- ክቡር ሚኒስትር ስለ ሁለተኛው ዙር ድርድር የሚያውቁት ነገር አለ?
- ሁለተኛ ዙር ድርድር ማለት?
- ሰሞኑን ይጀመራል ስለተባለው?
- ‹‹ጦርነት ይብቃ፣ ሰላምን እናፅና›› ብለን ሰሞኑን ዕውቅና ሰጥተን ጉዳዩን ዘግተነው የለም እንዴ?
- እሱንማ አውቃለሁ።
- ታዲያ ሁለተኛ ዙር የሰላም ድርድር የምትለው ምንድነው?
- በታንዛኒያ የሚካሄደውን ማለቴ ነው?
- እ … እሱን ነው እንዴ?
- አዎ።
- ታዲያ ምን ማወቅ ፈልገህ ነው?
- ሸኔ የሚባለው ማን እንደሆነ ማወቅ ፈልጌ ነው?
- ምን ማለትህ ነው? የትጥቅ ትግል የከፈተብን ነዋ?
- የት?
- እዚሁ አገራችን ውስጥ ነዋ?
- አገር ውስጥ መሆኑማ ገብቶኛል። የትኛው እንደሆነ ግን ለማወቅ አልቻልኩም።
- እንዴት? ስንት ሸኔ አለና ነው ለማወቅ የተቸገርከው?
- ባለፈው በሁለት አካባቢ የሚንቀሳቀሱ ሸኔዎች እንዳሉ አለቃ ሲናገሩ አልነበረ እንዴ?
- እህ … እሱ ነው ግራ ያጋባህ?
- አዎ።
- እንዲያው ዝም ብለህ እንጂ ነገሩ እንኳን ግራ የሚያጋባ አልነበረም።
- እንዴት ክቡር ሚኒስትር?
- ገና ለድርድር አልደረሰማ!
- ምኑ?
- አንደኛው ሸኔ።
- ታዲያ ከየትኛው ጋር ነው ድርድሩ የተጀመረው?
- በሌላ ክልል ከሚንቀሳቀሰው ጋር።
- ከእሱኛው ሸኔ ነው?
- አዎ። ምነው ደነገጥክ?
- እንዴት ከዚህ ቡድን ጋር መንግሥት ለሰላም ድርድር ተቀመጠ ብዬ ነዋ?
- ይህማ መንግሥታችን የሚገለጽበት አንዱ ባህሪ ነው።
- የቱ?
- ሆደ ሰፊነቱ!
- ግን ክቡር ሚኒስትር ቡድኑ የሚያነሳው ጥያቄ በሰላም ድርድር የሚፈታ ነው?
- እንዴት?
- ምክንያቱም ቡድኑ ወደ ትጥቅ ትግል የገባበት ዓላማ ይታወቃል። አሁንም ይህንኑ ዓላማውን ከማሳካት ወደ ኋላ እንደማይመለስ በይፋ እየገለጸ እኮ ነው?
- የትግሉ ዓላማ ምንድነው?
- እሱማ ግልጽ አይደል እንዴ?
- እኮ ለእኔ ግልጽ አድርግልኛ?
- እንዴ ክቡር ሚኒስትር?
- አቤት? ግልጽ አድርግልኛ?
- እኔ ግልጽ ነው አልኩኝ እንጂ፣ ሌላ ነገር እኮ አልተናገርኩም?
- ሌላ ነገር ምን?
- የትግል ዓላማው ትክክል አይደለም አላልኩም።
- አዎ፣ እንደዚያ አላልክም።
- ትችትም አልሰነዘርኩም።
- አዎ፣ አልተቸህም።
- እደግፋለሁም አላልኩም።
- ምን ሆንክ? ጤነኛ አይደለህም እንዴ?
- ኧረ ደህና ነኝ ክቡር ሚኒስትር።
- ታዲያ ለምን ተደነባበርክ፣ የትግል ዓላማውን ግለጽልኝ ነው እኮ ያልኩህ?
- እሱንማ ሰምቻለሁ።
- እኮ ግለጽልኛ?
- የክልሉ ሕዝብ የራሱን ዕድል በራሱ የመወሰን መብት እስኪያገኝ ድረስ እታገላለሁ ነው የሚለው።
- እርግጠኛ ነህ?
- አዎ! በድረገጹ ላይም ሆነ በሚዲያዎች በይፋ ነው የሚገለጸው።
- አልቀየረም?
- አልቀየረም። ይህንን ማሳካት ነው የሚፈልገው።
- እንዴት? ይህማ አይሆንም!
- እኔም የሰላም ድርድር ሊጀመር ነው ሲባል ግራ የገባኝ በዚህ ምክንያት ነው።
- እንደዚያማ ሊሆን አይችልም።
- እንዴት?
- የሰላም ሊባል አይችልም።
- ምኑ?
- ድርድሩ።
- ታዲያ የምን ሊባል ነው።
- ድርድር።
- እኮ የምን ድርድር ሊባል ይችላል?
- ድርድር ብቻ!
- ምን ለማሳካት?
- እሱን አብረን እንሰማለን።
- መቼ?
- መጨረሻ ላይ።
- Advertisment -
- Advertisment -