Friday, May 17, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ፍሬከናፍር‹‹ተፀፅጽተናል፤ ለተጎዱት ሁሉ ይቅርታ እንጠይቃለን!››

‹‹ተፀፅጽተናል፤ ለተጎዱት ሁሉ ይቅርታ እንጠይቃለን!››

ቀን:

የሮማኒያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ በኬንያ የሚገኙት አምባሳደሩ አፍሪካውያንን ከጦጣ ጋር ማነፃፀራቸው ተከትሎ ለተነሳው ቁጣ የሰጠው ይፋዊ ቃለ ይቅርታ፡፡ እንደ ቢቢሲ ዘገባ፣ የሮማኒያ አምባሳደር ድራጎስ ቲጋው ባለፈው ሚያዝያ አጋማሽ በናይሮቢ በሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት ሕንፃ ውስጥ ሆነው አንድ ጦጣ በመስኮት ከተመለከቱ በኋላ፣ ‹‹የአፍሪካ ቡድን ተወካዮች ሊቀላቀሉን›› ሲሉ ማፌዛቸውን ተከትሎ ይቅርታ የጠየቀው የሮማኒያ መንግሥት፣ አምባሳደሩን ወደ ቡካሬስት ጠርቷል። የዘረኝነት ባህሪም ሆነ አስተያየት ፈጽሞ ተቀባይነት እንደሌለው በሰኔ 4 ቀን 2015 ዓ.ም.  መግለጫው ያመለከተው የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ፣ የአምባሳደሩ ንግግር ሮማኒያ ከአፍሪካ አገሮች ጋር ያላት ግንኙነትን እንደማያበላሽ ተስፋ እናደርጋለን ብሏል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