Wednesday, June 19, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ስፖርትሰርከስ ኢትዮጵያና አንደኛው የሰርከስ ፌስቲቫል

ሰርከስ ኢትዮጵያና አንደኛው የሰርከስ ፌስቲቫል

ቀን:

በ1950ዎቹ አካባቢ ግለሰቦቹ በተለያዩ መድረኮች የሰርከስ ትዕይንቶችን ለማሳየት ሲጥሩ እንደነበር ይነገራል፡፡ በወቅቱ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ቴአትር ቤት (ብሔራዊ ቴአትር) ሰርከስ የሚያሳዩ ሰዎች ብቅ ብቅ ማለት መጀመራቸው ይጠቀሳል፡፡

በአንፃሩ በዘመናዊ መልክ መቅረብ የጀመረው በ1980 ዓ.ም. ሲሆን በተለያዩ  ከተሞች ሰርከስን መመልከት የተለመደ ነበር፡፡

ሰርከስ ባህር ዳር፣ ሰርከስ በጅማ፣ ሰርከስ ትግራይ፣ ሰርከስ አዳማ፣ እንዲሁም ደሴ፣ ደብረ ብርሃን፣ ድሬዳዋ እየተባለ ይዘወተር ነበር፡፡ የሰርከስ ትዕይንቶች በትምህርት ቤት፣ በበዓላት እንዲሁም በአደባባዮች ላይ ይዘወተራሉ፡፡

- Advertisement -

በተለያዩ አገሮች ላይ ኢትዮጵያን ወክለው ተሳትፎ የሚያደርጉ የሰርከስ ኢትዮጵያ ቡድኖች አገር ጉድ አስብለው ሲመለሱ መመልከት እየተለመደ መጥቷል፡፡

በሁሉም የዕድሜ ክልል የሚወደደው ሰርከስ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተቀዛቀዘ መጥቷል፡፡ ቀድሞ በኢትዮጵያ ሁሉም ከተሞች የሚዘወተረው ሰርከስ አሁን ላይ ደብዛው እየጠፋ ለመምጣቱ የተለያዩ ጉዳዮች ይጠቀሳሉ፡፡ በአንፃሩ በኢትዮጵያ የሰርከስ አርቲስቶች በተለያዩ አገሮች ላይ እየተዘዋወሩ ትርዒታቸውን የሚያሳዩ ወጣቶች ይገኛሉ፡፡

በአውሮፓና በአሜሪካ በግልና በቡድን፣ እየተዘዋወሩ አገራቸውን እያስጠሩ የሚገኙ አርቲስቶች አሉ፡፡

በቅርቡ በአውሮፓ የተለያዩ ከተሞች የባህር ዳር ሰርከስ ትርዒቱን ሲያሳይ ሰንብቷል፡፡

ሰርከስ ባህር ዳር በአውሮፓ ቆይታውን ሲያደርግ፣ በተለይ በጀርመን የጥበብ ትርዒቱን ከሦስት ወራት በላይ ሲያሳይ እንደነበር ተጠቅሷል፡፡ ዘጠኝ አባላትን በመያዝ በአውሮፓ የተለያዩ ከተሞች እየተዘዋወረ ትርዒቱን ሲያቀርብ የነበረው የባህር ዳር ሰርከስ ከተመሠረተ 19 ዓመት እንደሞላው ይነገራል፡፡

በአገር ውስጥ እንቅስቃሴ እየደበዘዘ ቢመጣም፣ በዓለም አቀፍ መድረኮች  ግን ያለው ተሳትፎ የነቃ እንደሆነ የኢትዮጵያ ሰርከስ ማኅበር ጥምረት ፕሬዚዳንት አቶ ተክሌ አሻግሬ ያስረዳሉ፡፡ ይህም በአገር ውስጥ በሰርከስ ስማቸው ሲጠቀስ የሚታወቁ ሰርከስ ደሴ፣ ሰርከስ ደብረ ብርሃን፣ እንዲሁም ሰርከስ ትግራይ የዓለም አቀፍ መድረኮች ለመጠቀም ሰፊ ዕድል እንዳላቸው ይገልጻሉ።

በየዓመቱ ከአንድ ሺሕ በላይ አርቲስቶች፣ በተለያዩ አገሮች ትርዒታቸውን ለማቅረብ እንደሚጓዙም አውስተዋል።

አርቲስቶቹ በዓለም ከፍተኛ ደረጃ በተሰጣቸው ትርዒቶች ሳይቀር መካፈል መጀመራቸውን አቶ ተክሉ ይናገራሉ፡፡

በዚህም አንድ ተወዳዳሪ በወሩ 10 ሺሕ ዶላር ማግኘት የሚያስችለውን አጋጣሚ እንደተፈጠረ ይጠቀሳል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የሰርከስ ማኅበር በሰባት ክልሎችና ሁለት ከተማ አስተዳደሮችን የሚገኙ 53 ሕጋዊ የሰርከስ ተቋማትን አቅፏል። በ1997 ዓ.ም. በወጣው አዲስ የማኅበራትና የበጎ አደራጎት አዋጅ በኋላ፣ የሰርከስ ኢትዮጵያ እንቅስቃሴ ማቆሙን የሚያነሱት አቶ ተክሉ፣ ሙሉ በሙሉ ትኩረቱ ወደ ዓለም አቀፍ ማዞሩ የአገር ውስጡን እንቅስቃሴ እንዳደበዘዘው ያብራራሉ፡፡

