Thursday, June 13, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ኪንና ባህልወጣቶችን ለማነቃቃት ያለመው ፌስቲቫል

ወጣቶችን ለማነቃቃት ያለመው ፌስቲቫል

ቀን:

በኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ የወጣቶች ተሳትፎ አነስተኛ መሆኑ ይታመናል፡፡ በተለይ በአገሪቱ የሚነሱ ችግሮችን ለመፍታት የወጣቱ ሚና ከፍተኛ ቢሆንም፣ በዘርፉ ላይ የተሠራ ነገር አለመኖሩ ችግሩን አባብሶታል፡፡ ይሁን እንጂ አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ችግሩን ለመፍታት ከሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመሆን ለሁለት ቀናት የቆየ ፌስቲቫል አካሂዷል፡፡

ፌስቲቫሉ ‹‹ዛሬን በንቃት ነገን በስኬት›› በሚል መሪ ቃል ሚያዝያ 21 እና 22 ቀን 2015 ዓ.ም. በሚሌኒየም አዳራሽ ተከናውኗል፡፡

ፌስቲቫሉ ‹የከፍታ ለወጣቶች› አካል ሲሆን፣ በጤና፣ በትምህርት፣ በንግድ ሥራና በሰላም ጉዳዮች ላይ ወጣቶች የጎላ አስተዋጽኦ እንዲኖራቸው ለማድረግ ያለመ መሆኑን፣ በአሜሪካ የልማት ተራድዖ ድርጅት የሚደገፈው የአምሬፍ ሔልዝ አፍሪካ ፕሮጀክት አስተባባሪ ቻላቸው ጥሩነህ ይናገራሉ፡፡

- Advertisement -

ፌስቲቫሉ ሲከፈት ንግግር ያደረጉት የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ በወጣቶች ላይ የሚያተኩር እንዲህ ዓይነት ፌስቲቫሎችን በማዘጋጀት የአገሪቱን የሰላም ግንባታ ማጠናከር ያስፈልጋል፡፡

በተለይም መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማትና ሌሎች የማኅበረሰብ ክፍሎች፣ እንዲሁም ወጣቶች ራሳቸው፣ ለተለያዩ ችግር ተጋላጭ መሆናቸውን መረዳት እንዳለባቸው ገልጸው፣ ይህንንም በመረዳት ያልተነካ አቅም መኖሩን በማወቅ አስፈላጊውን መፍትሔ ማዘጋጀት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያም እንዲህ ዓይነት ፌስቲቫሎችን በማዘጋጀት ወጣቶችን በአንድ ላይ በማገናኘት ልዩነቶችን በአንድነት እንዲያዋህዱና እንዲፈቱ ማድረግ ይገባል ያሉት፣ በኢትዮጵያ የአሜሪካ የልማት ተራድዖ ድርጀት ዳይሬክተር ሲያን ጆንስ ናቸው፡፡

ከአገሪቱ የሚሰበሰቡ ወጣቶችን በአንድ ላይ የማምጣት ሐሳቦችን ከፍ ለማድረግ ፌስቲቫሉ ጥሩ ዕድል የሚፈጥር መሆኑን ዳይሬክተሩ አክለው ገልጸዋል፡፡

በአንድ ዓመት ውስጥ 60 ሺሕ ወጣቶችን በአባልነት አቅፎ ሥልጠናና የተለያዩ የማነቃቂያ ሥራዎችን መከናወኑን፣ በቀጣይም የወጣቶች ተሳትፎ የሚጨምር ፕሮጀክት ነው ተብሏል፡፡

ከዚህ ቀደም እንዲህ ዓይነት መሰል ፌስቲቫል በሐዋሳና በባህር ዳር መዘጋጀቱ፣ በአሁኑ ወቅትም በአዲስ አበባ የተዘጋጀው ፌስቲቫል ከ17 ከተሞች የተውጣጡ ከ10 ሺሕ እስከ 20 ሺሕ ታዳሚ ወጣቶች መሆናቸውን በወቅቱ ተገልጿል፡፡

ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት በአሜሪካ የልማት ተራድዖ ድርጅት የሚደገፈው ፌስቲቫሉ፣ የሰሜኑ ግጭት ያደረሰው ጉዳት ግምገማ እንደተጠናቀቀ የትግራይ ክልል ተሳታፊዎችንም እንደሚያካትት ተጠቁሟል፡፡

በሚሌኒየም አዳራሽ በተካሄደው ፌስቲቫል ታዋቂ ድምፃውያኑ ሮፍናን፣ ቬሮኒካ አዳነ፣ እና ግርማ፣ ጃምቦ ጆቴ፣ አስጌ ደንዴሾና መስፍን ብርሃኔ፤ ኮሜዲያኑ ዜዶ፣ ፍልፍሉ፣ በኪ 4 ኪሎና ሙአዝ ጀማል ሥራዎቻቸውን አቅርበዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት...

የመንግሥት የ2017 ዓ.ም በጀትና የሚነሱ ጥያቄዎች

የ2017 ዓመት የመንግሥት ረቂቅ በጀት ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ለሚኒስትሮች...

ከፖለቲካ አባልነትና ከባንክ ድርሻ ነፃ የሆኑ ቦርድ ዳይሬክተሮችን ያካተተው ብሔራዊ ባንክ ያዘጋጃቸው ረቂቅ አዋጅና መመርያዎች

የኢትዮጵያ የብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማትን የተመለከቱት ድንጋጌዎችንና የባንክ ማቋቋሚያ...

የልምድ ልውውጥ!

እነሆ መንገድ ከቦሌ ሜክሲኮ። አንዱ እኮ ነው፣ ‹‹እንደ ሰሞኑ...