Friday, June 2, 2023
- Advertisment -
- Advertisment -

[ክቡር ሚኒስትሩ የቢሮ ስልካቸው ጠራ። ደዋዩ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ኃላፊ እንደሆኑ ሲነገራቸው የስልኩን መነጋገሪያ ተቀበሉ]

 • ሃሎ፡፡
 • እንዴት አሉ ክቡር ሚኒስትር።
 • ደህና ነኝ። አንተስ? አስተዳደሩስ?
 • ሕጋዊ ሰውነታችን ተነጥቆ እንዴት ማስተዳደር እንችላለን ክቡር ሚኒስትር?
 • ለዚህ ጉዳይ እንደደወልክ ገምቻለሁ።
 • ደብዳቤም እኮ ልከናል ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • አዎ። ሁለት ደብዳቤዎች ደርሰውኛል። አንድ ግን ያስገረመኝ አለ።
 • ምንድነው ክቡር ሚኒስትር?
 • ለቦርዱ ጥያቄ ያቀረባችሁት መቼ ነው?
 • ግንቦት 4 ነው።
 • ቦርዱ ደግሞ በማግስቱ ቅዳሜ ግንቦት 5 ውሳኔውን ይፋ አደረገ አይለም?
 • ልክ ነው።
 • ያው ግንቦት 6 ቀን ደግሞ እሑድ መሆኑ ይታወቃል።
 • አዎ።
 • ታዲያ የቦርዱ ውሳኔ ዘግይቶ ግንቦት 7 ነው የደረሰን እንዴት ይባላል? ወይስ ምጸት መሆኑ ነው?
 • የምን ምጸት ክቡር ሚኒስትር?
 • በዕለቱ አጠናቀቁት ማለታችሁ ይሆን?
 • ምኑን ነው የሚያጠናቅቁት?
 • ግንቦት 7 የጀመሩትን!
 • እሱን ደብዳቤ የጊዜያዊ አስተዳደሩ አይደለም።
 • እና የማን ነው?
 • የፓርቲያችን ነው።
 • ነው እንዴ?
 • አዎ። አሁን ወደ ዋናው ጉዳይ መግባት እችላለሁ ክቡር ሚኒስትር?
 • ለዚህ ጉዳይ አልነበር እንዴ የደወልከው?
 • ቢሆንም የግንቦት ወር ቀናቶች ጉዳዬ አይደሉም።
 • በል እሺ ወደ ጉዳይህ ግባ።
 • ክቡር ሚኒስትር ይህ ጉዳይ መፈታት አለበት። እርስዎም ጣልቃ መግባት ያለብዎት ይመስለኛል።
 • እኔማ እንዴት ጣልቃ እገባለሁ?
 • ምክንያቱም ይህ ጉዳይ ካልተስተካከለ በሰላም ስምምነቱ ላይ ተፅዕኖ ያመጣል። ስለዚህ ጣልቃ ገብተው መፍትሔ ሊሰጡት ይገባል።
 • በሕግ መሠረት የሚሠራ ገለልተኛ ተቋም እኮ ነው? እንዴት ብዬ ጣልቃ እገባለሁ?
 • የሕግ መኖርና በሕግ መሥራት ያስፈለገበት መሠረታዊ ዓላማ ሰላም ለማስፈን እንጂ ሰላምን ለመጻረር አይደለም። ይህንን እንደሚገነዘቡ እረዳለሁ ክቡር ሚኒስትር።
 • ቢሆንም ይህ ጉዳይ በሕግ መሠረት መፍትሔ ማግኘት የሚችል ቀላል ጉዳይ እንጂ እናንተ እንደምትሉት ዓይነት ክብደት የለውም።
 • ከባድ ነው እንጂ ክቡር ሚኒስትር። የሳለም ስምምነቱን የፈረመው ፓርቲ ህልውና ጠፍቶ እንዴት ወደፊት መራመድ እንችላለን?
 • እኔ እንደተረዳሁት ፓርቲው ህልውናው ሙሉ በሙሉ ሊያጣ የሚችል አይመስልኝም።
 • እርስዎ ጣልቃ ካልገቡ በቀር እንዴት ይሆናል?
 • በሕጉ መሠረት እንደ አዲስ ምዝገባ ማድረግ ይቻላል።
 • ይህንን እንደሚሉ እርግጠኛ ነበርኩ።
 • እንዴት?
 • መጥፎ ህልም አባኖኝ ነው ወደ እርስዎ ለመደወል የወሰንኩት።
 • ህልም?
 • አዎ። እንደ አዲስ ምዝገባ ለማድረግ ጥያቄ አቅርበን የተሰጠንን ምላሽ ሰምቼ ነው የባነንኩት።
 • ምላሹ ምን ነበር?
 • ለምዝገባ ያቀረባችሁት ስም በሌላ ፓርቲ ተይዟል የሚል ነበር።
 • የእናንተ ፓርቲ ስም ተይዞ?
 • አዎ!
 • ማነው የያዘው?
 • ወራሾች ነን የሚሉ ናቸው።
 • አይ አንተ፡፡
 • እንዴት?
 • ህልም አይደለማ ያባነነህ?
 • ታዲያ ምንድነው?
 • ትዝታ ነው፡፡
 • የምን ትዝታ?
 • የቅንጅት!

