Monday, June 24, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበኢትዮጵያ የወባ በሽታ ሥርጭት መጠን በሁለት ዓመት ውስጥ ጭማሪ ማሳየቱ ተገለጸ

በኢትዮጵያ የወባ በሽታ ሥርጭት መጠን በሁለት ዓመት ውስጥ ጭማሪ ማሳየቱ ተገለጸ

ቀን:

በኢትዮጵያ ያለፉት ሁለት ዓመታት የወባ ሥርጭት መጠን ጭማሪ የታየበት በመሆኑ በቀጣይ ጊዜያት ወደነበረበት ለመመለስ እንዲሁም በሰባት ዓመት ውስጥ ወባን ከአገሪቱ  ለማጥፋት የተለያዩ ስልቶች ተነድፈው እየተተገበሩ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በየዓመቱ ሚያዝያ 17 ቀን የሚከበረውን የዓለም የወባ ቀን ምክንያት በማድረግ ሚኒስቴሩ ከትናንት በስቲያ በሰጠው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ በተከታታይ የተከሰቱ ተፈጥሯዊና ሰው ሠራሽ ችግሮች ለወባ በሽታ መስፋፋት ምክንያት ናቸው።

ባለፉት አሥር ዓመታት በወባ በሽታ ምክንያት በየዓመቱ የሚከሰተውን የሕመምና የሞት መጠን በመቀነስ በአገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ውጤት ቢመዘገብም፣ ያለፉት ሁለት ዓመታት የወባ ሥርጭት መጠን ጭማሪ የታየበት በመሆኑ በቀጣይ ጊዜያት ወደነበረበት ለመመለስ እንዲሁም እ.ኤ.አ በ2030 ከአገሪቱ ለማጥፋት የተለያዩ ስልቶች ተነድፈው በመተግበር ላይ እንደሚገኝ የገለጹት የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ደረጀ ዱጉማ (ዶ/ር) ናቸው፡፡

እንደ ሚኒስትር ዴኤታው ማብራሪያ፣ ለመጨመሩም ሰው ሠራሽና ተፈጥሯዊ ምክንያቶቹ ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር ተያይዞ የዝናብ መቆራረጥ በመኖሩ፣ የወንዞች መቆራረጥና የድርቅ መከሰት፣ ከመስኖ ልማት ጋር በተያያዘ በየአካባቢው ያቆረ ውኃ መኖር፣ በማኅበረሰብ፣ በባለሙያዎችና በአመራሩ ዘንድ ከአሁን በፊት በተሠሩ ሥራዎች ወባ በከፍተኛ ደረጃ ሲቀንስ በተሳሳተ አረዳድ ጠፍቷል በሚል መዘናጋት መኖር ይጠቀሳሉ፡፡

የወባ በሽታ ከሰሃራ በታች በሚገኙ የአፍሪካ አገሮች ዋነኛ የጤናና የማኅበራዊ ዕድገት ችግር እንደሆነ የጠቆሙት ሚኒስትር ዴኤታ ደረጀ (ዶ/ር)፣ የዓለም ወባ ቀንን በየዓመቱ ማክበር የሚያስፈልግበት ዋና ምክንያት በሽታው አንዱና ዋነኛ የኅብረተሰብ የጤና ችግር በመሆኑ በወባ መከላከል፣ መቆጣጠርና ማስወገድ ላይ የሁሉንም ባለድርሻ አካላትን ተሳትፎና ድጋፍ የሚጠይቅ በመሆኑ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ማኅበረሰቡ በወባ መከላከል፣ መቆጣጠርና ማስወገድ ላይ ያለውን ግንዛቤ ለመጨመር የሚያስችሉ የተለያዩ ማስገንዘቢዎችን ማካሄድ፣ የወባ ትንኝ ቁጥጥርን ማጠናከር (የመኝታ አጎበርን ኅብረተሰቡ እንዲጠቀም ማቅረብ፣ የቤት ውስጥ የፀረ ወባ ትንኝ ኬሚካል ርጭት ማካሄድና የአካባቢ ቁጥጥርን መሥራት)፣ የወባ በሽታ ምርመራና ሕክምና አገልግሎት መስጠት፣ የወባ በሽታ ቅኝትና ምላሽ (Surveillance and response) ማጠናከር፤ የወባ በሽታን ከኢትዮጵያ ለማጥፋት እየተተገበሩ ያሉ ዋና ዋና ስልቶች መሆናቸውንም አመልክተዋል፡፡

የወባ አስተላለፊ ትንኝ አዲስ ዝርያ Anopheles Stephensi በተገኘባቸው በድሬዳዋ፣ ሶማሌ፣ ኦሮሚያና አፋር ክልሎች ውስጥ በሚገኙ ስምንት ከተሞች ላይ የወባ እጭ ቁጥጥር እየተሠራ ይገኛል፡፡ የወባ በሽታ የሚጠረጠሩ ሰዎችን ለመመርመር የሚያስችል በቂ መመርመሪያ ኪትና የፀረ ወባ መድኃኒቶች ግዢ ተካሂዶ በኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ቅርንጫፎች በኩል ለጤና ተቋማት መሠራጨቱንና እየተሠራጨም እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

በቀጣይ ከበልግ ዝናብ ጋር ተያያዞ የወባ ሥርጭት መጠን እንዳይጨምር መወሰድ ያለበት ጥንቃቄን አስመልክቶ ሚኒስቴሩ እንዳሳሰበው፣ ያልተሠራጩ የመኝታ አጎበሮችን በአስቸኳይ ለኅብረተሰቡ ማድረስ፣ ኅብረተሰቡም የተሰጠውን የመኝታ አጎበር ቢያንስ እስከ ሦስት ዓመት ድረስ በአግባቡ መያዝና በትክክል መጠቀም ይገባል፡፡

እንዲሁም ማኅበረሰቡ የአካባቢ ቁጥጥርን በመሥራት ግቢውንናና አካባቢውን ለወባ ትንኝ መራባት ምቹ እንዳይሆኑ ውኃ ያቆሩ ቦታዎችን በማፋሰስና በመደልደል እንዲሁም ውኃ ሊያቁሩ የሚችሉና ለቤት ውስጥ አገልግሎት የማይሰጡ ቁሳቁሶችን (የመኪና ጎማ፣ የሸክላ ስባሪዎች፣ የወዳደቁ ጣሳዎች፣ ወዘተ.) በማስወገድ የወባ አስተላላፊ ትንኝ እንዳትራባ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

የወባ ቅኝት፣ ክትትል፣ ግምገማ በማድረግ በሽታው መጨመር በሚታይባቸው አካባቢዎች በወረርሽኝ መልክ ተከስቶ ጉዳት እንዳያደርስ አፋጠኝ ምላሽ መስጠት ያስፈልጋል፡፡

‹‹ጊዜው ፈጠራንና ሀብትን ሥራ ላይ በማዋል ወባን የምናስወግድበት ነው›› በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ያለው የዓለም ወባ ቀን፣ ከሚያዝያ 25 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ለአምስት ተከታታይ ቀናት በሐዋሳ ከተማ በወባ ላይ የተሠሩ ልዩ ልዩ ጥናቶች የሚቀርቡበትና የማኅበረሰብ ንቅናቄ ሥራዎችም እንደሚከናወኑ ከሚኒስትር ደኤታው ማብራሪያ ለመረዳት ተችሏል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አስጨናቂው የኑሮ ውድነት ወዴት እያመራ ነው?

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የኑሮ ውድነት እንደ አገር ከባድ ፈተና...

‹‹ወላድ ላማቸውን አርደው ከደኸዩት ወንድማማቾች›› ሁሉም ይማር

በንጉሥ ወዳጅነው   የዕለቱን ጽሑፍ በአንድ አንጋፋ አባት ወግ ልጀምር፡፡ ‹‹የአንድ...

የመጋቢቱ ለውጥና ፈተናዎቹ

በታደሰ ሻንቆ ሀ) ችኩሎችና ገታሮች፣ መፈናቀልና ሞትን ያነገሡበት ጊዜ እላይ ...

ጥራት ያለው አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ሥርዓት ሳይዘረጉ አገልግሎት ለመስጠት መነሳት ስህተት ነው!

በተለያዩ የመንግሥትና የግል ተቋማት ውስጥ ተገልጋዮች በከፈሉት ልክ የሚፈልጉትን...