Sunday, March 23, 2025
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜና‹‹የኢትዮጵያ ሚና ለሱዳን መንግሥት አዎንታዊና ደጋፊ ነው›› የሱዳን የሽግግር መንግሥት የአፍሪካ ቀንድ...

‹‹የኢትዮጵያ ሚና ለሱዳን መንግሥት አዎንታዊና ደጋፊ ነው›› የሱዳን የሽግግር መንግሥት የአፍሪካ ቀንድ አገሮች ልዩ መልዕክተኛ

ቀን:

spot_img

ከተጀመረ አንደኛ ወሩን ላስቆጠረው የሱዳን ጦርነት ‹‹የኢትዮጵያ ሚና ለሱዳን መንግሥት አዎንታዊና ደጋፊ ነው፤›› ሲሉ፣ የሱዳን የሽግግር መንግሥት ምክር ቤት የአፍሪካ ኅብረትና የአፍሪካ ቀንድ አገሮች ልዩ መልዕክተኛ አስታወቁ፡፡

የሱዳን የሽግግር መንግሥት ምክር ቤት የአፍሪካ ኅብረትና የአፍሪካ ቀንድ አገሮች ልዩ መልዕክተኛው ዳፋላህ አል ሐጅ ዓሊ (አምባሳደር) ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ባለፈው ሳምንት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ጋር በአካል ተገናኝተው እንደነበርና ኢትዮጵያ የሱዳንን ሰላምና ደኅንነት ለማስጠበቅ የምትችለውን ሁሉ እንደምታደርግ አረጋግጠውላቸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ (ዶ/ር) በሱዳን ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ ሌላ የውጭ አካል እንዲጠቀምበት ኢትዮጵያ እንደማትፈቅድ መናገራቸውን፣ ልዩ መልዕክተኛው አስረድተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ወደ ኢትዮጵያ ለመምጣት የወሰኑ ሱዳናውያን ኢትዮጵያን እንደ ሁለተኛ ቤታቸው አድርገው እንዲቆጥሩ እንዳረጋገጡላቸውም ተናግረዋል፡፡ በሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች መካከል የተጀመረው ጦርነት ከጀመረ አንድ ወር ማስቆጠሩ የሚታወስ ነው፡፡ በሱዳን ጦር መሪ ጄኔራል አብዱልፈታህ አል ቡርሃንና የፈጥኖ ደራሽ ኃይል (አርኤስኤፍ) መሪ ጄኔራል መሐመድ ሃምዳን ዳጋሎ (ሄምቲ) መካከል ጦርነቱ የተቀሰቀሰው፣ ሚያዝያ 7 ቀን 2015 ዓ.ም. እንደነበር አይዘነጋም።

በጦርነቱ በትንሹ ከ670 በላይ ሰዎች ሲገደሉ በሺዎች መቁሰላቸው ይነገራል፡፡ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መረጃ እንደሚያሳየው፣ አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ሱዳናውያን ደግሞ ከቀዬአቸው ተፈናቅለዋል።

በሱዳን ለተፈጠረው ግጭት የዓለም አቀፍ ተቋማት ዕገዛና ፈጣን ምላሽ ምን ይመስላል ተብለው የተጠየቁት ልዩ መልዕክተኛው በሰጡት ምላሽ፣ የችግሩን የመጨረሻ ዕልባት በተመለከተ ጉዳዩ የውስጥ ጉዳይ እንደ መሆኑ መጠን የትኛውም አካል እንዲገባ እንደማይፈቅድለት አበክረው ተናግረዋል፡፡ ነገር ግን በግጭቱ ምክንያት ለተከሰተው ሰብዓዊ ድጋፍ ምላሽ ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጋር በትብብር ለመሥራት ቁርጠኝነታቸውን በመግለጽ፣ በግጭቱ ለተጎዱ ዜጎች የሚሰጠውን ምላሽ ለመቀበል የሱዳን መንግሥት ዝግጁ ነው ብለዋል፡፡

ከአራት ቀናት በፊት የሁለቱ ጦር ተወካዮች በሳዑዲ ዓረቢያ የወደብ ከተማ ጅዳ፣ ሰላማዊ ሰዎችን ከጥቃት ለመጠበቅና የረድዔት ድርጅቶችም ዕርዳታን በጦርነቱ ለተጎዱ ወገኖች እንዲያደርሱ የሚያደርግ ስምምነት ላይ እንደደረሱ ይታወሳል።

የሱዳን መንግሥት ሰላምና ፀጥታን የማስጠበቅ ኃላፊነቱን ለመወጣት በሳዑዲ ዓረቢያና በአሜሪካ ተነሳሽነት ለተደረገው እንቅስቃሴ መንግሥታቸው አዎንታዊ ምላሽ መስጠቱን ልዩ መልዕክተኛው አስታውቀው፣ የሱዳን መንግሥት ይህ ግጭት  ዕልባት ማግኘት እንዳለበት ያምናል ብለዋል፡፡

የዜጎችን ደኅንነትና ጥበቃ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ እንደሆነና ተዋጊዎች ሰላማዊ ዜጎችን በሚኖሩባቸው አካባቢዎች እንደ መገኘታቸው ዜጎች የትኛውንም ምግብና መድኃኒት ድጋፍ እንዳያገኙ አድርጓቸው መቆየቱን በማስታወስ፣ መንግሥት የተኩስ አቅም ሐሳቡን የተስማማበት ለዚህ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

በተያያዘም ጄኔራል አብዱልፈታህ አል ቡርሃን አራት ጄኔራል መኮንኖችን ከኃላፊነት ማንሳታቸውን የሱዳን ዜና ምንጮች መዘገባቸው የሚታወስ ሲሆን፣ አራቱን ጄኔራሎች የተነሱት ከጦር ሠራዊቱ ጋር እየተዋጋ ያለው ጀኔራል መሐመድ ዳጋሎ ከሚመሩት ፈጥኖ ደራሽ ሠራዊት ጋር ወግነዋል በማለት እንደሆነ በዘገባዎቹ ተጠቅሷል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የዓለም ኢኮኖሚ ከቀውስ ሥጋት የሚወጣው መቼ ነው? የኢትዮጵያስ እንዴት?

በጌታነህ አማረ የዚህ ጽሑፍ ዓላማ ኢትዮጵያ ለምታበስረውና ለምትከውነው ትንሳዔ ይረዳ...

የንብረቶች ዋጋ ማሽቆልቆልና የምግብ ነክ ሸቀጦች ዋጋ ንረት ተቃርኖ የነገሰበት የአገራችን ገበያ

በኢትዮጵያ ገበያ ውስጥ ያልተቋረጠ የዋጋ ዕድገት እያሳዩ ሲጓዙ ከነበሩ...

ቀጣናዊ ቀውስ ሊፈጥር የሚችለው ውጥረት ይርገብ!

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በትግራይ ክልል ውስጥ በስፋት እየተስተዋለ ያለው...
error: