Saturday, July 13, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናከ12 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ለከፍተኛ የምግብ እጥረት መጋለጣቸው ተነገረ

ከ12 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ለከፍተኛ የምግብ እጥረት መጋለጣቸው ተነገረ

ቀን:

በኢትዮጵያ ከ12 ሚሊዮን በላይ ወገኖች ከፍተኛ የምግብ እጥረት መጋለጣቸውን፣ የብሔራዊ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ለሪፖርተር አስታወቀ፡፡

በመላው ኢትዮጵያ በተለያዩ ክልሎች የሚገኙ ከ12 ሺሕ በላይ ለሚሆኑ ሰዎች ከፍተኛ የምግብ እጥረት እንዳጋጠመ፣ የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያና ተወካይ ዳይሬክተር አቶ አታለል አቡሃይ አስረድተዋል፡፡

በጣም አሳሳቢ የሆነው ጉዳይ የቅድሚያ ቅድሚያ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ወገኖች መሆኑን ያስረዱት አቶ አታለል፣ ‹‹የቅድሚያ ቅድሚያ ድጋፍ የሚስፈልጋቸው ተብለው በአራት ኳርተሮች የተለዩ አሉ፡፡ አሁን ያለንበት ወር ሦስተኛው ኳርተር ነው፡፡ በዚህ ወር የቅድሚያ ቅድሚያ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ተረጂ መገኖች አሉ፤›› ብለዋል፡፡

‹‹በጣም የተጎዱ ሰዎች አሉ፤›› ያሉት የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያው፣ ለአብነትም ጊዜያዊ የምግብ እጥረት ያጋጠማቸው በሲዳማ ክልል ከ28 ሺሕ በላይ፣ በጋምቤላ ክልል 600፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል 62 ሺሕ፣ አፋር ክልልን ጨምሮ በአጠቃላይ ከ108 ሺሕ በላይ ከፍተኛ ጉዳት ያጋጠማቸው ሰዎች እንዳሉ አስረድተዋል፡፡

‹‹በዚህ ወቅት በኢትዮጵያ በአጠቃላይ የቅድሚያ ቅድሚያ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ከ12 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ተረጂዎች አሉ፤›› ሲሉም አክለዋል ገልጸዋል፡፡

ከፍተኛ የምግብ እጥረት ያጋጠመበት ምክንያት ምን እንደሆነ ማንራሪያ እንዲሰጡ ሪፖርተር ላቀረበላቸው ጥያቄም የምርት መጠን ማነስ፣ የሰብል ብልሽት ማጋጠሙና የዓለም የምግብ ድርጅት በቅርቡ ድጋፍ በማቆሙ ምክንያትም እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

ኮሚሽኑ ያስረዳው ይህ የተረጅዎች ቁጥር ግን ቋሚ እንዳልሆ ማለትም ብዙዎቹ በአንድ ወቅት እንደሚጨምር፣ በሌላ ወቅት ደግሞ ሊቀንስ እንደሚችል ኮሚሽኑ ባደረገው ዳሰሳ መሠረት ከ12 ሚሊዮን በላይ የምግብ እጥረት ያገጠማቸው ሰዎች ቁጥራቸው በመስከረም 2016 ዓ.ም. ወደ ስምንት ሚሊዮን ዝቅ ሊል እንደሚችል ነው፡፡

በዚህ ወቅት የተረጂዎች ቁጥር የጨመረው ክረምት በመሆኑ ዜጎች ያላቸውን ምግብና ምግብ ነክ ነገር የሚጨርሱበት ወቅት በመሆኑ ነው ያሉት አቶ አታለል፣ ‹‹ተረጂዎች በጣም ከፍተኛ የሚባል የጉዳት ደረጃ ላይ ነው ያሉት፤›› ብለዋል፡፡

ለእነዚህ ወገኖች መንግሥት ድጋፍ የሚያደርገው ምግብና የምግብ ነክ የሆኑ ቁሶችን እንደሆነና በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በሶማሌ፣ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልሎች በድርቅ አደጋና በፀጥታ ምክንያት ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች መንግሥትና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በአጠቃላይ ከ605 በላይ ሚሊዮን ብር የሚሆን የገንዘብ ድጋፍ እንደቀረበላቸውም አስረድተዋል፡፡

