Friday, September 22, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

ይቅርብኝ!  

ትኩስ ፅሁፎች

ዓይኔ አይይ ይቅርብኝ ማየቴ ካልረዳኝ፣

የመጥፎ ድርጊት ጦር ጨረሩ ከጐዳኝ፡፡

አላውራ ይቅርብኝ ሰሚ ከበደነ፣

የአንደበቴ ቃል ወጥቶ ከባከነ፡፡

አልልበስ ይቅርብኝ መልበስ ካላሞቀኝ፣

ሞቀኝ ብዬ ሳወልቅ ብርዱ ካሳቀቀኝ፡፡

አልማር ይቅርብኝ መማር ካለወጠኝ፣

ቅቤ ጠብ ላይል ዝንት ዓለም ከናጠኝ፡፡

አላፍቅር ይቅርብኝ ማፍቀር ካሰቃየኝ፣

የሌባ ጣት ቅስሮሽ ሌት ተቀን ካጋየኝ፡፡

ይቅርብኝ መፈቀር አጉል ካንጠራራኝ፣

ከራሴ ህሊና ዘወትር ካጣለኝ፡፡

አልጸልይ  ይቅርብኝ ጸሎት ካልሠመረ፣

በአፌ እየማለልኩ ልቤ ከጨፈረ፡፡

አላልቅስ ይቅርብኝ ለቅሶ እኔን ካልረዳ፣

በ’ንባ ታጥቦ ላያልቅ የዚህ ዓለም ፍዳ፡፡

ምንም ምን ይቅርብኝ ምንም ምንም ነገር፣

አድሮ ሊጥ ከሆነ እንጀራው ሲጋገር፡፡

ይኼ ሁሉ ነገር እክል ከበዛበት፣

ከንቱ ባያደክመኝ ቢቀር ምናለበት?

   ምንም!

  • አፀደ ውድነህ መንግሥቱ “ድንጋይ መጽሐፍ ነው” (2005)
- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች