Sunday, June 16, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊዕገታ የሚያሻው ፀረ ተሕዋስያን መላመድ

ዕገታ የሚያሻው ፀረ ተሕዋስያን መላመድ

ቀን:

  • የማሕፀን በር ጫፍ ካንሰርና የኮቪድ-19 በሽታ ክትባት ዘመቻ በመካሄድ ላይ ነው

በዓለምና በአገር አቀፍ ደረጃ የሰዎችን ጤና ለከፋ ጉዳት ለተለያዩ የማኅበራዊ ቀውሶች ከሚዳረጉ አሥር የጤና ሥጋቶች መካከል ፀረ ተሕዋስያን መላመድ አንዱና ዋነኛው ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ይህም ሊሆን የቻለበት ምክንያት ከፀረ ተሕዋስያን መድኃኒቶች አጠቃቀም ጋር የተያያዙ ብዙ ክፍተቶች በመታወቃቸው ነው፡፡

ከክፍተቶቹም መካከል ለታካሚዎች የሚቀርቡ የመድኃኒት አማራጮች እያነሱ መምጣት፣ ሕመሞች በቀላሉ ሊድኑ አለመቻል፣ በአጭር ጊዜ ሊድኑ የሚችሉ ሕመሞች ረዥም ጊዜ በመውሰዳቸውና በዚህም የተነሳ ለተለያዩ ወጪዎች መዳረጋቸው ይገኙባቸዋል፡፡

የጤና ሚኒስትር ደኤታ ደረጀ ድጉማ (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ ይህ ዓይነቱ ችግር ከግምት ውስጥ በማስገባት ከአሥር ዓመት በፊት ከፀረ ተሕዋስያን መላመድ ጋር የተያያዘ የፖሊሲ ሰነድ ተዘጅቶ ተግባራዊ በመደረግ ላይ ይገኛል፡፡

- Advertisement -

ሰነዱ ሁለት ጊዜ ከመሻሻሉም ባለፈ በርካታ የአሠራር ነጥቦችን አካቷል፡፡ ካካተታቸውም ነጥቦች መካከልም የፀረ ተሕዋስያን መላመድን እንዴት መከላከል እንደሚቻል፣ በዚህ ዙሪያ ማኅበረሰቡ ምን ማድረግ እንዳለበት ሆስፒታሎችና ፋርማሲዎች እንዴት ኃላፊነታቸውን መወጣት እንዳለባቸው፣ እንዲሁም የቁጥጥር ሥርዓቱ ምን መምሰል እንዳለበት የሚጠቁሙና ሌሎች እንደሚገኙበት ነው የተናገሩት፡፡

የፀረ ተሕዋስያን መላመድ ችግር ከሰው ጤና ጋር ብቻ ሳይሆን ከእንስሳት ጤና ጋር የተያያዘ ስለሆነ ጤና ሚኒስቴር ከግብርና ሚኒስቴር፣ ሌሎችም ጉዳዩ ከሚመለከታቸው መንግሥታዊ ድርጅቶችና ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅትና በትብብር እንደሚሠራ ሳይገልጹ አላለፉም፡፡

በዝርዝር የተካተቱ ነጥቦች በሁሉም ሆስፒታሎች ውስጥ መሥራት እንደሚያዳግት በመገንዘብ በተመረጡ አሥር ሆስፒታሎች ውስጥ ግን ተግባራዊ እየተደረጉ መሆኑን፣ የመድኃኒቱን አያያዝና አቀማመጥ ግልጽነት እንዲኖረው መደረጉንም ተናግረዋል፡፡

‹‹ሰውነታችን የሚጎዱ ፀረ ተሕዋስያን መድኃኒትን መላመድ ሲጀምሩ ፀረ ተሕዋስያን መላመድ የሚለውን የአቻ ትርጉም ይወስዳሉ፤›› ያሉት ሚኒስትር ደኤታው በአሥሩም ሆስፒታሎች ውስጥ ፀረ ተሕዋስያን መላመድን የሚከላከሉና የሚቆጣጠሩ ኮሚቴዎች ተቋቁመው ኃላፊነታቸውን በመወጣት ላይ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡

በተካሄደውም የመከላከልና የመቆጣጠር ሥራ አማካይነት ፀረ ተሕዋስያን መድኃኒቶችን ማንም ሰው እንደፈለገው እንዳያዝ ለማድረግ እንዲቻል በሦስት ደረጃዎች ተለይተው እንዲቀመጡ ተደርጓል፡፡ በዚህም መሠረት ማንም ሰው በቀላሉ ማዘዝ የሚያስችለውን ለመላመድ ብዙም ሥጋት የሌላቸው፣ በሐኪም ብቻና በከፍተኛ ሐኪሞች ማለትም በስፔሻሊስቶችና በሰብ ስፔሻሊስቶች የሚታዘዙት እንደየቅደም ተከተላቸው በአንደኛ፣ በሁለተኛና በሦስተኛ ደረጃ ተለይተው ተይዘዋል፡፡

ከዚህም ሌላ ለማኅበረሰቡ በፀረ ተሕዋስያን መድኃኒቶች አጠቃቀም ላይ ትኩረት ያደረጉ የግንዛቤ ማስጨበጫ የሆነ ትምህርት አዘል ምክር መሰጠቱን ገልጸው፣ የተሰጠውም ምክሩም መድኃኒቶችን ሐኪም ባዘዘው መሠት ባግባቡ እንዲወስዱና እንዲጨርሱ፣ በምንም መልኩ ለሌላ ሰው እንዳያካፍሉ፣ ሳይጨርሱ እንዳይተዉ የሚጠቁም መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የግል ፋርማሲዎችም ያለ ሐኪም ትዕዛዝ እንዳይሸጡ እየተደረገ መሆኑን፣ ከውጭ የሚገቡ መድኃኒቶች ትክክለኛ ፈዋሽነታቸው የተረጋገጠ፣ ታዋቂና ትክክለኛ ከሆነ የመድኃኒት አምራች ኩባንያ መመረታቸውና መግባትቸው የማረጋገጥ ሥራ ተጠናክሮ እንደቀጠለም ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ የማሕፀን በር ጫፍ ካንሰርና የኮቪድ በሽታዎች መከላከያ ክትባት ለአሥር ቀናት ያህል በአገር አቀፍ ደረጃ ከሚያዝያ 17 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ በመካሄድ ላይ ነው፡፡

ከእነዚህም በሽታዎች መካከል የማሕፀን በር ጫፍ ካንሰር መከላከያ ክትባት ለአራት ቀናት ከተሰጠ በኋላ የኮቪድ 19 በሽታ መከላከያ ክትባት ደግሞ ለስድስት ቀናት ይጀመራል፡፡

በጤና ሚኒስቴር የእናቶች፣ ሕፃናትና አፍላ ወጣቶች ጤና አገልግሎት መሪ ሥራ አስፈጻሚ መሠረት ዘለዓለም (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ የመጀመርያው ዙር የማሕፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት ዕድሜያቸው 14 ዓመት ለሆናቸው ሴት ልጆች ይሰጣል፡፡

ባለፈው ዓመት ለወሰዱ ደግሞ ሁለተኛው ዙር ክትባት እንደሚሰጥ ነው የተናገሩት፡፡

እንደ ሥራ አስፈጻሚዋ አነጋገር፣ የመደበኛ ክትባት ጭራሽ ያልተከተቡና ጀምረው ያቋረጡ ዕድሜያቸው ከሁለት ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናት የመደበኛ ክትባት አገልግሎት ያገኛሉ፡፡ የኮቪድ 19 በሽታ መከላከያ ክትባት ዕድሜያቸው 12 ዓመትና ከዚያም በላይ ለሆኑ የኅብረተሰብ ክፍሎች ይሰጣሉ፡፡

‹‹እስከ ሚያዝያ 24 ቀን 2015 ዓ.ም. ድረስ በሚከናወነው በዚሁ ዘመቻ አራት ዋና ዋና ሥራዎች ይሠራሉ፡፡ እነርሱም ቤት ለቤት በሚደረግ ጉብኝት ዕድሜያቸው አምስት ዓመት ለሆኑ ሕፃናት የምግብ እጥረት ልየታ ከተደረገ በኋላ ችግር ያለባቸውን ሕፃናት ወደ ጤና ተቋም በመላክ ሕክምና እንዲያገኙ ይደረጋል፤›› ብለዋል፡፡

አፍላ ወጣቶች የጤና ምክር አገልግሎት መስጠት፣ ፌስቱላ ላጋጠማቸው እናቶች ልየታና በቀጣይ ሕክምና የሚያገኙበት ሁኔታ ማመቻቸት ከሚጠበቁት ሥራዎች መካከል ተጠቃሾች መሆናቸውን ነው ያመለከቱት፡፡

በዚህም ዘመቻ ወቅት በየደረጃው ያሉ አመራሮች የክትባት አገልግሎቱን የሚሰጡ የጤና ባለሙያዎች፣ ወላጆች/አሳዳጊዎች፣ መምህራንና አጠቃላይ የሚመለከታቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች አስፈላጊውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ መሠረት (ዶ/ር) ጥሪ አቅርበዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የምግብ ዋጋ ንረት አጣዳፊ ዕርምጃ ያስፈልገዋል!

መንግሥት የሚቀጥለውን ዓመት በጀት ይዞ ሲቀርብ በአንገብጋቢነት ከሚነሱ ጉዳዮች...

ከባለአንድ ዋልታ ወደ ባለብዙ ዋልታ የዓለም ሥርዓት የመሸጋገራችን እውነታ

በአብዱ ሻሎ አንገት ማስገቢያ እ.ኤ.አ. በፌብሩዋሪ 2022 የሩሲያ መንግሥት በዩክሬን ‹‹ልዩ...

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የውጭ ግንኙነት የሺሕ ዘመናት ታሪኳና እሴቶቿን የሚመጥን መሆን ይኖርበታል

(ክፍል አንድ) በተረፈ ወርቁ (ዲ/ን) እንደ መንደርደሪያ ለዛሬው የግል ትዝብቴንና ታሪክን ላዛነቀው...

ከአገር ግንባታ ጋር የተያያዙ ወሳኝ የቅርብ ታሪካችን አንጓዎች

በታደሰ ሻንቆ በአያሌው የተመረጡና ልጥ የሌላቸው ነጥቦች የተደራጁበት ይህ ታሪክ...