ያሁኑ ጥያቄ፡-
ትናንትም ነበረኝ ዛሬም ጠይቃለሁ፣
ነገ እንዳልጠይቅ ግን አሁን መልስ እሻለሁ፡፡
በጤና፣ በልማት በሌሎችም ዘርፎች፣
በግልፅ ይታያሉ ያሉብን ችግሮች፡፡
ነገር ግን ችግሩን በማስወገድ ፋንታ፣
ሁል ጊዜ አያለሁ የጥናት ጋጋታ፡፡
ተጠንቶ ያለቀው እንደአዲስ ሲጠና፣
ከዚያም ይቀጥላል የማያልቅ ሥልጠና፡፡
በሥልጠናው ላይም ጥያቄ ሲነሳ፣
#ይጠናል$ ይባላል እንዳዲስ ዳሰሳ፡፡
እስከ መቼ?
- አፀደ ውድነህ “ድንጋይ መጽሐፍ ነው” (2005)