ሰነፍ ሆይ እስከ መቼ ትተኛለህ? ከእንቅልፍህስ መቼ ትነቃለህ? ጥቂት ትተኛለህ፣ ጥቂትም ትቀመጣለህ፣ ጥቂትም ታንቀላፋለህ፣ ጥቂት ጊዜም እጅህን ወደ ደረትህ ትሰበስባለህ፤ ከዚህም በኋላ እንደ ክፉ መልእክተኛ ድህነት፣ እንደ ደገኛ ወራሪም ችጋር፣ በድንገት ይመጣብሃል፡፡ ሰነፍ ባትሆን ግን መከር እንደ ውኃ ምንጭ ይመጣልሃል፣ ድህነት ግን እንደሚሸሽ ክፉ ወራሪ ከአንተ ይርቃል፡፡ ዳግመኛም ሰነፍ ሰው እጁን ወደ ብብቱ ይሸሽጋል፤ ወደ አፉ ለማቅረብም ይታመማል አለ፡፡ ጥበበኛ ሰው ለራሱ አላዋቂ መስሎ ይታያል፤ ሰነፍ ሰው እጁን አቅፎ ሥጋውን በላ አለ፡፡
- ‹‹ዲድስቅልያ›› (2004)