ከነዋሪዎቿ ግማሽ ያህሉ ተፈናቅሏል፡፡

‹‹በዚህ መከራ ውስጥ እየኖርን ነው›› ያሉ ሶሪያውያንም፣ የሶሪያና የዓረብ አገሮች ግንኙነት መታደስን ነቅፈውታል፡፡ አንዳንድ ተቃዋሚዎችም፣ ‹‹ለአል አሳድ ይቅርታ የሚያደርግና ዕርቅ የሚፈጽም ቢኖር ወንጀለኛ ነው፤›› የሚል መፈክር ይዘው ታይተዋል፡፡

በሶሪያ ጦርነቱ ከተቀሰቀሰ ከ2011 በኋላ ሳዑዲ ዓረቢያና በርካታ የዓረብ አገሮች ከአል አሳድ መንግሥት ጋር የነበራቸውን ግንኙነት ትተው የሶሪያ ታጣቂዎችን ይደግፉ የነበረ መሆኑን ያስታወሰው ዘገባው፣ አሁን ላይ በሩሲያና በኢራን የሚደገፈው የአል አሳድ መንግሥት፣ በርካታ ቦታዎችን እየያዘ መሆኑን ተከትሎ የዓረብ አገሮች ግንኙነት እያደሱ መሆኑን ጠቁሟል፡፡

ተቃዋሚዎች እንዳሉት፣ ከአል አሳድ ጋር የሚኖር ዕርቅ ዕውን የሚሆነው በሕግ ከተጠየቁና ሁሉም እስረኞች ከተፈቱ በኋላ ነው፡፡

ተቃዋሚዎች ከአል አሳድ መንግሥት ጋር ነገሮችን አመቻችቶ መቀጠል አብዮቱን እንደማንቋሸሽ ነው ቢሉም፣ የዓረብ አገሮች ዳግም ግንኙነት እያደሱ ነው፡፡

እ.ኤ.አ. በ2018 ከሶሪያ ጋር የነበረው ግንኙነት ዳግም ያደሰው የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ ሲሆን፣ ቀዳሚውን ሥፍራ በመያዝም ደማስቆን ከሌሎች ዓረብ አገሮች ጋር እያስተሳሰረ ይገኛል፡፡

ከወር በፊት ሳዑዲ ዓረቢያና የሶሪያ ቀኝ እጅ ኢራን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ማደሳቸውም ሌሎች የዓረብ አገሮች ከሶሪያ ጋር የነበራቸውን የሻከረ ዲፕሎማሲ እንዲለሳለስ አግዟል፡፡

የሳዑዲ ዓረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ልዑል ፈይሰል ቢን ፋራን ከፕሬዚዳንት አል አሳድ ጋር በደማስቆ የተወያዩ ሲሆን፣ ይህም ሶሪያ በቀጣናው የገጠማት መገለል እንዲያበቃ ዕድል መክፈቱ ተነግሯል፡፡

የሶሪያ ከፍተኛ ዲፕሎማት ፈይሰል መክዳድ ሳዑዲ ዓረቢያን፣ አልጀሪያን፣ ቱኒዚያንና ግብፅን የጎበኙ ሲሆን፣ ከዘጠኝ የዓረብ አገሮች የተውጣጡ ዲፕሎማቶችም በሶሪያ ለዓመታት የዘለቀው ጦርነት እንዲያከትም በሳዑዲ ዓረቢያ ጂዳ መምከራቸው ይታወሳል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በአዲስ አበባ በድምቀት ተከበረ

የአዛርባጃን ኤምባሲ  የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በትላንትናው ዕለት አከበረ። ሰኞ...

የመንግሥትና የሃይማኖት ልዩነት መርህ በኢትዮጵያ

እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገሮች የሃይማኖት ተቋማት አዎንታዊ ሚና የጎላ...

ሐበሻ ቢራ ባለፈው በጀት ዓመት 310 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ

የአንድ አክሲዮን ሽያጭ ዋጋ 2,900 ብር እንዲሆን ተወስኗል የሐበሻ ቢራ...