Saturday, September 23, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየእናት ባንክ ‹‹ለእናቴ›› የተሰኘ የጽሑፍ ውድድር ሊያደርግ ነው

የእናት ባንክ ‹‹ለእናቴ›› የተሰኘ የጽሑፍ ውድድር ሊያደርግ ነው

ቀን:

በአበበ ፍቅር

የእናት ባንክ ‹‹ለእናቴ›› የተሰኘ ሁሉንም ማኅበረሰብ የሚያሳትፍና የሚያሸልም አገራዊ የጽሑፍ ውድድር ሊያካሂድ መሆኑን አስታወቀ፡፡

ውድድሩ በዋናነት ሁሉም ሰው ለእናቱ ያለውን ጥልቅ ስሜት፣ ፍቅር፣ አክብሮት፣ ውለታና ምሥጋና እንዲገልጹ ታሳቢ ተደርጎ እንደሆነ ሚያዝያ 26 ቀን 2015 ዓ.ም.  ባንኩ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል፡፡

ውድድሩ ዕድሜ ፆታና እንዲሁም የትምህርት ደረጃ የማይገድበው ሲሆን ማንኛውም ሰው የእናቱን ፍቅር በዝርወ ጽሑፍ፣ በግጥም፣ በወግ መልክና በደብዳቤ መግለጽ የሚችሉበት መድረክ እንደሆነ የእናት ባንክ የማርኬቲንግ ኮሙዩኒኬሽንና የከስተመር ሰርቪስ መምሪያ ዳይሬክተር ወ/ሮ አክሊል ግርማ ተናግረዋል፡፡

የጽሑፉ ማወዳደሪያ መሥፈርትና የውድድሩ ዳኝነት በቋንቋና ሥነ ጽሑፍ ተግባቦት ሰፊ ልምድ ባላቸው ከፍተኛ ባለሙያዎች የተዘጋጀና የሚከናወን መሆኑ ተገልጿል፡፡

‹‹ሁሉም ሰው ለእናቱ ያለውን ፍቅርና ስሜት የሚገልጽበት የራሱ ስሜት አለው፤›› ያሉት አቶ ቴዎድሮስ ተክለ አረጋይ ውድድሩ ሰዎች ለእናታቸው ያላቸውን ጥልቅ ስሜት በጽሑፍ የሚያወጡበትና በሚጽፉት ጽሑፍም ተወዳድረው በአገር አቀፍ ደረጃ ዕውቅናና ሽልማት የሚያገኙበት ነው ብለዋል፡፡

ውድድሩ ዳኞች የተወዳዳሪዎችን አቅም ለመለካትና ስለ እናታቸው ያላቸውን ፍቅርና ስሜት አወዳድረው የሚያበላልጡበት ሳይሆን፣ ይልቁንም ተወዳዳሪዎች ለእናታቸው ያላቸውን ፍቅርና አክብሮት እንዴት እንደሚገልጹና ስሜታቸውን ወደሌሎች ለማጋባት ምን ያህል ተጉዘዋል የሚለውን የሚዳኝበት ዓውድ እንደሆነ ቴዎድሮስ አክለው ተናግረዋል፡፡

ተወዳዳሪዎች ሥራቸውን በአገሪቱ የሥራ ቋንቋ ብቻ ማቅረብ አለባቸው የተባለ ሲሆን የሚቀርቡ ጽሑፎች ከዚህ በፊት በማንኛውም የኅትመትና የኤሌክትሮኒክስ የመገናኛ ብዙኃን ላይ ያልቀረቡ ወጥና አዲስ የተለየ መሆን እንዳለባቸው ተገልጿል፡፡

በሌላ በኩል ጽሑፉ ግልጽና ተነባቢ እንዲሁም በኮምፒዩተር ተጽፎ በ12 ‹‹ፎንት›› የፊደላት መጠንና በ1.5 የህዳግ መስመር መጻፍ እንዳለበትና እንዲሁም በኤ.ፎር የወረቀት ምጣኔ ከሦስት ገጽ ባልበለጠ መሆን ይኖርበታል፡፡

የማወዳደሪያ መሥፈርቶች የቅርፅ ጉዳይ 50 ከመቶ እንዲሁም የይዘት ጉዳይ 50 ከመቶ በድምሩ 100 ነጥብ እንዲይዙ ተደርገው መዘጋጀታቸው ተገልጿል፡፡

በተጨማሪ ተወዳዳሪዎች ስማቸውንና አድራሻቸውን የጽሑፍ ሥራቸውን ባቀረቡበት ወረቀት ላይ ሳይሆን በሚያሽጉበት ፖስታ ላይ ብቻ መጻፍ እንደሚጠበቅባቸው ተነግሯል፡፡

ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ጽሑፋቸውን በአካል ቀርበው ማስነባት ለማይችሉ፣ በተለይ ደግሞ ከአገር ውጭ ለሚገኙ ተወዳዳሪዎች ጽሑፋቸውን በlenat@ enatbanksc.com ላይ ማቅረብ እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡ ለውድድር ቀርበው አሸናፊ የሆኑ ጽሑፎችን ባንኩ በተለያዩ መንገዶች ሊጠቀምባቸው እንደሚችል አስታውቋል፡፡

ተወዳዳሪዎች ጽሑፋቸውን ከሚያዝያ 26 ጀምረው እስከ ግንቦት 23 ድረስ ባሉት የሥራ ቀናት በአቅራቢያቸው ባሉ የባንኩ ቅርንጫፎች በአካል በመገኘት ማስረከብ እንደሚጠበቅባቸው ተነግሯል፡፡

በውድድሩ መዝጊያ ላይ የተወሰኑ የውድድር ተሳታፊዎችና አሸናፊዎች እንዲሁም ጥሪ የሚደረግላቸው እንግዶች ባሉበት እንደሚካሄድ ለአሸናፊዎችም የተዘጋጀው ሽልማት ይበረከትላቸዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ኮሚሽን ሪፖርት ምን ይዟል?

ለአሜሪካ ድምፅ አማርኛ ዝግጅት የስልክ አስተያየት የሰጡ አንድ የደንበጫ...

መንግሥት በአማራ ክልል ለወደሙ የአበባ እርሻዎች ድጋፍ እንዲያደርግ ተጠየቀ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአማራ ክልል የተፈጠረው ግጭትና አለመረጋጋት በቢዝነስ...

አምናና ዘንድሮ!

እነሆ መስከረም ጠብቶ በአዲስ መንፈስ ተሞልተን መንገድ ጀምረናል። ‹‹አዲስ...