Saturday, June 15, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዜናየጎላ የኦዲት ችግር የተገኘበት የፀረ ሙስና ኮሚሽን ብልሹ አሠራርን ለመታገል ከዋና ኦዲተር...

የጎላ የኦዲት ችግር የተገኘበት የፀረ ሙስና ኮሚሽን ብልሹ አሠራርን ለመታገል ከዋና ኦዲተር ጋር ተፈራረመ

ቀን:

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ከአንድ ሳምንት በፊት ባቀረበው የመንግሥት ተቋማት የ2014 ዓ.ም. የኦዲት ሪፖርት ሒሳባቸው የጎላ የኦዲት ችግር አለባቸው ተብለው ከተዘረዘሩት ተቋማት መካከል አንዱ የሆነው ሥነ ምግባር ፀረ ሙስና ኮሚሽን፣ ብልሹ አሠራሮችንና ሙስናን ለመታገል ከፌዴራል ዋና ኦዲተር ጋር ተፈራረመ፡፡

ሁለቱ ተቋማት በሕግ የተሰጣቸውን ሥልጣንና ተግባራት መሠረት በማድረግ ከፌዴራል ተቋማት ውስጥ የመልካም አስተዳደር፣ የግልጽነትና የተጠያቂነት ሥርዓት ለማስፈን፣ ሙስናንና ብልሹ አሠራሮችን በጋራ ለመከላከል እንዲችሉ የሚያስችላቸው የመግባቢያ ሰነድ ማክሰኞ ሰኔ 27 ቀን 2015 ዓ.ም. ስምምነት ፈጽመዋል፡፡

የፌዴራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ከአንድ ሳምንት በፊት ለፓርላማው ባቀረበው የኦዲት ሪፖርት ላይ እንደተገለጸው፣ ፀረ ሙስና ኮሚሽን ሒሳባቸው የጎላ ችግር ያለበት በመሆኑ ተቀባይነት የሚያሳጣ አስተያየት ከተሰጠባቸው ተቋማት መካከል አንዱ ነው፡፡

- Advertisement -

የፌዴራል ዋና ኦዲተር የኦዲት ሪፖርት እንደሚያሳየው፣ ፀረ ሙስና ኮሚሽን ከመመርያ ውጪ ለሾፌሮች የተከፈለ የተሽከርካሪ ማሳደሪያና ማፅጃ ክፍያና መንግሥትን ለተጨማሪ ወጪ የዳረገ ግዥ በመፈጸም፣ ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበ አቅራቢ ሳለ ከፍተኛ ዋጋ ያቀረበን አቅራቢ አሸናፊ አድርጎ በመምረጥ፣ በጀት ዓመቱን  ሳይጠብቅ የተከፈለ ገንዘብ፣ ማስረጃ የሌለው ተሰብሳቢ ሒሳብና በመሳሰሉ ጉዳዮች የኦዲት ክፍተቱን አሳይቷል፡፡

በተጨማሪም የምዝገባ ሰነድ የሌለው የተከፋይ ሒሳብ፣ ሥራ ላይ ያልዋለ በጀት፣ ያለ ሒሳብ መደቡ የተመዘገበ የወጪ ሒሳብ፣ ከተሽከርካሪዎች አስተዳደር ጋር በተገናኘ 41 ተሽከርካሪዎች በግዥ፣ በስጦታ ወይም በዝውውር መሆኑን በግልጽ የሚያሳይ የንብረት ገቢ ደረሰኝ አለመቆረጥ፣ ለገቢዎች ሚኒስቴር ገቢ ያልተደረገ የገቢ ግብር፣ ከበጀት በላይ የወጣ ሒሳብ የሚሉ የኦዲት ከፍተቶች እንደተገኙበት በኦዲቱ ተጠቅሷል፡፡

ይሁን እንጂ ከአንድ ሳምንት በፊት የጎላ ኦዲት ክፍተት አለበት ተብሎ የተገለጸው የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ራሱን ሳያስተካክል ሌሎችን እንዴት ሊገመግም ይችላል በሚል ሪፖርተር ጥያቄ ያቀረበላቸው ኮሚሽነር ሳሙኤል ኡርቃቶ (ዶ/ር)፣ ‹‹ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተጠራቀሙ የመጡ የኦዲት ክፍተቶች ላይ ዕርምጃ ለመውሰድ እየተዘጋጀን ነው፤›› ብለዋል፡፡

