Friday, June 2, 2023
- Advertisment -
- Advertisment -

ጠንካራና አስተማማኝ ተቋማት በሌሉበት ውጤት መጠበቅ አይቻልም!

በኢትዮጵያ ዘርፈ ብዙ ብሔራዊ ጉዳዮች ላይ የሚስተዋሉ መዛነፎችና አለመግባባቶች ዋነኛ ምክንያታቸው፣ ከበፊት ጀምሮ እስካሁን ድረስ ጠንካራና አስተማማኝ ተቋማትን ለመገንባት አለመቻል ነው፡፡ በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካ፣ በፀጥታ፣ በፍትሕ፣ በዲፕሎማሲና በሌሎች መስኮች ጠንካራ ተቋማትን ገንብቶ ብቃት ባላቸው ሰዎች እንዲመሩ ማድረግ የግድ መሆን አለበት፡፡ ተቋማት ባልተጠናከሩበትና ብቁ አመራሮችና ባለሙያዎች በሌሉበት ኢኮኖሚም ሆነ ሌላው ዘርፍ ውጤት አይገኝበትም፡፡ ግለሰቦች በአገር አመራርም ሆነ በተለያዩ የሥራ መስኮች የሚኖራቸው አስተዋፅኦ ከፍተኛ እንደሆነ ቢታመንም፣ ጠንካራና አስተማማኝ ተቋማት ከሌሉ የእነሱ ፋይዳ እዚህ ግባ የሚባል አይሆንም፡፡ የግለሰቦች ተክለ ሰብዕና ላይ እየተተኮረ ተቋማት ሲኮስሱ ኢትዮጵያ የአምባገነንነትና የሕገወጥነት መፈንጫ ትሆናለች፡፡ ሕግና ሥርዓት ተከብሮ በሰላም መንቀሳቀስ የሚቻለው ከግለሰቦች በላይ ተቋማት ጠንካራ ሲሆኑ ነው፡፡ ግጭት ተወግዶ በሁሉም የፖለቲካ ኃይሎችና በማኅበረሰቦች መካከል ሕጋዊና ሰላማዊ ግንኙነት የሚኖረው፣ ተቋማት ተጠናክረው በሥርዓት ለመኖር የሚያስችሉ መደላድሎች ሲመቻቹ ነው፡፡ ከማንም ተፅዕኖ ነፃና አስተማማኝ ጠንካራ ተቋማት ሳይገነቡ፣ ሰላምም ሆነ ዕድገት ይመጣሉ ብሎ ማሰብ አይቻልም፡፡

በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ቀውስ ካስከተሉ ምክንያቶች መካከል በከፍተኛ ደረጃ የሚጠቀሰው፣ በሰሜን ኢትዮጵያ ለሁለት ዓመታት ያህል የተካሄደው አውዳሚ ጦርነት ነው፡፡ በዚህ አስከፊ ጦርነት ከደረሰው ሰብዓዊ ቀውስ በተጨማሪ ከፍተኛ መጠን ያለው የአገር ሀብት ወድሟል፡፡ ለልማት መዋል የሚገባው ሀብት ለጦርነት ማካሄጃ በመሆኑ ምክንያት፣ ብዙኃኑን ሕዝብ እንደ ሰደድ እሳት በቁጥጥር ሥር መዋል ላልቻለው የኑሮ ውድነት ዳርጓል፡፡ ከሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ቀጥሎ በየአካባቢው የሚከሰቱ ግጭቶችና ጥቃቶች የዜጎችን እንቅስቃሴ በመገደባቸው፣ ምርቶችን ከቦታ ወደ ቦታ ማንቀሳቀስ አልተቻለም፡፡ በዚህም ምክንያት ኢኮኖሚው በብርቱ እየተጎዳ ነው፡፡ ኢኮኖሚውን ከዚህ ሁሉ ውጥንቅጥ ውስጥ ማውጣት የሚቻለው ጠንካራዊ ተቋማዊ ቁመናና አቅም ማዳበር ሲቻል ነው፡፡ ሥራ አጥነትን በከፍተኛ መጠን ለመቀነስ፣ ምርታማነትን ለመጨመርና የዋጋ ግሽበትን ወደ ነጠላ አኃዝ ለመቀየር ጠንካራ ተቋማት ያስፈልጋሉ፡፡ ዜጎች በከፍተኛ የኑሮ ችግር ውስጥ ሆነው አላስፈላጊ ፕሮጀክቶች ላይ ማተኮር ተገቢም ሕጋዊም አይደለም፡፡ ጠንካራ ተቋማት ቢኖሩ ኖሮ ቅድሚያ ለሚሰጣቸው አንገብጋቢ ፕሮጀክቶች ትኩረት ይሰጥ እንደነበር ይታወቅ፡፡

