እንጥረብ ዘላ ጉያው ተሸጉጣ፣
በድሪቶ ገብታ በለበሰው ቁምጣ፣
የገበሬውን ደም መጥምጣ መጥምጣ
በደበሎው ፀጉር ሌትም ቀንም ዘልላ፣
የተቀደሰውን የተማሪን ገላ፣
በልታ ስትጠግብ ስትመስል ቅሬላ፣
ቁንጫም እንደ ሰው መታመም ታውቃለች፣
ደም ብዛት ሲይዛት መዝለል ታቆማለች፣
ቁንጫም እንደ ሰው መድኃኒት ስታጣ፣
መብረር ሲቸግራት ጠግባ ተንዘርጥጣ
እንደተቆዘረች ትሞታለች ፈርጣ፡፡
ታደለ ገድሌ ‹‹ቅኔ እና ቅኔያዊ ጨዋታ ለትዝታ›› (1997 ዓ.ም.)