ሆኖም ግን ሰርከስ እየተሻሻለ ለመምጣት አንዱ ማሳያ በአገሪቱ የሰርከስ ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ ነው። ጥበቡ ለዓለም አቀፍ መድረኮች ትኩረት ማድረጉ በአገር ውስጥ እንደተረሳ ተደርጎ ተቆጥሯል ይላሉ፡፡

በርካታ አርቲስቶች ኢትዮጵያን በተለያዩ መድረኮች  ወክለው በመሳተፍ  በስምንት ዘርፍ የዓለም ድንቃ ድንቅ ላይ መሳተፍ ችለዋል፡፡

የሥልጠና አዳራሽ ዕጦት፣ የግንዛቤ እጥረትና የታክስ ችግር ጥበቡን እየፈተነው እንደሚገኝ አቶ ተክሉ አክለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የሰርከስ ማኅበር ጥምረት ከሚያዝያ 27 እስከ 29 ቀን 2015 ዓ.ም. በአዲስ አበባ፣ የኢትዮጵያ የባህል ማዕከል አንደኛውን አገር አቀፍ የሰርከስ ፌስቲቫል እንደሚያካሂድ አስታውቋል፡፡

ፌስቲቫሉ የሰርከስ ትርዒትን እንደ ኪነ ጥበብ በመገንዘብ ያሸበረቁ የኢትዮጵያ ባህላዊ፣ ማኅበራዊና ሃይማኖታዊ እሴቶችን ለተቀረው ዓለም ለማስተዋወቅ ያለመ  እንደሆነ ተገልጿል፡፡

ፌስቲቫሉ ለአፍሪካ ሰርከስ ጥበብ አስተዋጽዖ እንደሚኖረው ለፈጠራ የሰርከስ ትርዒት ዕድገት የራሱን ሚና ይጫወታል ተብሏል። ዝግጅቱ የሰርከስ ኩባንያዎችና አርቲስቶች ምርቶቻቸውን በዓለም አቀፍ ገበያ ለመሸጥ ከተለያዩ የሰርከስ ፕሮዳክሽን ድርጅቶች ጋር እንዲገናኙ ዕድል እንደሚሰጥም ተጠቁሟል፡፡

ፌስቲቫሉ የተለያዩ አጓጊ ክንውኖችን እንደሚያስተናገዱበት የተገለጸ ሲሆን ስብሰባዎች፣ የሕዝብ መዝናኛዎች፣ የልምድ ልውውጥ፣ የሰርከስ ጥበብ ውድድርና ትርዒቶች በዓለም መድረክ መሪ በሆኑ ኢትዮጵያውያን የሰርከስ አርቲስቶች እንደሚቀርቡ ታውቋል፡፡ በዝግጅቱ ላይ ከ80 በላይ ብሔረሰቦች የባህል እሴቶች በጥበብ እንደሚቀርቡም ተጠቁሟል፡፡

ለሦስት ቀናት በሚቆየው ፌስቲቫል ከ20,000 በላይ ታዳጊዎች ይገኛሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ ከሰባት ክልሎች የተውጣጡ 53 የሰርከስ ቡድኖችና 250 የሰርከስ አርቲስቶች ትርዒቶቻቸውን ያቀርባሉ፡፡

የኢትዮጵያ ሰርከስ ፌስቲቫል የማዘጋጀት አጠቃላይ ዓላማ ሁሉም የሰርከስ ቡድኖችን በማሰባሰብ በኢትዮጵያ ውስጥ የሰርከስ ጥበብን ይበልጥ ለማስተዋወቅ በራሳቸውና በዓለም አቀፍ ማኅበረሰቦች መካከል መልካም ተሞክሮዎችን የሚለዋወጡበት መድረክ መፍጠር ነው፡፡ እንደ አዘጋጆቹ ገለጻ፣ የፌስቲቫሉ  ዓላማዎች የኢትዮጵያ የሰርከስ ዕድገትና አቅም ለአገርና ለዓለም አቀፍ ባለድርሻ አካላት ማሳየት፣ በኢትዮጵያ ሰርከስ ኩባንያዎችና ድርጅቶች መካከል ጠንካራና አዎንታዊ ግንኙነት መፍጠር፣ የሰርከስ ጥበብን በኢትዮጵያ ተመራጭ የመዝናኛ መንገድ ማድረግ፣ የሰርከስ ትርዒት ለኅብረተሰቡ ያለውን ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊና ባህላዊ ፋይዳ  ማሳየት የሕዝቡን ማኅበራዊ ትስስር በተሳታፊዎች መካከል መልካም ተሞክሮ በመለዋወጥ መልሶ መገንባት ናቸው፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅና የሚስተጋቡ ሥጋቶች

ከሰሞኑ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ...

የመጨረሻ የተባለው የንግድ ምክር ቤቱ ምርጫና የሚኒስቴሩ ውሳኔ

በአገር አቀፍ ደረጃ ደረጃ የንግድ ኅብረተሰቡን በመወከል የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ...

ሚስጥሩ!

ጉዞ ከካዛንቺስ ወደ ስድስት ኪሎ፡፡ የጥንቶቹ አራዶች መናኸሪያ ወዘናዋ...