ኢኮኖሚው ከገባበት ቀውስ ውስጥ የሚላቀቀው የዓለም ባንክና አይኤምኤፍ፣ በእጅ ጥምዘዛ የሚፈልጉትን በማስፈጸም በሚለቁት ብድርና ዕርዳታ እንዳልሆነ ሊታወቅ ይገባል፡፡ በኢትዮጵያ በተለያዩ ጠንካራ ተቋማዊ አደረጃጀቶች በጥናት ላይ የተመሠረቱ አሠራሮችን ተግባራዊ ማድረግ ከተቻለ፣ መዘዘኛ ፖሊሲዎችንና ስትራቴጂዎችን ተገዶ በማውጣት ከውጭ ከሚገኝ ድጋፍ ላይ አይተኮርም ነበር፡፡ የጠንካራ ተቋማት መኖር በሁሉም የአገሪቱ ክልሎች ውስጥ ጥያቄ አለን ከሚሉ ወገኖች ጋር ሰላማዊ ግንኙነት በመመሥረት ለመነጋገርና ለመደራደር፣ ዕልቂትና ውድመት የሚያስከትሉ ግጭቶችን እንዳይቀሰቀሱ ለማድረግ ይረዳል፡፡ በሕጋዊና በሰላማዊ መንገድ መንቀሳቀስ ስለማያቅት የጥፋት ጎዳና ውስጥ ከመግባት ይከላከላል፡፡ ለብሔራዊ መግባባትና ዕርቅ ከፍተኛ ትኩረት ይሰጣል፡፡ አለመግባባቶች ሲያጋጥሙ በኃይል ለመፍታት የሚኬድበት ርቀት እንደማያዋጣ፣ የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በሚገባ አሳይቷል፡፡ በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች ውስጥ ለአገር ህልውና ተግዳሮት እየሆኑ ያሉ ችግሮች በፍጥነት በሰላማዊ መንገድ ይፈቱ፡፡ በሁለቱ ክልሎች ውስጥ ያሉ ዜጎች ዕፎይታ አግኝተው ፊታቸውን ወደ ልማት እንዲያዞሩም ተቋማት ብቁ ሆነው ይጠናከሩ፡፡

ሰብዓዊ መብቶችን ማስከበርና የሕግ የበላይነትን ማረጋገጥ ጉዳይ ጊዜ ሊሰጠው የማይገባ ተግባር ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ በርካታ ዜጎች ሰብዓዊ መብቶቻቸው ተገፈው ለእንግልት መዳረጋቸውን በከፍተኛ ጩኸት እያሰሙ ነው፡፡ በታጣቂዎች ጥቃት በማንነታቸው እየተለዩ ከሚሳደዱትና ከሚፈናቀሉት ጀምሮ፣ ለዓመታት የኖሩባቸው ጎጆዎቻቸው እየፈረሱባቸው ሜዳ ላይ የወደቁ ወገኖች እሪታ ከአድማስ እስከ አድማስ እያስተጋባ ነው፡፡ በሕግ የተረጋገጡላቸው መብቶች እየተደፈጠጡ አገልግሎት የሚነፈጉ ወገኖች ዕንባቸውን እያዘሩ ነው፡፡ ጉቦ ካልከፈሉ በስተቀር መስተንግዶ ማግኘት የተሳናቸው ዜጎች አቤቱታችንን የሚሰማን አጣን እያሉ ነው፡፡ ሕግ ባለበት አገር ሕገወጥነት ከመጠን በላይ ሲንሰራፋና ዜጎች ተስፋ ሲቆርጡ፣ የመንግሥት ዋነኛ ኃላፊነቱ ሕግና ሥርዓት መኖሩን ማረጋገጥ ነው፡፡ ነገር ግን ለሕግና ለሥርዓት ደንታ በሌላቸው ሹማምንት ምክንያት ‹‹ጆሮ ዳባ ልበስ›› ማለት የተመረጠ ይመስላል፡፡ ገዥው ፓርቲ ብልፅግናም ሆነ የሚመራው መንግሥት ጠንካራ ተቋማት እንዲገነቡ ፈቃደኛ ካልሆኑ፣ ሕገወጦች የበላይነቱን ይይዙና ጦሱ ለራሳቸው ጭምር ይተርፋል፡፡ በቅርቡ በቢሾፍቱ ከተማ ፖሊስ ጣቢያና በሌሎች አካባቢዎች የተፈጸሙ ጥቃቶች የችግሩ ማሳያ ናቸው፡፡

