Thursday, June 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትዋሊያዎቹ በፌዴሬሽኑ የቴክኒክ ዳይሬክተር እንደሚመሩ ተገለጸ

ዋሊያዎቹ በፌዴሬሽኑ የቴክኒክ ዳይሬክተር እንደሚመሩ ተገለጸ

ቀን:

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን (ዋሊያዎቹ) የሚመሩትን ዋና አሠልጣኝ አስታውቋል። ከአሠልጣኝ ውበቱ አባተ ጋር ውሉን ማቋረጡን የገለጸው ፌዴሬሽኑ፣ ቡድኑን በጊዜያዊነት የሚመሩ አሠልጣኞች ስም ይፋ አድርጓል።

ፌዴሬሽኑ ብሔራዊ ቡድኑን ላለፉት ሁለት ዓመታት ሲመሩ ከቆዩት አሠልጣኝ ውበቱ አባተ ጋር በስምምነት ከተለያየ በኋላ፣ ቀጣዩን አሠልጣኝ ለመምረጥ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ባደረገው ውይይት፣ በቴክኒክ ዳይሬክተርነት እየሠሩ የሚገኙት ኢንስትራክተር ዳንኤል ገብረማርያም በጊዜያዊ ዋና አሠልጣኝነት ቀጣይ ጨዋታዎችን እንዲመሩ ከውሳኔ መድረሱን አስታውቋል።

ኢንስትራክተር ዳንኤልን እንዲያግዙ በፕሪምየር ሊጉ በመሥራት ላይ የሚገኙና በወቅታዊ ውጤታማነትም የተሻሉ ሆነው የተገኙት የባህር ዳር ከተማ አሠልጣኝ ደግአረገ ይግዛው ምክትል አሠልጣኝ ሆነው እንዲሠሩ ከውሳኔ መድረሱን ፌዴሬሽኑ ገልጿል።

ከዚህም ባሻገር ፌዴሬሽኑ ለአሠልጣኙና ለክለባቸው ባህር ዳር ከተማ ጥያቄ አቅርቦ ፈቃደኛ በመሆናቸው፣ ምክትል አሠልጣኝ ሆነው ተሾመዋል ሲል ገልጿል። የግብ ጠባቂ አሠልጣኝ ሹመት ደግሞ በቅርቡ እንደሚደረግ ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ጠቁሟል።

ብሔራዊ ቡድኑ በአይቮሪኮስቱ የአፍሪካ ዋንጫ የምድቡን ሦስተኛና አራተኛ ጨዋታ አድርጎ በሁለቱም መረታቱን ተከትሎ ዋና አሠልጣኙን መሰናበቱ ይታወሳል።  ብሔራዊ ቡድኑ አምስተኛውን የምድብ ጨዋታ ሰኔ 13 ቀን ለማከናወን ሞዛምቢክን ምርጫው ማድረጉን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለካፍ አስታውቋል።

ፌዴሬሽኑ በምሥራቅ አፍሪካ አገሮች በሚገኙ ስታዲየሞች ላይ ለማከናወን ጥረት ቢያደርግም፣ አልተሳካለትም ሩዋንዳ ተፈቅዶላት የነበረው ስታዲየም ጊዜያዊ ፈቃዱ በመነሳቱ፣ ታንዛኒያም የተሰጣት ፈቃድ የብሔራዊ ቡድኗን ጨዋታ ብቻ እንድታከናወን በመሆኑ፣ ሱዳን በወቅታዊ አለመረጋጋት እንዲሁም ዑጋንዳና ኬንያ የተፈቀደ ስታዲየም ስለሌላቸው በምሥራቅ አፍሪካ አገሮች ማከናወን አልተቻለም፡፡

ዋሊያዎቹ ለዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ ጠባብ ዕድል ይዘው የማላዊና የግብፅ አቻቸውን ይገጥማሉ።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በአዲስ አበባ በድምቀት ተከበረ

የአዛርባጃን ኤምባሲ  የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በትላንትናው ዕለት አከበረ። ሰኞ...

የመንግሥትና የሃይማኖት ልዩነት መርህ በኢትዮጵያ

እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገሮች የሃይማኖት ተቋማት አዎንታዊ ሚና የጎላ...

ሐበሻ ቢራ ባለፈው በጀት ዓመት 310 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ

የአንድ አክሲዮን ሽያጭ ዋጋ 2,900 ብር እንዲሆን ተወስኗል የሐበሻ ቢራ...