Thursday, September 21, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዝንቅ‹‹የምን ሰይጣን ነው ገፍትሮ የጣለኝ››

‹‹የምን ሰይጣን ነው ገፍትሮ የጣለኝ››

ቀን:

ይቺው ወርቅ ያንጥፉ ይቺው ባለቤቴ ዛሬ እንዲህ ዘምና ፍዳዬን ልታስቆጥረኝ ያኔ ክፉኛ ተጃጅላብኝ ነበር ነው የምላችሁ፡፡ የዚያን ለት ልብሷንና ጫማዋን ከገዛን በኋላ ላዳራችን ወደ አልቤርጎ ነበር የሔድነው፡፡ አልጋ ከያዝን በኋላ ዘበኛውን ወደ ዘመዶቻቸው ቤት ሸኝተን ለስላሳ መጠጥ አስመጥተን እየጠጣን ሳለን ሳልገዛው የረሳሁት እቃ ስለነበር ወደሱቅ ትቼያት ሄጄ ሳለሁ የሠራችው ሥራ ምን ጊዜም አይረሳኝም፡፡

የተከራየነው የሽቦ አልጋ የረገበ ወይም የተወጠረ መሆኑን ለመፈተሽ ያህል አንድ ሁለቱ በቁሜ እየወደቅሁበት ስንጋለልበት ለካስ ወርቅ ያንጥፉ አይታኝ ኖሯል፡፡ እኔ ሱቅ ደርሼ እስክመጣ ድረስ እኔ እንዳደረግሁት ለማድረግ ስትንደረደር ሔዳ አልጋው ላይ ስትወጣ ሽቦው አንጥሮ ከወለሉ ላይ ያነጥፋታል፡፡ ነፍስና ሥጋዋ በድንጋጤ ሲለያዩ ከወደቀችበት ተነሥታ፡ ‹‹የምን ሰይጣን ነው ገፍትሮ የጣለኝ›› ብላ ካልጋው ስር ባይኖቿ ስታፈላልግ ትልቅ ነጭ የሽንት ‹‹ፖፖ›› ታያለች፡፡ ‹‹ውይ ለካስ ይኸ ሰይጣን ኖሯል ካልጋው ስር ተቀምጦ አፈር ድሜ ያስጋጠኝ›› ትልና ፈርታ ከነክንብንቧ ከክፍሉ ጥግ ትቆማለች፡፡ ቀስ ብላ ወደ ፊት ለፊቷ ስታይ ግድግዳ ላይ የተሰቀለው ትልቅ መስታዋት መልሶ መልኳን ያሳያታል፡፡ እሷ ግን የራሷ መልክ መሆኑን ልብ ባለማለቷ ‹‹ወይ ጉዴ! የቤቷም ባለቤት ሁኔታዬን ቁመው እያዩኝ ናቸው ለካ›› በማለት ከቆመችበት እንባዋን ታፈሰዋለች፡፡

በዚህ ጭንቀት ላይ እያለች ከሱቅ ተመልሼ ስመጣ የኮካ ኮላ ጠርሙሶቹና ብርጭቆዎቹ በሙሉ ከሲሚንቶው ወለል ላይ ተከስክሰዋል፡፡ የድንጋጤ ውጋት ቀስፎ እንደያዘኝ ‹‹ወርቅ ያንጥፉ! ወርቅ ያንጥፉ!›› እያልኩ ወደ ክፍሉ ስገባ ከግድግዳ ጥግ ቆማ እየተንሰቀሰቀች ስታለቅስ አገኘኋት፡፡ ምን እንደ ሆነች ስጠይቃት አሁን ያጫወትኳችሁን ድርጊቷን ገለጸችልኝና የገመተችውና ያሰበችው ሁሉ እሷ እንዳለችው አለመሆኑን በጥሞና አስረድቼያት አረጋጋኋት፡፡

  • አበራ ለማ ‹‹የማለዳ ስንቅ›› (1980)
spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ኮሚሽን ሪፖርት ምን ይዟል?

ለአሜሪካ ድምፅ አማርኛ ዝግጅት የስልክ አስተያየት የሰጡ አንድ የደንበጫ...

መንግሥት በአማራ ክልል ለወደሙ የአበባ እርሻዎች ድጋፍ እንዲያደርግ ተጠየቀ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአማራ ክልል የተፈጠረው ግጭትና አለመረጋጋት በቢዝነስ...

አምናና ዘንድሮ!

እነሆ መስከረም ጠብቶ በአዲስ መንፈስ ተሞልተን መንገድ ጀምረናል። ‹‹አዲስ...