በአገራዊ የምክክር ኮሚሽን አማካይነት ይጀመራል የተባለው ብሔራዊ ውይይት በፍጥነት ተጀምሮ፣ በዘርፈ ብዙ ችግሮች ላይ መምከርና መግባባት ላይ የሚያደርሱ ዘዴዎችን መፈለግ የግድ የሚልበት ጊዜ ላይ ነን፡፡ ብሔራዊ ምክክሩ እርስ በርስ ለመደማመጥና መተማመን ለመፍጠር የሚረዳ ከመሆኑም በላይ፣ ችግሮችን ለመፍታት የሚያግዙ መፍትሔዎችን በጋራ ለማፈላለግም መሠረት ይጥላል፡፡ ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች እንዲከበሩ፣ ሁሉንም ወገኖች የሚያሳትፍ የፖለቲካ ምኅዳር እንዲፈጠር፣ ከሕጋዊና ከሰላማዊ አማራጮች ውጪ የጉልበተኝነት ባህሪ እንዲወገድ፣ ሴረኝነትና ጉልበተኝነት ቦታ እንዳይኖራቸው፣ በዝርፊያና በማጭበርበር መክበር እንዲቀር፣ ብልሹ አሠራሮች እንዲጠፉ፣ አድሎአዊነትና ኢፍትሐዊነት እንዳይኖሩ፣ በብሔርና በጥቅም እየተቧደኑ መዝረፍ እንዲያበቃ፣ ለሥነ ምግባርና ለሞራል ፀር የሆኑ አሳፋሪ ድርጊቶች እንዲናቁና በአጠቃላይ በመከባበርና በመተባበር መንፈስ አብሮ ለመሥራት የሚያስችሉ ጠንካራ ተቋማት ለመፍጠር ይረዳል፡፡ በዚህ መሠረት ተባብሮ ለአገር መሥራት የሚያስችል ሁኔታ ሲኖር ሕገ መንግሥቱን ለማሻሻል፣ አሳታፊና ፍትሐዊ ሥርዓት ለማደላደል ይቻላል፡፡ ጠንካራና ነፃ ተቋማት ሳይኖሩ ሰላም ማስፈን አይቻልም፣ አገር መገንባትም አይታሰብም፡፡

ሁሉንም ወገኖች የሚያግባቡ ጠንካራ ተቋማት መገንባት ከተቻለ የኢኮኖሚ ዕድገት ማምጣት አያቅትም፡፡ የጋራ ተጠቃሚነት ያለው የኢኮኖሚ ዕድገት ሲኖር የፖለቲካ ቀውስን ማስቆም ይቻላል፡፡ በትምህርት፣ በጤና፣ በግብርና፣ በኢንዱስትሪ፣ በተለያዩ መሠረተ ልማቶችና በመሳሰሉት የጋራ ተሳትፎና ተጠቃሚነት የሚኖርበት ሥርዓት ለማስፈን ጠንካራ ተቋማት ያስፈልጋሉ፡፡ የአጠቃላይ ሕዝቡን የኑሮ ሁኔታ በማሳደግ ከድህነት የሚያላቅቁ አዋጭ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች በመዘርጋት፣ የፖለቲካ ውጥረቶችንና አለመረጋጋቶችን ማስወገድ ይቻላል፡፡ ከእነዚህ የመፍትሔ ማመላከቻዎች በተጨማሪ ለሐሳብ ልዕልና ትኩረት ያስፈልጋል፡፡ እየተደመጥን አይደለም የሚሉ ወገኖች ሐሳቦቻቸውን በግልጽና በነፃነት ማቅረብ አለባቸው፡፡ ከመደበኛ መንግሥታዊ ተቋማት ባልተናነሰም ዴሞክራሲያዊ ተቋማት ሲጠናከሩ፣ የሥልጣን ሉዓላዊ ባለቤት የሆነው ሕዝብ መብቱ ይከበራል፡፡ በዚህ መንፈስ በጋራ ሲሠራ የፖለቲካውም ሆነ የኢኮኖሚው ዕድገት አስተማማኝ ይሆናል፡፡ እነዚህን ሁሉ መልካም ነገሮች በምልዓት ለማግኘት ግን ለነፃ፣ አስተማማኝና ጠንካራ ተቋማት ግንባታ ትኩረት መስጠት የግድ መሆን አለበት!

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅን የሚተካ ረቂቅ ተዘጋጀ

ከቫት ነፃ የነበረው የኤሌክትሪክ ኃይል ገደብ ተቀመጠለት የገንዘብ ሚኒስቴር ከሃያ...

አገር የሚገቡ የግል ዕቃዎችን በሚገድበው መመርያ ምክንያት በርካታ ንብረቶች በጉምሩክ መያዛቸው ተገለጸ

በአየር መንገድ ተጓዦች ወደ አገር የሚገቡትን የግል መገልገያ ዕቃዎች...

ብሔራዊ ባንክ ለጥቃቅንና አነስተኛ ብድሮች ዋስትና መስጠት ሊጀምር ነው

ኢንተርፕራይዞችን ብቻ የሚያገለግል የፋይናንስ ማዕከል ሥራ ጀመረ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ...

አዋሽ ባንክ ለሁሉም ኅብረተሰብ የብድር አገልግሎት የሚያስገኙ ሁለት ክሬዲት ካርዶች ይፋ አደረገ

አዋሽ ባንክ ለሁሉም የኅብረተሰብ ክፍሎች በዘመናዊ መንገድ ብድር ማስገኘት...
- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በአዲስ አበባ በድምቀት ተከበረ

የአዛርባጃን ኤምባሲ  የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በትላንትናው ዕለት አከበረ። ሰኞ...

የመንግሥትና የሃይማኖት ልዩነት መርህ በኢትዮጵያ

እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገሮች የሃይማኖት ተቋማት አዎንታዊ ሚና የጎላ...

ሐበሻ ቢራ ባለፈው በጀት ዓመት 310 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ

የአንድ አክሲዮን ሽያጭ ዋጋ 2,900 ብር እንዲሆን ተወስኗል የሐበሻ ቢራ...

የባንኮች ብድር አሰጣጥ ፍትሐዊና ብዙኃኑን ያማከለ እንዲሆን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አሳሰበ

ባንኮች የብድር አገልግሎታቸውን በተቻለ መጠን ፍትሐዊ፣ የብዙኃኑን ተጠቃሚነት ያማከለና...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

የፖለቲካ ምኅዳሩ መላሸቅ ለአገር ህልውና ጠንቅ እየሆነ ነው!

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ምኅዳር ከዕለት ወደ ዕለት የቁልቁለት ጉዞውን አባብሶ እየቀጠለ ነው፡፡ በፖለቲካ ፓርቲዎች የእርስ በርስ ግንኙነትም ሆነ በውስጠ ፓርቲ ዴሞክራሲ የሚታየው መስተጋብር፣ ውል አልባና...

የመኸር እርሻ ተዛብቶ ቀውስ እንዳይከሰት ጥንቃቄ ይደረግ!

ክረምቱ እየተቃረበ ነው፡፡ የክረምት መግቢያ ደግሞ ዋናው የመኸር እርሻ የሚጀመርበት ጊዜ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ከእርሻው ክፍለ ኢኮኖሚ 70 በመቶ ያህሉን የሰብል ምርት የምታገኘው በመኸር እርሻ...

የሕዝቡን ኑሮ ማቅለል እንጂ ማክበድ ተገቢ አይደለም!

መንግሥት አገር ሲያስተዳድር ለበርካታ ወጪዎቹ ገንዘብ ስለሚያስፈልጉት አስተማማኝ የገቢ ምንጮች ሊኖሩት ይገባል፡፡ በጀት ሲይዝም ሆነ ወጪዎቹን ሲያቅድ ጠንቃቃ መሆን ይኖርበታል፡፡ ወቅቱ ለመጪው ዓመት በጀት...