Sunday, April 14, 2024
- Advertisment -
- Advertisment -

[ክቡር ሚኒስትሩ አየር መንገዱ ወጪ ቆጣቢ የሥራ እንቅስቃሴ በማድረግ የውጭ ምንዛሪ ግኝቱን በሚያሳድግበት ሁኔታ ላይ ከተቋሙ ኃላፊ ጋር እየተወያዩ ነው]

 • ቀደም ብዬ እንደገለጽኩት ትልቁ ወጪያችን ለነዳጅ ግዥ የሚውለው ነው። ክቡርነትዎ እንደሚገነዘቡት የዩክሬን ጦርነት የዓለም የነዳጅ ዋጋ በእጅጉ አሻቅቧል።
 • ቢሆንም አገሪቱ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ችግር ውስጥ ስለምትገኝ አየር መንገዱ ይህንን ለማቃለል አስተዋጽኦ ማድረግ ይኖርበታል።
 • እኛም ይህንን እንገነዘባለን ነገር ግን አብዛኛው ወጪያችን በውጭ ምንዛሪ የሚከፈል በመሆኑ ነው በሚፈለገው ልክ አስተዋጽኦ ማድረግ ያልቻልነው።
 • አቅዳችሁ ከሠራችሁ የሚጠበቅባችሁን አስተዋጽኦ ማሳካት ትችላላችሁ። ዛሬ ባትችሉም ነገ ማድረግ ይቻላል።
 • እርግጥ ነው እኛም ትልቁ ወጪያችንን ለመቀነስና ከአየር ብክለት ነፃ የሆነ በረራ ለማድረግ አቅደን በአገር ውስጥ ነዳጅ ለማምረት ዝግጅት ጀምረናል።
 • ነዳጅ ለማምረት?
 • አዎ። ከአየር ብከለት ነፃ የሆነ ነዳጅ በአገር ውስጥ ለማምረት የጥናት ዝግጅቱ አልቋል።
 • ከአየር ብከለት ነፃ የሆነ ነዳጅ እንዴት ነው የምታመርቱ?
 • ነዳጁን ለማምረት በዋነኝነት የምንጠቀመው ግብዓት መኖ ነው።
 • ምንድነው ?
 • መኖ ነው ያልኩት ክቡር ሚኒስትር።
 • መኖ ለአውሮፕላን? እየቀለዱ ነው?
 • ተረፈ ምርቱን ማለቴ ነው።
 • የአርብቶ አደሩ ከብቶች በድርቅ ምክንያት እያለቁ እንደሆነ አያውቀም?
 • ሰምቻለሁ።
 • ታዲያ ምን የተረፈ ምርት አለ። ከአርብቶ አደሩ ጋር ልትሻሙ ካልሆነ በስተቀር?
 • ከአርብቶ አደሩ የተረፈ መኖ ማለቴ አይደለም።
 • ከመኖው ውስጥ ለምግብነት የማይውለውን ነው ለመጠቀም ያሰብነው።
 • ያው ሽሚያ ነው።
 • እንደዛ አይደለም ክቡር ሚኒስትር። አንደኛ ገና ጥናት ላይ ነው። ሁለተኛ ደግሞ እራሳችን የምናመርተውን መኖ ነው የምንጠቀመው።
 • እንደዛ ነው?
 • አዎ። እንደውም ለምግብነት የሚውለውን ክፍል ለአርብቶ አደሩ ማቅረብ እንችላለን። በተጨማሪም…
 • በተጨማሪ ምን ?
 • ከአየር ብክለት ነፃ የሆነ ነዳጅ ለማምረት የምንጀምረው ፕሮጀክት ስለሆነ በዓለም አቀፍ የገንዘብ ዕርዳታና ብድር የሚተገበር ነው።
 • በውጭ ምንዛሪ ማለት ነው?
 • በትክክል። ለዚህ ተብሎ የተቋቋመ ዓለም አቀፍ የካርበን ልቀት ቅነሳ ፈንድ አለ።
 • ይኼ በጣም ድንቅ ዕቅድ ነው።
 • ይመስለኛል። ፕሮጀክቱን ይሁንታ ካገኘ ፈንዱ ነፃ ፋይናንስና ወለድ የማይከፈልበት የረዥም ጊዜ ብድር ያቀርብልናል።
 • አሁኑኑ ይጀመር። በፍጥነት ይመረት።
 • ምኑ?
 • መኖው፡፡
 • ይህ እኮ እ.ኤ.አ. በ2050 ለማሳካት የያዝነው ዕቅድ ነው ክቡር ሚኒስትር?
 • አሁኑኑ ይጀመር፡፡
 • እ…
 • በተጨማሪ ደግሞ…
 • በተጨማሪ ምን?
 • መንግሥት የሚከታተለው ፕሮጀክት እንደሆነ ይነገር!

