በትምህርት ላይ የሚሠራና ኢትዮጽያን ጨምሮ 26 አገራትን በአባልነት ያቀፈው ኦርጋናይዜሽን ፎር ኤዱኬሽን ኮኦፕሬሽን የተባለ ድርጅት፣ዋና መቀመጫውን አዲስ አበባ አድርጎ ሥራ መጀመሩን አስታወቀ። ዛሬ ግንቦት 10 ቀን 2015 ዓ.ም. በይፋ ሥራ መጀመሩን ያስታወቁት የድርጅቱ ዋና ጸሐፊ አቶ ማንሱር ቢን ሙሳላም እንዳሉት፣ ለዋና ቢሮው ግንባታ የሚውልና ጎጃም በረንዳ አካባቢ የሚገኝ ስድስት ሄክታር መሬት ከመንግስት ተረክበዋል።
የሳውዝ ቱ ሳውዝ ትብብርን በማጠናከር ትምህርት ፍትሃዊ፣ አካታችና ተደራሽ እንዲሆን ድርጅቱ ከአባል አገራት ጋር በመሆን እንደሚሠራና በአገሮቹ ዘላቂ ልማት ለማሰቀጠልም ሳይንሳዊ ጥናቶችን እንደሚተገብር አክለዋል።