ይህ ትብብር የሁለቱ ተቋማት የገለልተኞች ምልክት ነው ያሉት ኮሚሽነሩ፣ ‹‹ዋና ኦዲተር በሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ላይ አስተያየት ይሰጣል በሌላ በኩል ደግሞ ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በዋና ኦዲተር ላይ አስተያየት መስጠቱን ይቀጥላል፤›› ብለዋል፡፡ ይሁን እንጂ የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ንፁህ የሆነ ሥራ መሥራት እንዳለበት አስረድተው፣ በቀጣይ ሩብ ዓመት ውስጥ ዕርምጃ ለመውሰድ ለሌሎች ተቋማት ምሳሌ ለመሆን እንደሚሠሩና በዚህ የማጣራት ሒደት በተቋማቸው የሙስና ድርጊት ከተገኘ ዕርምጃ ይወስዳል ሲሉ አስታውቀዋል፡፡  

ሁለቱ አካላት ማክሰኞ ዕለት የተፈራረሙት ስምምነት በመንግሥት ተቋማት ውስጥ የተጠያቂነት፣ የመልካም አስተዳደርና የግልጽነት ሥርዓት ማስፈን እንዲቻል፣ ሙስናና ብልሹ አሠራሮች ሊከሰቱባቸው በሚችሉ ተቋማትና የሥራ ዘርፎች ላይ ተከታታይ የሆኑ ጥናቶችን በጋራ ለመሥራት ያግዛል ተብሏል፡፡ በተጨማሪም ሚስጥራዊ መረጃዎችንና ማስረጃዎችን በሚስጥር ጠብቆ ለማቆየት ይረዳል ተብሏል፡፡

የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽነር ሳሙኤል (ዶ/ር) ሁለቱ ተቋማት በመንግሥት ተቋማት የመልካም አስተዳደር እንዲሰፍን የሚጫወቱት ሚና ከፍተኛ መሆኑን፣ ሥራቸውም መረጃና ዕውቀት መር ነው ብለዋል፡፡ ኮሚሽነሩ የሚመሩት ተቋም ሰፋ ያሉ የሙስና ሥጋት ጉዳዮችን ቀድሞ በመለየት የመከላከል ሥራ ላይ የሚያተኩር በመሆኑ፣ በቀጣይ የአገር ሀብት ለታለመለት ዓላማ እንዲውል የቅድመ መከላከል ሥራ ይከናወናል ሲሉም አስረድተዋል፡፡

በመጪዎቹ አሥር ዓመታት የኢትዮጵያን ብልፅግና ለማሳካት መንግሥት የሚያደርገውን ርብርብ ማሳካት የሚቻለው ሀብት በአግባቡ መጠቀም ከተቻለ ብቻ እንደሆነ አውስተው፣ ይህ ካልሆነና ሀብት ለተለያዩ ቡድኖች የሚውል ከሆነ ኢትዮጵያ ማደግም መበልፀግም አትችልም ብለዋል፡፡

ስምምነቱ ብልሹ አሠራርን በመታገልና ተጠያቂነትና ግልጽነትን ከማስፈን አኳያ ሁለቱ ተቋማት ወሳኝ መሆናቸውን የጠቀሱት የፌዴራል ዋና ኦዲተር ወ/ሮ መሠረት ዳምጤ፣ የሁለቱ ትብብር መንግሥት ከሕዝብ ጋር ያለውን ታማኝነት የበለጠ እየተጠናከረ እንዲመጣ ይረዳል ብለዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት...

የመንግሥት የ2017 ዓ.ም በጀትና የሚነሱ ጥያቄዎች

የ2017 ዓመት የመንግሥት ረቂቅ በጀት ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ለሚኒስትሮች...

ከፖለቲካ አባልነትና ከባንክ ድርሻ ነፃ የሆኑ ቦርድ ዳይሬክተሮችን ያካተተው ብሔራዊ ባንክ ያዘጋጃቸው ረቂቅ አዋጅና መመርያዎች

የኢትዮጵያ የብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማትን የተመለከቱት ድንጋጌዎችንና የባንክ ማቋቋሚያ...

የልምድ ልውውጥ!

እነሆ መንገድ ከቦሌ ሜክሲኮ። አንዱ እኮ ነው፣ ‹‹እንደ ሰሞኑ...