Saturday, September 30, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

ፍቅረማርቆስ ደስታና ሐዲስ ዓለማየሁ

ትኩስ ፅሁፎች

ለሐዲስ ዓለማየሁ የመጀመርያ መጽሐፌን ከቡስካ በርተጀርባን እንዲገመግሙልኝ ስሰጣቸው እንዲህ አሉኝ፡- ‹‹እኔ ደራሲ ነኝ። አንተ ደሞ ይዘህ የመጣኸልኝ የድርሰት ጽሑፍ ነው፡፡  ደራሲ የደራሲን ጽሑፍ ሲገመግም እኔን ሁን ማለቱ አይቀሬ ነው፡፡ ስለዚህ በሥርዓት ደራሲን የሚዳኘው ሐያሲ ስለሆነ ለዘሪሁን አስፋው ማስታወሻ እጽፍለታለሁ። ሄደህ ስጠው!›› አሉኝ። ዘሪሁን (ለረዳት ፕሮፌሰር) የመጽሐፉን ረቂቅ ስሰጠው ቢሮው ውስጥ የተቆለሉትን የተማሪዎች ጽሑፍና ገና ያልተገመገሙ የመጽሐፍ ረቂቅ ጥራዞችን አሳየኝና ‹‹አልችልም›› አለኝ፡፡ አዲስ አበባ እስክደርስ ድረስ ያሳለፍኩት ስቃይ ትዝ ብሎኝ ይሁን በሌላ ምክንያት እዚያው ጋሽ ዘሪሁን (ረዳት ፕሮፌሰር)  ቢሮ ውስጥ አለቀስኩ፡፡ ጋሽ ዘሪሁን ደነገጡ፡፡ አባበሉኝ፡፡ የመጽሐፌን ረቂቅ ተቀብለው ሸኙኝ፡፡ ጠዋት ላይ ከጎረቤት ስልክ እንደሚፈልገኝ ሲነገረኝ ተረበሽኩ፡፡ የስልኩን እጀታ እንደያዝኩ ‹‹እንዴት አደርህ ፍቅረ ማርቆስ? ዘሪሁን ነኝ!›› ሲሉኝ ደንግጬ የስልኩን እጀታ ለቀቅኩ። እንደገና ተረጋግቼ ሳወራቸው ቢሯቸው እንድመጣ ነገሩኝ፡፡ ቢሯቸው ስገባ ከወንበራቸው ቆመው ተቀበሉኝ፡፡ ‹‹ትናንት ስላሳዘንከኝ ረቂቁን እቤት ወስጄ ከእራት በፊት አንድ ገጽ ላነብ ሙከራ ባደርግ መጽሐፉ ይዞኝ ሄደ፡፡ ትልቅ መጽሐፍ ነው!›› አሉኝ፡፡ በደስታ ሰከርኩ፡፡ ከቢሯቸው ልወጣ ስል ‹‹ምን ልታደርግ አሰብከው?›› አሉኝ፡፡ ‹‹እኔ ችሎታ እንዳለኝ ለማረጋገጥ ነበር እርስዎ ዘንድ የመጣሁት፡፡ እርሱን ደግሞ አሁን ነገሩኝ!›› አልኳቸው፡፡ እሳቸው ግን ተቃወሙኝ፡፡ ‹‹የለም የለም… ይሄ በጣም ትልቅ ጥናት ነው፡፡ መታተም አለበት፡፡ Ethiopian Studies የሚመራው ባህሩ ዘውዴ (ፕሮፌሰር)  ስለሆነ ሄደህ ለሱ ስጠው! እኔ የጻፍኩልህን ሂስም ጨምረህ ስጠው!›› አሉኝ፡፡ አመስግኜ ከቢሯቸው ወጣሁና ለባህሩ ዘውዴ (ፕሮፌሰር) ሰጠኋቸው፡፡ እሳቸው ካነበቡት በኋላ ተባበሩኝ፡፡ ከቡስካ በስተጀርባም ታተመች፡፡

  • ፍቅረማርቆስ ደስታ በጨዋታ እንግዳ መርሐ ግብር ላይ ያወጋው
- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች