Thursday, June 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትዋሊያዎቹ አዲስ የበረኛ አሠልጣኝ አገኙ

ዋሊያዎቹ አዲስ የበረኛ አሠልጣኝ አገኙ

ቀን:

ለአይቮሪኮስቱ የአፍሪካ ዋንጫ፣ የምድብ የማጣሪያ ጨዋታውን እያደረገ ለሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ዋሊያዎቹ)፣ አሠልጣኝ ውብሸት ደሳለኝን የበረኛ አሠልጣኝ አድርጎ መሾሙን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ፡፡

ፌዴሬሽኑ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ እንደገለጸው፣ በቅርቡ በተሰናበቱት የበረኛ አሠልጣኝ ደሳለኝ ገብረ ጊዮርጊስ ምትክ የተሾሙት አሠልጣኝ ውብሸት የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ የግብ ጠባቂዎች አሠልጣኝ ናቸው፡፡

ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ቡድኑን ላለፉት ሁለት ዓመታት ሲመሩ ከቆዩት ከዋና አሠልጣኝ ውበቱ አባተ ጋር ውሉን ማቋረጡን ተከትሎ፣ በጊዜያዊ ዋና አሠልጣኝነት እንዲመሩ የቴክኒክ ዳይሬክተሩን ኢንስትራክተር ዳንኤል ገብረማርያምና በምክትልነት የባህር ዳር ከተማ አሠልጣኝ ደግአረገ ይግዛው  መሾሙ ይታወሳል፡፡

ብሔራዊ ቡድኑ በአይቮሪኮስቱ የአፍሪካ ዋንጫ የምድቡን ሦስተኛና አራተኛ ጨዋታ አድርጎ በሁለቱም መረታቱን ተከትሎ ዋና አሠልጣኙን መሰናበቱ ይታወሳል። 

 ዋሊያዎቹ አምስተኛውን የምድብ ጨዋታቸውን ሰኔ 13 ቀን 2015 ዓ.ም. የሚያከናውኑት በሞዛምቢክ ሲሆን፣ የመጨረሻውንና ስድስተኛውን ግጥሚያ ካይሮ ላይ ከፈርዖኖች (ግብፅ) ጋር በመስከረም 2016 ዓ.ም. የሚደርጉ ይሆናል፡፡

የዋሊያዎቹ የምድብ ጨዋታቸው ገጽታ

የ2023 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በምድብ መ ከኢትዮጵያ (ዋሊያዎቹ) ጋር ያሉት ግብፅ፣ ጊኒና  ማላዊ ናቸው፡፡ ቡድኖቹ የማጣርያ ጨዋታቸውን ግንቦት 25 ቀን 2014 ዓ.ም. የጀመሩ ሲሆን፣ የሚያጠናቅቁት በመስከረም 2016 ዓ.ም. ይሆናል፡፡ እስካሁን ባደረጉት የደርሶ መልስ ጨዋታ ኢትዮጵያ ካደረገቻቸው አራት ጨዋታዎች ያሸነፈችው አንድ ግብፅን ብቻ ነው፡፡ በ3 ነጥብ በ2 የግብ ዕዳ የመጨረሻውን ደረጃ ይዛለች፡፡

ኢትዮጵያ በአራቱ ጨዋታዎች 7 ጎሎች ተቆጥሮባት፣ ያስቆጠረችው ግን 5 ነው፡፡ ግቦቹን ያሰቆጠሩት ሽመልስ በቀለ፣ ዳዋ ሆጤሳ፣ ኪቲካ ጀማ፣ ከንአን ማርክነህና አቡበከር ናስር ናቸው፡፡

ግብፅና ጊኒ ተመሳሳይ ነጥብ 9 ይዘው በግብ ክፍያ ግብፅ (5) በመያዟና ጊኒን በ2 በመብለጧ መሪነቱን ጨብጣለች፡፡ ማላዊ ከኢትዮጵያ ጋር እኩል 3 ነጥብና 6 የግብ ዕዳ  ቢኖራትም 3ኛነትን የያዘችው ኢትዮጵያን በመርታቷ ነው፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በአዲስ አበባ በድምቀት ተከበረ

የአዛርባጃን ኤምባሲ  የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በትላንትናው ዕለት አከበረ። ሰኞ...

የመንግሥትና የሃይማኖት ልዩነት መርህ በኢትዮጵያ

እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገሮች የሃይማኖት ተቋማት አዎንታዊ ሚና የጎላ...

ሐበሻ ቢራ ባለፈው በጀት ዓመት 310 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ

የአንድ አክሲዮን ሽያጭ ዋጋ 2,900 ብር እንዲሆን ተወስኗል የሐበሻ ቢራ...