Thursday, June 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች ለአዋኪ ድርጊቶች መጋለጣቸው ተጠቆመ

የአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች ለአዋኪ ድርጊቶች መጋለጣቸው ተጠቆመ

ቀን:

በአበበ ፍቅር

ተቋማት ተናበው ባለመሥራታቸውና የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት ባለመወጣታቸው፣ በአዲስ አበባ ውስጥ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ለተለያዩ አዋኪ ድርጊቶች መጋለጣቸው ተነገረ፡፡

በትምህርት ቤቶች አካባቢ የሚገኙ አዋኪ ድርጊቶችን በተመለከተ የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮና የሚመለከታቸው አካላት፣ ግንቦት 10 ቀን 2015 ዓ.ም. ውይይት አድርገው ነበር፡፡

በውይይቱም አገር ተረካቢ በሚሆኑ ታዳጊዎች ላይ ኃላፊነት የጎደላቸውና ሕገወጥ በሆኑ አካላት አማካይነት፣ በተማሪዎች ላይ አዋኪ ድርጊቶች እየተፈጸሙ እንደሆነ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡

በትምህርት ቤቶች እስከ 200 ሜትር ባሉ ርቀቶች የመማር ማስተማር ሒደቱን ሊያውኩ የሚችሉ ጭፈራ ቤቶች፣ የሐሺሽና የትምባሆ ማጨሻ ቤቶች፣ እንዲሁም የጫት መቃሚያና የሲጋራ ማጨሻዎችን ተማሪዎችን ማዕከል አድርገው በመክፈት ትውልድን እያመከኑ እንደሆነ ተነግሯል፡፡

እነዚህን አዋኪ ድርጊቶች የመከላከል ከፍተኛ ሚና የነበራቸው ተቋማት መናበብ ባለመቻላቸውና በጋራ ባለመቆማቸው፣ ትምህርት ቤቶች በተለያዩ እኩይ ተግባራት ተከበዋል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዘለዓለም ሙላቱ (ዶ/ር) አስረድተዋል፡፡

የመማር ማስተማሩን ሒደት ከፍተኛ ጫና ውስጥ የሚከቱና በተማሪዎች ሥነ ምግባር ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ የሚያሳድሩ ድርጊቶች መበራከታቸውን ዘለዓለም (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡

እነዚህን እኩይ ተግባራት በተለይ በትምህርት ቤት ዙሪያ በሚፈጽሙ አካላት ላይ ተገቢው ዕርምጃ ሊወሰድባቸው ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ባለፉት ዘጠኝ ወራት ብቻ ተማሪዎችን ማዕከል አድርገው በተከፈቱና የመማር ማስተማር ሒደቱ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ባሳደሩ 2,662 የተለያዩ የንግድ ቤቶች ላይ ዕርምጃ መወሰዱን፣ የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን አስታውቋል፡፡

በመድረኩ ላይ በቀረበ ጥናታዊ ጽሑፍ ተማሪዎች በመፀዳጃ ቤቶች ሲጋራ ሲያጨሱ፣ እንዲሁም በቦርሳቸው ውስጥ ሲጋራ ይዘው መገኘታቸው ተነግሯል፡፡

በትምህርት ቢሮና በሚመለከታቸው አካላት ብዙ ጥረት ቢደረግም የተፈለገው ውጤት ሊመጣ እንዳልቻሉና ችግሩ መባባሱን ተወያዮች ገልጸዋል፡፡

በአንዳንድ ትልልቅ ትምህርት ቤቶች ግቢ ውስጥ ሐሺሽ ተዘርቶ በቅሎ መገኘቱን ተናግረዋል፡፡ ይህንን ችግር በቀላሉ ልናልፈው አይገባም ሲሉ ከቂርቆስ ክፍለ ከተማ መምህራን ማኅበር የመጡ ተሳታፊ አሳስበዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በአዲስ አበባ በድምቀት ተከበረ

የአዛርባጃን ኤምባሲ  የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በትላንትናው ዕለት አከበረ። ሰኞ...

የመንግሥትና የሃይማኖት ልዩነት መርህ በኢትዮጵያ

እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገሮች የሃይማኖት ተቋማት አዎንታዊ ሚና የጎላ...

ሐበሻ ቢራ ባለፈው በጀት ዓመት 310 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ

የአንድ አክሲዮን ሽያጭ ዋጋ 2,900 ብር እንዲሆን ተወስኗል የሐበሻ ቢራ...