በሸገር ከተማ አስተዳደር ቤት የሚፈርስባቸው፣ ከኦሮሚያ ክልል በተለይም ወለጋና ሰሜን ሸዋ ዞን በፀጥታ ችግር ምክንያት የሚፈናቀሉ ሰዎች በመኖራቸው የጠፈናቃዮች የቁጥር ጭማሪ እንዳለና እንደሌለ ማብራሪያ እንዲሰጡ ጥያቄ የቀረበላቸው አቶ አታለል፣ ‹‹የቁጥሩ ጭማሪ ውቅታዊ ነው፡፡ አንዳንዴ ቁጥሮች ከፍም ዝቅም ይላሉ፡፡ በሰው ሠራሽና በተፈጥሮ ክስተቶች የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር በክልል ደረጃ ሲታይ በትግራይ ክልል ከአምስት ሚሊዮን በላይ፣ በአማራ ክልል ከሁለት ሚሊዮን በላይ፣ እንዲሁም በአፋር ክልል ከ716 ሺሕ በላይ ተረጂዎች አሉ፤›› ብለዋል፡፡

ለትግራይ ክልል ከ2,700 በላይ ሜትሪክ ቶን፣ ለአማራ ክልል ከ83 ሺሕ በላይ ሜትሪክ ቶን፣ እንዲሁም ለአፋር ክልል ከ28 ሺሕ በላይ ሜትሪክ ቶን ሚሆን የምግብ ነክ ድጋፍ በመንግሥትና መንግሥታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ድጋፍ ማድረግ እንደተቻለና በአጠቃላይ በሦስቱም ክልሎች ወደ አራት ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን የሚጠጋ የዓይነት ድጋፍ ስለመደረጉ ገልጸዋል፡፡

በጎንደር በሚገኘው ቀበሮ ሜዳ፣ በዋግኸምራ ዞን፣ በኦሮሚያ ክልል በቦረና መጠለያ ጣቢያዎች ያሉ የተፈናቃይ አስተባባሪዎች በበኩላቸው የድጋፍ እጥረት እንዳለባቸው ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

በፀጥታ ችግር ሳቢያ ከኦሮሚያ ክልል ወለጋ፣ ከትግራይና ከቤሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች የተፈናቀሉ በጎንደር ቀበሮ ሜዳ መጠለያ ካምፕ የሚገኙ ከ2,100 በላይ ተፈናቃዮች ለከፍተኛ የምግብ እጥረት መጋለጣቸውን የመጠለያ ካምፑ አስተባባሪ አስተባባሪ አቶ መላሽ ታከለ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡ በ2015 በጀት ዓመት ድጋፍ የተደረገላቸው ሦስት ጊዜ ብቻ መሆኑን፣ መንግሥት ግን በየ45 ቀኑ ድጋፍ እንደሚያደረግ ቃል ቢገባም በወቅቱ ድጋፍ እየደረሳቸው አለመሆኑንም አስተባባሪው አስረድተዋል፡፡

በአማራ ክልል ዋግኸምራ ብሔረሰብ ዞን አስተደደር የአደጋ መከላከልና የቅድመ ማስጠንቀቂያ ምላሽ ቡድን ቡድን መሪ ወ/ሮ ዝናሽ ወርቁ በበኩላቸው፣ ተፈናቃዮች ከፍተኛ የምግብ እጥረት እንዳጋጠማቸው ገልጸዋል፡፡

በመጠለያ ጣቢያ ሰባት ሺሕ ያህል ከትግራይና ኦሮሚያ ክልሎች ለመጡና ወደ ቀዬአቸው ላልተመለሱ ተፈናቃዮች ከክልሉም ሆነ ከፌዴራሉ መንግሥትም የሚላክላቸው ዕርዳታ እንደሌለ፣ የዓለም የምግብ ፕሮግራም በስርቆት ምክንያት ድጋፍ በማቋረጡ ሳቢያ ተፈናቃዮች ለከፍተኛ የምግብ እጥረት እንደተጋረጡ አስረድተዋል፡፡

የብሔራዊ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ከፍተኛ የምግብ እጥረት አለባቸው በተባሉ የመጠለያ ጣቢያዎች የተነሳውን ቅሬታ በተመለከተ ምላሽ የሰጠው፣ ክልሎች ሪፖርት በሚያደርጉት ተፈናቃይ ልክ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ነው፡፡ የዓለም የምግብ ፕርግራም ድጋፉን በማቆሙ የድጋፍ እጥረት እንደሚያጋጥምና ተፅዕኖ እንደሚያሳድር፣ ችግሩን ለመቅረፍ መንግሥት የዲፕሎማሲ ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑን አቶ አታለል ተናግረዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የሰብዓዊ መብት ጉዳይና የመንግሥት አቋም

ሰኔ ወር አጋማሽ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ከፍተኛ የሰብዓዊ...

ከሰሜኑ ጦርነት አገግሞ በሁለት እግሩ ለመቆምና ወደ ባንክነት ለመሸጋገር የተለመው ደደቢት ማክሮ ፋይናንስ

በኢትዮጵያ የፋይናንስ ኢንዱስትሪ ውስጥ በቀዳሚነት ስማቸው ከሚጠቀሱት ውስጥ ደደቢት...