 

 

 

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

ያልተቃናው የልጆች የንባብ ክህሎት

አንብቦና አዳምጦ መረዳት፣ የተረዱትን ከሕይወት ጋር አዋህዶ የተቃና ሕይወት...

እንስተካከል!

ሰላም! ሰላም! ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ እንዲሁም የሰው ዘር በሙሉ፣...

የሙዚቃ ምልክቱ ሙሉቀን መለሰ ስንብት

የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ በ1950ዎቹ እና በ1960ዎቹ በኪነ ጥበባትም ሆነ...

‹‹ደስታ›› የተባለችው አማርኛ ተናጋሪ ሮቦት በሳይንስ ሙዚየም

‹‹እንደ ሮቦት ዋነኛው አገልግሎቴ ውስብስብ የሆኑ የቴክኖሎጂ ውጤቶችንና አሠራሮችን...

በአዲስ አበባ ከ700 ሺሕ በላይ የትራፊክ የደንብ ጥሰቶች መፈጸማቸው ተገለጸ

በአዲስ አበባ 716,624 የትራፊክ የደንብ ጥሰቶች መፈጸማቸውን፣ የአዲስ አበባ...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[ክቡር ሚኒስትሩ ከፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባላት ጋር በአገራዊ ጉዳዮች ላይ እየመከሩ ነው]

ክቡር ሚኒስትር ባለፈው ሊያወያዩን ሲመጡ ለአገራችን የፖለቲካ ችግር መፍትሔው አንድና አንድ እንደሆነ ነግረንዎት ነበር፣ ያስታውሳሉ? አላስታውስም። ባለፈው የተገናኘን ጊዜ ይህችን አገር ከችግር የሚያወጣው መፍትሔ አንድና አንድ...

[ክቡር ሚኒስትሩ በዕረፍት ቀናቸው በመኖሪያ ቤታቸው ሆነው ከባለቤታቸው ጋር ከውጭ እንዳይገቡ ስለተከለከሉ ምርቶች እያወሩ ነው]

እኔ እምልህ ...ኤል ሲ እንዳይከፈት ተከልክሏል ሲባል አልነበረም እንዴ? ኤል ሲ ደግሞ ምንድነው? ሌተር ኦፍ ክሬዲት ነዋ!? አልገባኝም? አስመጪዎች ከውጭ ለሚያስገቡት ዕቃ የሚያስፈልጋቸውን የውጭ ምንዛሪ ከባንኮች አይደል የሚያገኙት? አዎ። ኤል...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሥራ መልስ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን በተመስጦ እየተከታተሉ አንዳንዴም በመገረም እየሳቁ አገኟቸው]

አንዴ? ምን አገኘሽ? ምን አገኘሽ ማለት? ለብቻሽ የሚያስቅሽ ማለቴ ነው? እ... ምን ላድርግ ብለህ ነው? ወዶ አይስቁ ሆኖብኝ ነው። እንዴት? ምንድነው ነገሩ? በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን እያዳመጥኩ ነዋ? አለቃ ከሕዝብ ተወካዮች ጋር...