Saturday, June 15, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዜናየኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ቴሌቪዥን ጣቢያ እንዲያቋቁም የቀረበው ረቂቅ አዋጅ ቅሬታ ቀረበበት

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ቴሌቪዥን ጣቢያ እንዲያቋቁም የቀረበው ረቂቅ አዋጅ ቅሬታ ቀረበበት

ቀን:

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ቴሌቪዥን ጣቢያ እንዲያቋቁም የቀረበው ረቂቅ ማሻሻያ አዋጅ ከፓርላማ አባላት ተቃውሞ ቀረበበት፡፡

የፕሬስ ድርጅት የማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1151/2011ን ለማሻሻል በቀረበው ረቂቅ ላይ፣ በኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎች መዘመን ምክንያት ዓለም የጥብቆ ያህል እየጠበበች እንደመጣች የሚያብራራው ረቂቁ፣ የቴክኖሎጂው መዘመን አያሌ ጥቅም ቢያስገኝም ከተወዳዳሪነት አለመደበል የተነሳ በኢትዮጵያ ጉዳትም እንዳደረሰ ተመላክቷል፡፡

ለአብነትም ‹‹የሩቁን ትተን በቅርቡ በተካሄደው የሕልውናና የመከላከል ዘመቻ ወቅት ከገጠመን የክህደት ጦርነት ይልቅ፣ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በሚዲያዎቹ የከፈተብን ዘመቻ እጅጉን ጎድቶናል፤›› ይላል፡፡ ይህም የኢትዮጵያን ሰላምና ዕድገት ለማይፈልጉ ኃይሎችም ምቹ ሁኔታ እንደፈጠረላቸው ያብራራል፡፡

- Advertisement -

 በዓለም አቀፍ ደረጃ የኤሌክትሮኒክስ ሚዲያው እያደገ በመሄዱና የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትም ከኅትመት ሚዲያው በተጨማሪ በቴሌቪዥን ዘርፍ ቢሰማራ ውጤታማ ሊሆን እንደሚችል የሚያብራራው ረቂቁ፣ ተቋሙ በዚህ መልኩ ቢቀረጽ ለኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃንም ተጨማሪ አቅም ይፈጥራል ይላል፡፡

ይሁን እንጂ የምክር ቤቱ አባል አቶ አሰማኸኝ አስረስ በሰጡት አስተያየት፣ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ጥሩ እየሠራ በመሆኑ ‹‹ይህን የያዘውን መልክና ይዘት መልቀቅ አለበት ብዬ አላምንም፤›› ስለዚህ ለዚህ ተቋም ቴሌቪዥን እንዲያቋቁም መፍቀድ አሁን ካሉት የብሮድካስት ሚዲያዎች ጋር የተገናኘ ሥራን መድገም ይሆናል ብለዋል፡፡

በረቂቅ አዋጁ እንደ ማሳያ የተወሰደው የኡጋንዳው ኒውቪዥን የተሰኘ የሚዲያ ካምፓኒ መሆኑን ሲያብራሩ፣ ይህ ቪዥን ግሩፕ የተሰኘ ተቋም በቅኝ ግዛት ወቅት በእንግሊዞች እንደተመሠረተ፣ ነገር ግን ይህ ተቋም በተለያየ ጊዜ ስማቸውን እየቀያየሩ እ.ኤ.አ. 1986 ራሱን እንደ ቢዝነስ በመቁጠር፣ አክሲዮን በመሸጥ አሁን ላይ 2000 ባለ አክሲዮኖች ያሉት ተቋም ነው ብለዋል፡፡ ይህ ቪዥን ሚዲያ የቢዝነስ ተቋም በመሆኑ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትን እንደ መነሻ አድርጎ በዚያ መልኩ መቅረጽ በጣም አስቸጋሪ ነው ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ቴሌቪዥን ይክፈት ማለት በመንግሥት ስፖንሰር እየተደረጉ የቀጠሉትን ሚዲያዎች አሁንም የሚደግም ሌላ የሀብት ብክነት ነው ብለዋል፡፡

በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ አባሉ አብርሃም በርታ (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ የፕሬስ ድርጅትን ወደ ብሮድካስት እንዲገባ ያስፈለገበት ምክንያት ግልጽ አይደለም ብለዋል፡፡ አክለውም አሁን በአገሪቱ ውስጥ ያሉት የብሮድካስት ሚዲያዎች ያሉባቸው ችግሮች እየታወቀ፣ ይህን ፕሬስ ድርጅት ወደ ቴሌቪዥንነት መቀየር አስፈላጊነቱ ግልጽ አይደለም ብለዋል፡፡ ስለሆነም ቴሌቪዥን እንዲያቋቁም ማድረጉ ምን እንዲፈጥር ታስቦ ነው በማለት አክለው ጠይቀዋል፡፡

በመጨረሻም በረቂቁ ላይ የተነሱትን ጥያቄዎች በማካተት ለዝርዝር ዕይታ ለዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተመርቷል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት...

የመንግሥት የ2017 ዓ.ም በጀትና የሚነሱ ጥያቄዎች

የ2017 ዓመት የመንግሥት ረቂቅ በጀት ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ለሚኒስትሮች...

ከፖለቲካ አባልነትና ከባንክ ድርሻ ነፃ የሆኑ ቦርድ ዳይሬክተሮችን ያካተተው ብሔራዊ ባንክ ያዘጋጃቸው ረቂቅ አዋጅና መመርያዎች

የኢትዮጵያ የብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማትን የተመለከቱት ድንጋጌዎችንና የባንክ ማቋቋሚያ...

የልምድ ልውውጥ!

እነሆ መንገድ ከቦሌ ሜክሲኮ። አንዱ እኮ ነው፣ ‹‹እንደ ሰሞኑ...