በኢትዮ ጵያ አገልግሎት መስጠት ከጀመረ ሰባት ወራትን ያስቆጠረው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሞባይል መኒ (M-PESA) ፈቃድ ማግኘቱን አስታወቀ።
የሳፋሪኮም ኬንያ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሚስተር ፒተር ንዴግዋ ዛሬ ግንቦት 3 ቀን 2015 ዓ ም ንጋት ላይ የተቋማቸውን ዓመታዊ የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት ለባለድርሻ አካላት ሲያቀርቡ እንዳስታወቁት፣ በኢትዮጵያ አገልግሎት መስጠት ከጀመረ ሰባት ወራትን ያስቆጠረው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የድጅታል ፋይናንስ አገልግሎት መስጠት የሚያስችለውን ሞባይል መኒ ፈቃድ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ማግኘቱን አስታውቀዋል። በሚቀጥሉት ሳምንታት አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምርም ጠቁመዋል።