የአርኪ ሪል ስቴት ኤክስፖ ግንቦት 5 ቀን 2015 ዓ.ም. በሚሌኒየም አዳራሽ ተከፍቷል፡፡ በኤክስፖው የቤት ሻጮችና ገዥዎች፣ በኮንስትራክሽን ዘርፉ የተሰማሩ ታላላቅ የሪል ስቴት አልሚዎች እንዲሁም የኮንስትራክሽን ግብዓት አቅራቢዎች እየተሳተፉበት መሆኑን አዘጋጆቹ ተናግረዋል፡፡ የተለያዩ ተቋማትን ለማገናኘትና ለማስተሳሰር ዕድል ይሰጣል የተባለለት ኤክስፖውን ያዘጋጀው አርኪ ኤጀንት ኦርጋናይዘር ነው፡፡ በኤክስፖ ከመቶ በላይ በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶች፣ ባንኮችና አጋር ድርጅቶች ተሳትፈውበታል፡፡ ለሦስት ቀናት በተካሄደው ኤክስፖ የቤት አልሚዎች እየገነቡት ያለው ቤት ያለበት ደረጃ፣ ቤቶቹን ዋጋ፣ ሊገነቡት ስላቀዱት ቤት፣ ስለሚፈልጉት ዕቃና አገልግሎት ከኤክስፖ ተሳታፊዎችና ከጎቢኚዎች ጋር መረጃና ልምድ ተለዋውጠውበታል፡፡
ፎቶ መስፍን ሰለሞን