Monday, September 25, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ለውጥ ቅድመ ምላሾች የምትዘጋጅበት አቅም ልትፈጥር ይገባል ተባለ

ኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ለውጥ ቅድመ ምላሾች የምትዘጋጅበት አቅም ልትፈጥር ይገባል ተባለ

ቀን:

ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን አስመልክቶ ከምትሠራቸው የቅድመ ማስጠንቀቂያ ሥራዎች ባሻገር፣ ለቅድመ መከላከል ምላሾች የምትዘጋጅበትን አቅም ልትፈጥር እንደሚገባ ተገለጸ፡፡

ይህ የተገለጸው የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ከግብርና ሚኒስቴርና አይክራ (AICCRA) ከተሰኘው የአየር ንብረት ጥናትና ምርምር ተቋም ጋር በመሆን ግንቦት 17 ቀን 2015 ዓ.ም. በራዲሰን ብሉ ሆቴል አሰናድቶት በነበረው የውይይት መድረክ ላይ ነው፡፡

በመድረኩ ላይ ኢትዮያን ጨምሮ የአፍሪካ አገሮች ከአየር ንብረት ቅድመ ማስጠንቀቂያ ጋር በተያያዘ የተቻላቸውን ጥረት ቢያደርጉም፣ ተቋማዊ አቅማቸውንና እንዲሁም ለዚያ የሚሆነውን መሠረተ ልማት፣ የቴክኒክና የሰው ኃይል አቅም ማደግ መቻል እንዳለበት ተገልጿል፡፡

የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ማንደፍሮ ንጉሤ (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ የአየር ንብረት ለውጥን አስመልክቶ መሥራት ካለበት ነገሮች አንዱ እንዴት ተደርጎ ነው የሚተነበየው? የሚለው ነው፡፡ ትንበያ በተቋም ደረጃም ሆነ በግለሰብ ደረጃ አቅም ይፈልጋል ያሉት ማንደፍሮ (ዶ/ር)፣ አሁን ላይ ኢትዮጵያ ባላት የተቋማት አቅምና ባላት ሳይንቲስቶች ይህን ማሟላት ከባድ ነው ብለዋል፡፡ ይኼ አቅም እስኪፈጥር ግን አቅም ያላቸውን ተቋማት ወደ አገሪቱ በማምጣትና አቅማቸውን ከመጠቀም ጎን ለጎን የራስን አቅም እየገነቡ የመተንበይ አቅም ማሳደግ ወሳኝ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ አክለዋል፡፡

መረጃውን መሰብሰብ መተንተን፣ የተነተነውን ወደ ምክረ ሐሳብ ቀይሮ ማሠራጨት ላይ የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ከአጋር ድርጅቶች ጋር እየተሠራ እንደሚገኝ ተጠቅሷል፡፡

የአይክራ የምሥራቅና ደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ፕሮግራም መሪ የሆኑት ዳዊት ሰለሞን (ዶ/ር) እንደተናገሩት፣ እርሳቸው የሚመሩት ተቋም በአሁኑ ሰዓት የአፍሪካ የአየር ንብረት ምን ይመስላል? የሚለውን በተመረጡ ስምንት ዘርፎች ያጠናል፡፡ የአየር ንብረት በማክሮ ኢኮኖሚ፣ ጥቅል የአገር ውስጥ ምርት (ጂዲፒ)፣ በዋጋ ንረት፣ በሰብል እህልና በእንስሳት ሀብት ላይ ምን ዓይነት ተፅዕኖ አለው? የሚሉትን ጉዳዮች ካለፈው፣ ከአሁኑና ከወደፊቱ ጋር አተያይና ምልከታ እንደሚደረግ ዳዊት (ዶ/ር) አክለዋል፡፡

በኢትዮጵያ ባለፉት ሁለትና ሦስት ዓመታት በምሥራቅ፣ በደቡብ ምሥራቅና በደቡብ የአገሪቱ ክፍሎች ድርቅ ከፍተኛ የሆነ አደጋ አድርሷል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ በአገር ውስጥ የሚገኙ ተቋማትም ሆነ አኅጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ተቋማት መረጃዎች በመስጠት የነበራቸው ሚና ቅንጅት ምን ጥያቄ ይነሳበት ነበር፡፡

ዳዊት (ዶ/ር) እንደሚሉት፣ የተከሰተው ድርቅ ኢትዮጵያንም ሆነ የአካባቢው አገሮችን ጎድቷል፡፡ መታወቅ ያለበት ጉዳይ ድርቁ ምን ይመስላል? መቼ ይመጣል?  እንዴት ነው በሚለው ላይ ከቀጣናዊ የአየር ንብረት ለውጥ የትንበያ ማዕከላት ጋርና ከኢትዮጵያ ሚትዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ጋር የቅድመ ትንበያ ሥራ ተሠርቷል፡፡

‹‹ሁልጊዜም ቢሆን ድርቅ ይመጣል፡፡ እዚህ ላይ የቅድመ ትንበያ ድርጊት ወሳኝ ነው፡፡ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ሥርዓት ያስፈልጋል፡፡ ከዚያ ሌላ ለቅድመ ምላሹ መዘጋጀትም ይገባል፤›› ዳዊት (ዶ/ር) ብለዋል፡፡

‹‹Early Warning for All›› የሚል ትልቅ ፖሊሲ እየተዘጋጀ መሆኑን ያስረዱት ዳዊት (ዶ/ር)፣ ይህ ፖሊሲ ‹‹እንዴት አድርገን ነው ቅድመ ማስጠንቀቂያና ለእያንዳንዱ ሰው ማድረስ የሚቻለው፤›› የሚል ይዘት ያለው ነው፡፡ በተጨማሪም ይኼንን መረጃ በመመርኮዝ መንግሥትም ሆነ መንግሥታዊ ያልሆነ አካል እንዴት አድርጎ ራሱን ያዘጋጃል የሚለው ሁለተኛው ጉዳይ ነው፡፡

በአይክራ – የኢልሪ አማካሪ ብርሃኑ በላይ (ፕሮፌሰር) እንዳሉት፣ የአየር ንብረት ለውጥ በተለይም እንደ ኢትዮጵያ ላለ በግብርና ላይ ለሚተዳደር አገር በጣም ከፍተኛ የሆነ ጫና የሚያደርግ ክስተት ነው፡፡

ከማንኛውም አገር በላይ ኢትዮጵያ በድርቅና በውኃ ሙላት የምትቸገር አገር ስለሆነች ለዚህ የሚሆኑ የተለያዩ ስትራቴጂዎችንና ምክሮችን የመቋቋም ሥራ ያስፈልገዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የቤት ባለንብረቶች የሚከፍሉትን ዓመታዊ የንብረት ታክስ የሚተምን ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ

በአዋጁ መሥፈርት መሠረት የክልልና የከተማ አስተዳደሮች የንብረት ታክስ መጠን...

እንደ ንብረት ታክስ ያሉ ወጪን የሚያስከትሉ አዋጆች ከማኅበረሰብ ጋር ምክክርን ይሻሉ!

የመንግሥትን ገቢ በማሳደግ ረገድ አስተዋጽኦ እንዳላቸው የሚታመኑት የተጨማሪ እሴት...

ለዓለምም ለኢትዮጵያም ሰላም እንታገል

በበቀለ ሹሜ ያለፉት ሁለት የዓለም ጦርነቶች በአያሌው የኃያል ነን ባይ...