Saturday, September 23, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናበዋግኽምራ ብሔረሰብ ዞን ከ20 ሺሕ በላይ ተፈናቃዮች በከፋ ችግር ውስጥ መሆናቸው ተገለጸ

በዋግኽምራ ብሔረሰብ ዞን ከ20 ሺሕ በላይ ተፈናቃዮች በከፋ ችግር ውስጥ መሆናቸው ተገለጸ

ቀን:

በአማራ ክልል ዋግኽምራ ብሔረሰብ ዞን በሁለት ወረዳዎች፣ በሰሜኑ ጦርነት የተፈናቀሉ ከ20 ሺሕ በላይ ሰዎች ወደ ቀያቸው ባለመመለሳቸው በከፋ ችግር ውስጥ መሆናቸውን የዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር አስታወቀ፡፡

በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት ከቄያቸው የተፈናቀሉ ከ20 ሺሕ በላይ ሰዎች ወደ ቄያቸው ባለመመለሳቸው፣ በከፋ ችግርና እንግልት ውስጥ መሆናውን ለሪፖርተር የገለጹት የዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር አደጋ መከላከል የቅድመ ማስጠንቀቂያ ምላሽ ቡድን መሪ ወ/ሮ ዝናሽ ወርቁ ናቸው፡፡

‹‹በከፋ ችግር ውስጥ ናቸው›› የተባሉት ተፈናቃዮቹ የተፈናቀሉት ከአበርገሌና ጻግብጅ ወረዳዎች እንደሆነ፣ ነዋሪዎቹ ለመፈናቀል የተገደዱት በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት የሕወሓት ታጣቂዎች ወረዳዎቹን በመቆጣጠራቸው እንደነበር፣ አሁንም ቢሆን ወረዳዎቹ ሙሉ ለሙሉ ከታጣቂ ቡድኑ ነፃ ባለመውጣታቸው ተፈናቃዮቹን ወደየቄያቸው መመለስ አልተቻለም ተብሏል፡፡

እንደገለጻው ከሆነ፣ በአበርገሌ ወረዳ 5,080፣ በጻግብጅ ወረዳ ደግሞ 15,227 በአጠቃላይ ከሁለቱም ወረዳዎች ከ20 ሺሕ በላይ ተፈናቃዮች ወደ ቀድሞ ቄያቸው እንዳልተመለሱና በከፋ ችግር ውስጥ እንደሚገኙ ተገልጻል፡፡

በዞኑ በሚገኙ ሁለት ወረዳዎች ውስጥ ያሉ ከ22 በላይ ቀበሌዎች አሁንም (ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ) በሕወሓት ታጣቂዎች ቁጥጥር መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን፣ ከእነዚህ ቀበሌዎች ተፈናቅለው በሰቆጣ የሚገኙ ሰዎችን ወደ መኖሪያ ቤታቸው መመለስ እንዳልተቻለ፣ የዕርዳታ እጥረትም ፈተና መሆኑ ተነግሯል፡፡

ከአበርገሌና ጻግብጅ ወረዳዎች ተፈናቅለው በሰቆጣ ከተማ መጠለያ ካምፖች የሚገኙ ከ79 ሺሕ በላይ ሰዎች ከቀያቸው ተፈናቅለው የነበረ ሲሆን፣ አብዛኛዎቹን መመለስ ቢቻልም ከ20 በላይ የሚሆኑትን ግን መመለስ አልተቻለም፡፡

ተፈናቃዮቹ አሁን ያሉበትን ሁኔታ በተመለከተ ማብራሪያ የተሰጠው፣ የድጋፍ እጥረት እንዳለ፣ ተፈናቃዮቹ በወዳጅ ዘመድ ቤት ተጠግተው እንደሚገኙ፣ የመሠረታዊ ፍላጎቶች ከፍተኛ እጥረት እንደተጋረጠባቸው፣ ከክልሉ የሚሰጠው ዕርዳታ አነስተኛና በውቅቱ የማይደርስ በመሆኑ የተለያዩ የተራድኦ ድርጅቶች ድጋፍ እንዲያደርጉ ነው፡፡

በሁለቱ ወረዳዎች ተፈናቅለው ከነበሩ 79 ሺሕ ሰዎች መካከል ዕድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ 16 ሺሕ ሕፃናት፣ ስምንት ሺሕ ነፍሰ ጡሮችና በርካታ አረጋዊያንና አቅመ ደካሞች በመጠለያ ካምፕ እንዳሉ ሲገለጽ የነበረ ሲሆን፣ አሁን ከ50 ሺሕ በላይ የሚሆኑት ወደየቄያቸው መመለስ ቢቻልም ካተመለሱት መካከልም ነፍሰጡር እናቶች፣ ሕፃናት፣ አረጋዊያን ሰዎች እንዳሉ ተመላክቷ፡፡

ከሕወሓት ታጣቂዎች ነፃ ወጥተዋል በተባሉ ቀበሌዎች የተመለሱ ተፈናቃዮችና ሳይፈናቀሉ በዚያው ጸንተው የኖሩ ሰዎች አካባቢው ቤት ንብረቸው በጦርነት በመውደሙ፣ ማሳቸውን ከሁለት ዓመት በላይ እህል ባለመዘራቱ ምክንያት ምርት ስለሌለው ድጋፍ እንደሚሹ ተመላክቷል፡፡

በጻግብጅና አበርገሌ ወረዳ የሚገኙ ነዋሪዎች ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ምንም እንኳ ከሰቆጣ የተለያዩ መጠለያ ጣቢያዎች ወጥተው ወደ ቄያቸው ቢመለሱም፣ ቤት ንብረታቸው እንደወደመ፣ ገና ወደ ቤታቸው ያልተመለሱ ሰዎች መኖራቸውን፣ አሁንም ቢሆን የሕወሓት ታጣቂዎች ‹‹እንመጣለን፣ አካባቢውን ዳግም እንቆጣጠራለን›› እያሉ በሚነዙት ወሬ ከፍተኛ ሥጋት እንዳለባቸው አስረድተው፣ የሚመለከተው አካል በድጋሚ ችግር ሳይገጥማቸው መፍትሔ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ኮሚሽን ሪፖርት ምን ይዟል?

ለአሜሪካ ድምፅ አማርኛ ዝግጅት የስልክ አስተያየት የሰጡ አንድ የደንበጫ...

መንግሥት በአማራ ክልል ለወደሙ የአበባ እርሻዎች ድጋፍ እንዲያደርግ ተጠየቀ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአማራ ክልል የተፈጠረው ግጭትና አለመረጋጋት በቢዝነስ...

አምናና ዘንድሮ!

እነሆ መስከረም ጠብቶ በአዲስ መንፈስ ተሞልተን መንገድ ጀምረናል። ‹‹አዲስ...