Saturday, September 30, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናከቀጣዩ ዓመት በጀት ውስጥ 281 ቢሊዮን ብሩ የበጀት ጉደለት ነው ተባለ

ከቀጣዩ ዓመት በጀት ውስጥ 281 ቢሊዮን ብሩ የበጀት ጉደለት ነው ተባለ

ቀን:

ለቀጣዩ በጀት ዓመት ከቀረበው 801.65 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ በጀት ውስጥ 281 ቢሊዮን ብር የሚሆነው ያልተጠራ የበጀት ጉድለት መሆኑ ተገለጸ።

የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ዛሬ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡት የበጀት ሪፖርት እንደገለጹት ለ2016 ዓ.ም. በጀት ዓመት የቀረበው አጠቃላይ በጀት አብዛኛው ከአገር ውስጥ የገቢ ምንጮች የሚሸፈን ነው።

ነገር ግን ለበጀቱ መሸፈኛ ይገኛል ተብሎ በታቀደው አጠቃላይ ገቢና ወጪ ይሆናል በተባለው 801.65 ቢሊዮን ብር መካከል፣ 281 ቢሊዮን ብር ያልተጣራ የበጀት ጉደለት መሆኑን ተናግረዋል።

ይህ የበጀት ጉድለት የሚሸፈነውም ከአገር ውስጥና ከውጭ ብድር እንደሚሆን የጠቀሱት ሚኒስትሩ፣ ከአጠቃላይ የበጀት ጉድለቱ ውስጥ 39 ቢሊዮን ብር ከውጭ ብድር እንደሚሸፈን ተናግረዋል። የተቀረው 242 ቢሊዮን ብር ደግሞ ከአገር ውስጥ ብድር እንደሚሸፈን ገልጸዋል።

ይገኛል ተብሎ ከታቀደው የአገር ውስጥና የውጭ ብድር ውስጥ 53.7 ቢሊዮን ብር የሚሆነው ተመልሶ ለአገር ውስጥና ለውጭ ዋና ብድር ክፍያ የሚውል በመሆኑ፣ የበጀት ዓመት የተጣራ የበጀት ጉድለት 227 ቢሊዮን ብር እንደሚሆንና ይህም ከአጠቃላይ የአገር ምርት ያለው ድርሻ 21 በመቶ መሆኑን ተናግረዋል።

ለበጀት ጉድለቱ መሸፈኛ የሚሆነው አብዛኛው ብድር ከአገር ውስጥ ምንጮች የሚወሰድ ከመሆኑ አኳያ የዋጋ ንረት ሊያስከትል የሚችል ቢሆንም በዋጋ ንረት ላይ የጎላ ተጽዕኖ እንዳይፈጥር ብድሩ በግምጃ ቤት ሰነድና የመካከለኛ ዘመን ቦንድ በመሸጥ ለማግኘት መታቀዱን ገልጸዋል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአማራ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ

እሑድ ጠዋት መስከረም 13 ቀን 2016 ዓ.ም. የፋኖ ታጣቂዎች...

ብሔራዊ ባንክ ለተመረጡ አልሚዎች የውጭ አካውንት እንዲከፍቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የፈቀደበት መመርያና ዝርዝሮቹ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ አጠቃቀምንና ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮችን...

እነ ሰበብ ደርዳሪዎች!

ከሜክሲኮ ወደ ዓለም ባንክ ልንጓዝ ነው። ሾፌርና ወያላ ጎማ...