Wednesday, March 19, 2025
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትበፉክክር በቀጠለው ቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሦስት ክለቦች ተፋጠዋል

በፉክክር በቀጠለው ቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሦስት ክለቦች ተፋጠዋል

ቀን:

spot_img

ቅዱስ ጊዮርጊስ ነጥቡን በአምስት አስፍቷል

የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ የአምስት ሳምንታት ዕድሜ ብቻ ቀርቶታል፡፡ በ2015 ዓ.ም. በሊጉ እየተሳተፉ የሚገኙ ክለቦች ከፍተኛ ፉክክር እያደረጉ ነው፡፡ በውድድር ዘመኑ ጥሩ ጊዜ ማሳለፍ ያልቻሉ ክለቦች ከወዲሁ መውረዳቸውን ሲያረጋግጡ የሊጉን የደረጃ ሰንጠረዥ እየመራ የሚገኘው ቅዱስ ጊዮርጊስ ሁለተኛውን የባህር ዳር ከተማን በአምስት ነጥብ ልዩነት እየመራው ይገኛል፡፡

በ25ኛ ሳምንት የሊጉ መርሐ ግብር ሃዲያ ሆሳዕናን የገጠመው ባህር ዳር ከተማ 2ለ1 መረታቱን ተከትሎ ከመሪው ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ያለው ነጥብ በአምስት አስፍቶታል፡፡

በዚህኛው ሳምንት ቅዱስ ጊዮርጊስ ወላይታ ድቻን ገጥሞ 2ለ1 በማሸነፍ የዋንጫ ግስጋሴውን በመያያዙ ፈረሰኞቹ የሊጉን 16ኛ ዋንጫ ለማንሳት ዕድላቸውን ማስፋት ችለዋል፡፡ በአንፃሩ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር አንገት ለአንገት ተናንቆ ሲጓዝ የነበረው ባህር ዳር ከተማ 50 ነጥብ ሰብስቦ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡

ዘንድሮ ፕሪሚየር ሊጉን የተቀላቀለው የኢትዮጵያ መድን ሌላኛው የውድድሩ ድምቀት ሆኖ ቀጥሏል፡፡ መድን 24 ጨዋታዎችን አከናውኖ (ይኼ ዘገባ እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ) 44 ነጥቦችን በመሰብሰብ ሦስተኛ ደረጃን፣ ፋሲል ከነማ 25 ጨዋታ አድርጎ በ37 ነጥብ አራተኛ ደረጃን ይዘዋል፡፡

በመሪውና በተከታዩ መካከል የአምስት ነጥብ ልዩነት ቢኖርም ዋንጫውን ለማንሳት ከፈረሰኞቹ በተጨማሪ ባህር ዳርና መድን ዕድል አላቸው፡፡

በሌላ በኩል ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ፕሪሚየር ሊግ የገባው ለገጣፎ ለገዳዲ እግር ኳስ ክለብ በጠዋቱ መውረዱን አረጋግጧል፡፡ ክለቡ አምስት ጨዋታዎች እየቀሩት 12 ነጥብ ብቻ መያዙን ተከትሎ ወደ ታችኛው ሊግ መውረዱን አረጋግጧል፡፡

ክለቡ ቀሪ አምስት ጨዋታዎችን በማሸነፍ 26 ነጥብ ለመሰብሰብ ቢችልም ከመውረድ አይታገደውም፡፡ ሌላኛው በወራጅ ቀጣና ላይ የሚገኘው አርባ ምንጭ ከተማ ከአዳማ ከተማ ጋር ያለምንም ግብ መለያየቱን ተከትሎ የመውረድ ሥጋት አጋጥሞታል፡፡ ክለቡ በ2015 ዓ.ም. ከኤሌክትሪክና መድን ጋር ወደ ፕሪሚየር ሊግ ማደጉ ይታወሳል፡፡

አርባ ምንጭ ከተማ ካደረጋቸው 25 ጨዋታዎች አራቱን አሸንፎ በ14 አቻ ሲወጣ በሰባት ተረትቶ 26 ነጥብ በመሰብሰብ 14ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡ ሁለተኛው መውረዱን ያረጋገጠው ኤሌክትሪክ ሲሆን 24 ጨዋታዎችን በማድረግ 18 የግብ ዕዳ ይዞና 11 ነጥቦችን ብቻ ሰብስቦ የመጨረሻውን 16ኛ ደረጃ ይዟል፡፡

የሊጉ መርሐ ግብር በባህር ዳር፣ ድሬዳዋ፣ አዳማና ሐዋሳ ከተሞች ላይ ሲከናወን የቆየ ሲሆን፣ 29ኛ እና 30ኛ ሳምንት ደግሞ በአዳማ እንደሚከናወን የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር አስታውቋል፡፡

በሌላ በኩል በከፍተኛ ሊግ ሲሳተፉ የነበሩት ሦስት ክለቦች ወደ 2016 ዓ.ም. ቤቲኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ማደጋቸውን አረጋግጠዋል፡፡

በከፍተኛ ሊግ ምድብ ለ2015 ዓ.ም. አሸናፊ ሻሸመኔ ከተማ እግር ኳስ ክለብ፣ በምድብ ሀ ንግድ ባንክ እንዲሁም በምድብ ሐ አሸናፊ መሆን የቻለው ሀምበሪቾ ዱራሜ የ2016 ዓ.ም. ቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ማደጋቸውን ያረጋገጡ ክለቦች ናቸው፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

‹‹እልህ ምላጭ ያስውጣል›› ከሚል የፖለቲካ ባላንጣነት የመላቀቅ ፈተና

በዝማም ታረቀኝ ትውልድ የታሪክ ባለ ዕዳ ነው፡፡ የአሁኑ ትውልድም በአገራችን...

ኑሮና ብልኃቱ አልሳካ ያለው የጉርስና የመጠለያ ነገር

በገነት ዓለሙ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የኑሮ ውድነት የጠያቂ መብዛትንና የሸቀጥ...

ወደ ጦርነት የሚወስዱ መንገዶች በፍጥነት ይዘጋጉ!

ከአንዱ ግጭት ወደ ሌላው የሚደረገውን ጥድፊያ በቅጡ ማስቆም ባለመቻሉ...

የነገው ሰው እንዴት ይታነፅ?

በሳህሉ ባዬ በዚህ መጣጥፍ የምንመለከተው ዓብይ ነጥብ ጨዋታ በሕፃናት አስተዳደግ...
error: