Sunday, October 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትለአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ በተመደበው ኢትዮጵያዊ ዳኛ ላይ ሥጋት እንዳለው የግብፅ ክለብ...

ለአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ በተመደበው ኢትዮጵያዊ ዳኛ ላይ ሥጋት እንዳለው የግብፅ ክለብ አስታወቀ

ቀን:

  • ክለቡ ዳኛው ‹‹የጡረታ መውጫው የመጨረሻ ጨዋታ›› መሆኑ አሳስቦኛል ብሏል

የ2023 የአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ እንዲመራ በአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) የተመደበው ኢንተርናሽናል ዳኛ ባምላክ ተሰማ ከግብፁ ክለብ አል አህሊ ቅሬታ ቀረበበት፡፡

አል አህሊ ከሞሮኮ ዋይዳድ ክለብ ጋር የሚያደርገውን የፍፃሜ ጨዋታ እንዲመራ የተመረጠው ባምላክ መመረጥ እንዳሳሰባቸው የግብፁ ክለብ ዋና አሠልጣኝ ማርሴል ኮላር ተናግረዋል፡፡

እሑድ ሰኔ 4 ቀን 2015 ዓ.ም. አል አህሊና ዋይዳድ የሚያደርጉትን ጨዋታ ኢትዮጵያዊው ዳኛ እንዲመሩት በካፍ መመደባቸው ይታወቃል፡፡

በካይሮ ዓለም አቀፍ ስታዲየም በመጀመርያው ዙር የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ 2 ለ 1 ማሸነፍ የቻለው የግብፅ ክለብ ሲሆን፣ በሞሮኮ የሚያደርገው የፍፃሜ ጨዋታ ግን ኢትዮጵያዊ ዳኛ መመደቡ እንዳሠጋቸው የግብፁ አህራም ኦንላይን ጋዜጣ አስነብቧል፡፡

‹‹ከዋይዳድ ጋር የምናደርገውን የሁለተኛ ጨዋታ እንዲመራ ባምላክ መሰየም በጣም የሚያበሳጭና አሳሳቢ ጉዳይ ነው፡፡ ምክንያቱም የመጨረሻው ጨዋታ ስለሚሆንና እሱም ጡረታ ስለሚወጣ፤›› በማለት የአል አህሊው አሠልጣኝ ማርሴል ከጨዋታ በኋላ በነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

‹‹ዳኛው የመጨረሻ ጨዋታቸው ስለሆነ ምንም ዓይነት ቁርጠኝነት ወይም ኃላፊነት አይወስዱም፤›› ሲሉ ሥጋታቸውን አስቀምጠዋል፡፡

ሆኖም አሠልጣኙ ፍትሐዊ የሆነ ዳኝነት ከኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል ዳኛ እንደሚጠብቁ ተስፋ እንዳላቸውም አልሸሸጉም፡፡

በግብፁ ጋዜጣ የወጣውን መረጃ ተከትሎ ሪፖርተር ያነጋገራቸው ኢንተርናሽናል ዳኛ ባምላክ ተሰማ፣ ‹‹የካዛብላንካው የፍፃሜ ጨዋታ የመጨረሻ ጨዋታቸው መሆኑና በጡረታ ለመገለል ወስነዋል ተብሎ የተዘገበው የሐሰት ዜና ነው፤›› ሲሉ አስተባብለዋል፡፡

‹‹የተባለው ዜና ሐሰት ነው፡፡ እኔ ዝግጅቴን እያደረግሁ ነው፤›› በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

የ43 ዓመቱ ባምላክ እ.ኤ.አ. ከ2012 ጀምሮ 38 የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎችን ሲመሩ ሁለቱ የፍፃሜ ጨዋታ ናቸው፡፡ ባምላክ ከካፋ ውድድሮች ባሻገር ዓለም ዋንጫን ጨምሮ በርካታ የፊፋ የእግር ኳስ ውድድሮችን መምራት መቻላቸው ይታወቃል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ተመድንና ዓለም አቀፋዊ ሕግን ከእነ አሜሪካ አድራጊ ፈጣሪነት እናድን!

በገነት ዓለሙ በእኔ የተማሪነት፣ የመጀመርያ ደረጃ ተማሪነት ጊዜ፣ የመዝሙር ትምህርት...

የሰላም ዕጦትና የኢኮኖሚው መንገራገጭ አንድምታ

በንጉሥ ወዳጅነው ፍራንክ ቲስትልዌይት የተባሉ አሜሪካዊ ጸሐፊ ‹‹The Great Experiment...

ድህነት የሀብት ዕጦት ሳይሆን ያለውን በአግባቡ ለመጠቀም አለመቻል ነው

በአንድነት ኃይሉ ድህነት ላይ አልተግባባንም፡፡ ብንግባባ ኖሮ ትናንትም ምክንያት ዛሬም...