ጥንት ጀምሮ በቃል ሲነገር የሚኖረውን የአባቶቻችንን ተረት ብንመለከተው ብዙ የሚጠቅም ምክር እናገኝበታለን፡፡ ‹‹ደባ ራሱን ስለት ድግሱን›› እንደሚባለው ክፉ ሥራ መሥራት ጉዳቱ ለሠሪው ነው፡፡ ንብ ሌላውን አጠቃለሁ ስትል በመርዟ ትነድፋለች፡፡ እሷም ይህን ክፋት ከሠራች በኋላ አንድ ደቂቃ ሳትቆይ ትሞታለች፡፡ የእሳት ራትም እንዲሁ መብራቱን ለማጥፋት ስትሞክር ተቃጥላ ራሷ ትጠፋለች፡፡ ትንኝ የሰው ዓይን ለማወክ ትገባና ሕይወቷን አጥታ ተጎትታ ትወጣለች፡፡ እንክርዳድን የዘራ እንክርዳድን ያመርታል፡፡ ክፉ የሠራም ሰው በክፋቱ ይጠፋል፡፡ ሰው የሚድነው በምነቱና በቅንነቱ ብቻ ነው፡፡
- አያሌው ዘብሔረ ጎጃም ‹‹አዲስ ዘመን›› (የካቲት 20 ቀን 1935 ዓ.ም.)