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅን የሚተካ ረቂቅ ተዘጋጀ

ከቫት ነፃ የነበረው የኤሌክትሪክ ኃይል ገደብ ተቀመጠለት የገንዘብ ሚኒስቴር ከሃያ...

አገር የሚገቡ የግል ዕቃዎችን በሚገድበው መመርያ ምክንያት በርካታ ንብረቶች በጉምሩክ መያዛቸው ተገለጸ

በአየር መንገድ ተጓዦች ወደ አገር የሚገቡትን የግል መገልገያ ዕቃዎች...

ብሔራዊ ባንክ ለጥቃቅንና አነስተኛ ብድሮች ዋስትና መስጠት ሊጀምር ነው

ኢንተርፕራይዞችን ብቻ የሚያገለግል የፋይናንስ ማዕከል ሥራ ጀመረ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ...

አዋሽ ባንክ ለሁሉም ኅብረተሰብ የብድር አገልግሎት የሚያስገኙ ሁለት ክሬዲት ካርዶች ይፋ አደረገ

አዋሽ ባንክ ለሁሉም የኅብረተሰብ ክፍሎች በዘመናዊ መንገድ ብድር ማስገኘት...
- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በአዲስ አበባ በድምቀት ተከበረ

የአዛርባጃን ኤምባሲ  የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በትላንትናው ዕለት አከበረ። ሰኞ...

የመንግሥትና የሃይማኖት ልዩነት መርህ በኢትዮጵያ

እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገሮች የሃይማኖት ተቋማት አዎንታዊ ሚና የጎላ...

ሐበሻ ቢራ ባለፈው በጀት ዓመት 310 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ

የአንድ አክሲዮን ሽያጭ ዋጋ 2,900 ብር እንዲሆን ተወስኗል የሐበሻ ቢራ...

የባንኮች ብድር አሰጣጥ ፍትሐዊና ብዙኃኑን ያማከለ እንዲሆን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አሳሰበ

ባንኮች የብድር አገልግሎታቸውን በተቻለ መጠን ፍትሐዊ፣ የብዙኃኑን ተጠቃሚነት ያማከለና...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[ክቡር ሚኒስትሩ አምሽተው ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው ‹‹ፈተናዎችን ወደ ዕድል በመቀየር ሕዝባችንን እናሻግራለን›› የሚለውን የቴሌቪዥን ዜና ተመልክተው ለብቻቸው ሲስቁ አገኟቸው]

ስልክ እያወራሽ ነበር እንዴ? ኧረ በጭራሽ... ምነው? ታዲያ ምንድነው ብቻሽን የሚያስቅሽ? አይ... በቴሌቪዥኑ የሚቀርበው ነገር ነዋ። ምንድነው? ድሮ ድሮ ዜና ለመስማት ነበር ቴሌቪዥን የምንከፍተው፡፡ አሁንስ? አሁንማ ቀልዱን ተያይዘውታል... አንተ ግን በደህናህ...

[ክቡር ሚኒስትሩ አየር መንገዱ ወጪ ቆጣቢ የሥራ እንቅስቃሴ በማድረግ የውጭ ምንዛሪ ግኝቱን በሚያሳድግበት ሁኔታ ላይ ከተቋሙ ኃላፊ ጋር እየተወያዩ ነው]

ቀደም ብዬ እንደገለጽኩት ትልቁ ወጪያችን ለነዳጅ ግዥ የሚውለው ነው። ክቡርነትዎ እንደሚገነዘቡት የዩክሬን ጦርነት የዓለም የነዳጅ ዋጋ በእጅጉ አሻቅቧል። ቢሆንም አገሪቱ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ችግር ውስጥ...

[ክቡር ሚኒስትሩ የነዳጅ ግብይት በዲጂታል ክፍያ መንገድ ብቻ እንዲፈጸም የተላለፈውን ውሳኔ አተገባበር ላይ ስለተነሱ ቅሬታዎች ከባልደረባቸው ጋር እየተወያዩ ነው]

ክቡር ሚኒስትር አተገባበሩ ጥሩ ቢሆንም፣ ከፍተኛ ወቀሳ እየደረሰብን ነው። ዲጂታል የግብይት ሥርዓቱን ለማስፋፋት በመጣራችን መመስገን ሲገባን እንዴት እንወቀሳለን? የሚገርመው በዲጂታል ክፍያ ላይ የተሰማሩ ኩባንያዎች ናቸው በዋነኛነት...