በየዓመቱ ሚያዝያ 23 ቀን (ሜይ 1 ቀን) የዓለም ሠራተኞች ቀን – ሜይ ዴይ የሚከበርበት ነው፡፡ የየአገሮቹ ሠራተኞች በመሪ ቃሉ መሠረት የሚያከብሩት አደባባይ ወጥተው በትዕይንተ ሕዝብ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) ዕለቱን መስቀል አደባባይ ምጣኔ ሀብትን በተመለከተ ለመንግሥት ጥያቄ ለማቅረብ የጠራው ሠልፍ እንዳይደረግ ተከልክሎ በአርምሞ አልፎታል፡፡ በተለያዩ አገሮች በዓሉ የተከበረው በአደባባይ ሲሆን አንዷ አክባሪ አገር ናይጄርያ ናት (ያደባባይ ፎቶ)፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በዓሉን አስመልክቶ የእንኳን ያደረሳችሁ መልዕክት በማኅበራዊ ትስስር ገጹ የሚኒስትሯን ሙፈርያት ከማልና የኢሠማኮ ፕሬዚዳንት ፎቶ በማያያዝ ገልጿል፡፡
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -
ፌርማታ ፅሁፎች
ትኩስ ፅሁፎች
- Advertisement -
- Advertisement -