ልብሽን በውስጤ ይዤ እኖራለሁ (ልቤ ውስጥ አድርጌ)
መቼም አይለየኝ
(የትም ቦታ ብሄድ አንቺም ትሄጃለሽ
ፍቅሬ ሆይ ውዲቱ፤ ያደርግሁት ሁሉ እኔ ለብቻዬ
ያንቺው ፈጠራ ነው ፍቅሬ ወለላዬ)
አንዳችም አልራራም ዕድል የሚሉትን
(ዕድሌ ነሽና፣ የኔ ወለላዬ)
አልሻም ዓለምም
(ውብ ነሽና ዓለሜ፤ የእኔ ሀቀኛያቱ)
የጨረቃ ትርጉም የመቼውም ቢሆን አንቺው ስለሆንሽ
ፀሐይም ዘወትር ቢዘፍን እንዳሻው አሁንም አንቺው ነሽ
እነሆ ጥልቅ ምሥጢር ማንም የማያውቀው
(የሥሩ ሥርና የምቡጡም እምቡጥ የሰማይ ሰማይ ዛፍም
እንደሆነ ስያሜው ሕይወት፤ ሆኖም
የሚያድግ ከሚመኘው በላይ ነፍስም ሆነ አዕምሮ ከሚደብቀው)
ይህ ነው ዕፁብ ድንቁ ኮከብን ከኮከብ ለይቶ ያኖረው
ልብሽን በውስጤ ይዤ እኖራለሁ (ልቤ ውስጥ አድርጌ)
ከኢኢ ካሚንግስ (1894 – 1962) ስድ ትርጉም በዳዊት ዘኪሮስ