Wednesday, October 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናኢሠማኮ ነገ ሊያደርገው የነበረው ሰላማዊ ሰልፍ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመከልከሉ ተሰርዟል...

ኢሠማኮ ነገ ሊያደርገው የነበረው ሰላማዊ ሰልፍ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመከልከሉ ተሰርዟል አለ

ቀን:

_ፓሊስ የደረሰኝም ሆነ የሰማሁት ነገር የለም ብሏል

የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) በየዓመቱ ሚያዝያ 23 ቀን የሚከበረውን የዓለም የሠራተኞች ቀን (ሜይዴይ)፣ ነገ ሚያዚያ 23 ቀን 2015 ዓም በሰላማዊ ሰልፍ በመስቀል አደባባይ እንደሚከበር የተነገረና ሪፖርተር ጋዜጣም በዛሬው እትሙ የዘገበ ቢሆንም፣ ዛሬ ሚያዚያ 22 ቀን 2015 ዓም ምሽት ላይ መሰረዙ ተነግሯል።

በኢሠማኮ ፕሬዚደንት አቶ ካሣሁን ፎሎ ፊርማ ተረጋግጦ ለሪፖርተር የተላከው መግለጫ እንደሚገልጸው፣ በዓሉ በተለያዩ ዝግጅቶች ሲከበር መቆየቱ ይታወቃል። በዘንድሮው 48ኛው የሜይዴይ በዓልን በአዲስ አበባና ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶቹ በሚገኙበት በሰላማዊ ሰልፍ ለማክበር | አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ሲያደርግ ቆይቶ፣ የበዓሉን አከባበርና አጠቃላይ መርሀ-ግብር አስመልክቶ ሚያዝያ 21 ቀን 2015 ዓ.ም. ጋዜጣዊ መግለጫ በመገናኛ ብዙሀን ማስተላለፉ አስታውሷል፡፡

ነገር ግን ሚያዝያ 23 ቀን 2015 ዓ.ም. በመስቀል አደባባይ በዓሉን ለማክበር የተያዘው ፕሮግራም “የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጸጥታ ቢሮ ስለከለከለን” ፕሮግራሙን ለመሰረዝ የተገደድን መሆኑን እየገለጽን፤ ይህንኑ መልዕክት የኢትዮጵያ ሠራተኞች እንዲያውቁት ብሏል።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንም ነገ ሚያዚያ 23 ቀን 2015 ዓም ምንም የሚያውቃቸው ኩነቶችና ሰልፍ እንደሌለም አስታውቋል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ተመድንና ዓለም አቀፋዊ ሕግን ከእነ አሜሪካ አድራጊ ፈጣሪነት እናድን!

በገነት ዓለሙ በእኔ የተማሪነት፣ የመጀመርያ ደረጃ ተማሪነት ጊዜ፣ የመዝሙር ትምህርት...

የሰላም ዕጦትና የኢኮኖሚው መንገራገጭ አንድምታ

በንጉሥ ወዳጅነው ፍራንክ ቲስትልዌይት የተባሉ አሜሪካዊ ጸሐፊ ‹‹The Great Experiment...

ድህነት የሀብት ዕጦት ሳይሆን ያለውን በአግባቡ ለመጠቀም አለመቻል ነው

በአንድነት ኃይሉ ድህነት ላይ አልተግባባንም፡፡ ብንግባባ ኖሮ ትናንትም ምክንያት ዛሬም...